Connect with us

የባላገሩ ቴሌቭዥን መሥራች አብርሃም ወልዴ ሽልማት!!

የባላገሩ ቴሌቭዥን መሥራች አብርሃም ወልዴ ሽልማት!!
የቅዱስነታቸው ልዩ ጽ/ቤት

ዜና

የባላገሩ ቴሌቭዥን መሥራች አብርሃም ወልዴ ሽልማት!!

የባላገሩ ቴሌቭዥን መሥራች አብርሃም ወልዴ ሽልማት!!

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ/ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ  የሥራ ሓላፊዎች እና ሠራተኞች እንዲሁም አዲስ የተመረጡት የሀገር አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አገልጋዮች የሥራ ዕቅዳቸውን  ለቅዱስነታቸው በማቅረብ ለማስባረክ እና መመሪያ ለመቀበል በተያዘላቸው መርሐ ግብር ላይ የዕለቱ የክብር እንግዳ ለነበሩት የባላገሩ ቴሌቪዥን ድርጅት ባለቤት አቶ አብርሃም ወልዴ የመታሰቢያ ሽልማት ሰጡ።

ቅዱስነታቸው የባላገሩ ቴሌቪዥን ድርጅት ባለቤት አቶ አብርሃም ወልዴ በቤተ ክርስቲያን ልጅነታቸው ላበረከቱት ታሪክ የማይረሳው ውለታ ለእርሳቸውና ለድርጅቱ የመታሰቢያ ሽልማት በሰጡበት መርሐግብር ላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ  የቁርጥ ቀን ልጅ የሆኑት አቶ አብርሃም ወልዴን ስለ መልካም ሥራቸው በማመስገን ሰፋ ያለ ምክርና ቃለ ቡራኬ አስተላልፈዋል።

በመርሐ  ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤትና የውጭ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ሓለ ፊ የድሬዳዋ እና ጅቡቲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ክቡር መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኃይለ ገብርኤል ነጋሽ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጸሐፊ ተገኝተዋል ሲል የቅዱስነታቸው ልዩ ጽ/ቤት ዘግቧል ።

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top