Connect with us
#ድሬደዋ
የፌ/መ/ት/ባ/ድሬዳዋ ቅርንጫፍ

ዜና

#ድሬደዋ

#ድሬደዋ

በድሬደዋ አስተዳደር የሳቢን ሰኢዶ ታክሲ መጫኛ ወደ ቄራ መዛወሩ ተገለፀ፡፡

የታክሲ አሽከርካሪዎች ከመጋቢት 17 ጀምሮ ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ሳቢያን የሚያደርጉት ጉዞ በማደያ አድርጎ በተዘጋጁ የውስጥ ለውስጥ  መንገዶች መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

አሁን ላይ ከከተማዋ መንገዶች የመያዝ አቅም በላይ የሆነውን የተሸከርካሪ ፍሰት ባሉት ውስን መንገዶች ባግባቡ ለማስተናገድ እንዲያስችል ታሳቢ በማድረግ አማራጭ የተሸከርካሪ መንገዶችን አገልግሎት ላይ ለመዋል እየሰራ እንዳለ በትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅረንጫፍ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

በጽ/ቤቱ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ም/ኮማንደርጉሉማ ታዬ እንደ ገለፁት

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከአስተዳደሩ ፓሊስ ኮሚሽን የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ከድሬደዋ አስተዳደር ከተማ ስራስኪያጅ ጋር በመቀናጀት  ከመጋቢት 17 2013 ጀምሮ ለሁሉም የታክሲ አገልግሎት ሰጭ ተሽከርካሪዎች ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ሳቢያን ሚያደርጉትን ጉዞ በማደያ አድርገው በኳስሜዳው በኩል በተዘረጋው ኮብል ብሄራዊ – ጉልት መዳረሻቸውን ቄራ እንዲያደርጉና መጫኛና ማውረጃ ስፍራውም እዛው እንደሆን መወሰኑን ተናግረዋል፡፡

ይህ በመሆኑም ማንኛውም የታክሲ አሽከርካሪ እንደቀድሞው በሰኢዶ አካባቢ መቆም የተከለከለ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

መመለሻቸው እንደቀድሞው ከቀድሞው ቄራ በዋናው መንገድ ይሆናል ብለዋል፡፡

ይህ ሲባል ቀደም ሲል በነበሩት ፌረማታዎች ህግና ምልክቱን ተከትሎ ሰዎችን መጫን እነደሚቻል ገልፀዋል፡፡ እንደሁም በውስጥ ለውስጥ መንገዶቹ ላይ ተሳፋሪው  በቀረበው ቦታ  መውረድ ይችላልም ብለዋል፡፡

ይህንን በምሳሌ ሲያስረዱም

አንድ አሽከርካሪ መነሻውን ከሼል ወደ ሳቢያን  ቢደርግ

ሼል-ዲፖ-ማደያ-በቡና ባንክ(ኳስ ሜዳ) -ብሄራዊ-ጉሊት መዳረሻው የቀድሞው ቄራ ይሆናል ማለት ነው

አሸዋ-መስቀለኛ-ኳስሜዳ-ብሄራዊ-ጉሊት መዳረሻው የቀድሞው ቄራ ይሆናል ማለት ነው።

ይህ ስምሪት በተለይ ሳቢን ሰኢዶ አካባቢ የሚታየውን መጨናነቅ በከፍተኛደረጃ እንደሚቀንስ ታምኖበት ወደ ስራ መገባቱን ምክትል ኮማንደር ጉልማ ተናግረዋል፡፡

ከሚያዚያ 17 ጀምሮም ከትራፊክ ዳይሬክቶሬቱ ጋር በመቀናጀት ህግ የማስከበር ስራው ተጠናክሮ እንደሚሰጥም ተናግረዋል፡፡

ለዚህ ይረዳ ዘንድ የትራፊክ ምልክቶችን በአዲሱ ተለዋጭ መንገድ ላይ የመትከል ተግባር ተከናውኗል ነው ያሉት፡፡

(ምንጭ ፦ የፌ/መ/ት/ባ/ድሬዳዋ ቅርንጫፍ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top