Connect with us

ደኑ ተቃጠለ አንበል፤ እየነደደ ያለው ነጋችንና ተስፋችን ነው

ደኑ ተቃጠለ አንበል፤ እየነደደ ያለው ነጋችንና ተስፋችን ነው

ነፃ ሃሳብ

ደኑ ተቃጠለ አንበል፤ እየነደደ ያለው ነጋችንና ተስፋችን ነው

ደኑ ተቃጠለ አንበል፤ እየነደደ ያለው ነጋችንና ተስፋችን ነው

(ሄኖክ ስዩም ~ድሬ ቲዩብ)

ሰሞኑን በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጥሮ ሀብቶቻችን ላይ የእሳት ቃጠሎ ተከስቷል፡፡ የሚነደው ተፈጥሮ ቦታም ቀጠናም አልመረጠም፡፡ በጋው በመጣ ቁጥር እሳት ለማጥፋት መጠራራቱ መፍትሔ አይደለም፡፡ አስቀድሞ እሳቱን እንዳይነሳ ለማድረግ መስራት ያስፈልጋል፡፡

የተፈጥሮ ሀብቱን እያወደመ ያለው እሳት መነሻው ብዙ አይነት ነው፡፡ ለብሔራዊ ፓርኮችና ለደን ጥብቅ ስፍራዎች አጎራባች አርሶ አደሮች ለማሳ ዝግጅት የሚለኩሱት እሳት ተሰዶ የሚገባው ወደ ተፈጥሮ ሀብቱ ነው፡፡ 

እስከ ቀበሌ ያለው መዋቅር አርሶ አደሩን ማስገንዘብ ይኖርበታል፡፡ ማሳ ላይ የሚለቀቀው እሳት የት ድረስ ተጉዞ ምን እንደሚያመጣ ማሰብም ያስፈልጋል፡፡

በሌላ በኩል ጥሩ የግጦሽ ሳር ፍለጋ በሚለኮስ እሳት የሚወድመውን የአርብቶ አደሩ ወሰንተኛ የተፈጥሮ ሀብትም ጉዳይ እንዲሁ ከወዲሁ መከታተል ያስፈልጋል፡፡

ሆን ተብሎ በተፈጥሮ ጠላቶች የሚለኮሱ እሳቶችን ደግሞ ክትትልና ቁጥጥሩ ለአንድ አካል ብቻ መተው የለበትም፡፡ እያንዳንዱ የጽጥታ መዋቅር በሚለኮስ እሳት ራሱ ጭምር ሊያጣ ስለሚችለው ጸጋና ሊገጥመው ስለሚችል መከራ ግንዛቤው እንዲኖረው ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

እንደ ሀገር በእሳት ቁጥጥር ስልት ብዙ እርቀት አልሄድንም፡፡ በተለኮሰ ቁጥር ሂሊኮፕተር መከራየት የማትችል ሀገር አለችን፡፡ መፍትሔው እሳቱ እንዳይነድ ከነደደ እንዳይበዛ ከበዛ ከቁጥጥር ውጪ እንዳይሆን ማድረግ ነው፡፡

እንዲህ ባለ በጋ እድሜ ጠገብ ዛፉን የማያወድም ቀላል እሳት ለተፈጥሮ ሀብቱ መልሶ መፋፋት መልካም ነበር፡፡ ግን ብዙ ቦታዎቻችን የእሳት መክሊያ ድንበር የላቸውም፡፡ አንዱ ጋ የተነሳው እሳት መቆሚያ ሳይኖረው የትም ይደርሳል፡፡ ያ ደግሞ ፈተና ነው፡፡ ያ ደግሞ ያስቸግራል፡፡

አሁን ዜናው እንዲህ ያለ ቦታ ተቃጠለ ሲል ሩቅ ይመስለናል፡፡ ኑሯችን ውስጥ የገባ እሳት ነው፡፡ ቤታችንን የሚበላ እሳት ነው፡፡ አንኮበር ወፍ ዋሻ ሩቅ አይደለም፡፡ የአዲስ አበቤው አየር ነው፡፡ አሰቦት ሩቅ አይደለም፡፡ 

የምዕራብ ሀረርጌ ውሃና አየር ነው፡፡ ጭላሎ ሩቅ አይደለም ከገብስ ምርታችን ጋር የተቆራኘ ጸጋ ነው፡፡ ስሜንም ሩቅ አይደለም ብዙ ትርጉም ያለው ኑሯችን ነው፡፡ የረርም እንዲሁ የመዲናዋ የንጹህ አየር ባንክ ነው፡፡

የተቃጠልነው እኛ ነን፡፡ የምናድነውም ራሳችን ነው፡፡ ከእሳት ስለማምለጥ ብቻ ሳይሆን ስላለመቃጠል እናስብ፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top