Connect with us

የሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርሃግብር ቅዳሜ ዕለት ይከናወናል

የሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርሃግብር ቅዳሜ ዕለት ይከናወናል
ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

ነፃ ሃሳብ

የሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርሃግብር ቅዳሜ ዕለት ይከናወናል

የሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርሃግብር ቅዳሜ ዕለት ይከናወናል

ለሕዝብ እንደራሴ ምክር ቤት በግል ዕጩ ኾነው የቀረቡት መምህር፣ ደራሲ፣ የማህበረሰብ አንቂ የሆኑት ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የምርጫ ቅስቀሳ መርሀግብር ማስጀመሪያ ኘሮግራም ከነገ በስቲያ ቅዳሜ መጋቢት 18 ቀን 2013 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል እንደሚካሄድ ተሰማ፡፡

የሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የምርጫ ቅስቀሳ የሚዲያ ንዑስ ኮምቴ የተገኘ ዜና እንደሚያስረዳው ዲያቆን ዳንኤል የሚወዳደሩት በአዲስአበባ የካ ክፍለከተማ የምርጫ ክልል 28 እና ቦሌ ክፍለ ከተማ ምርጫ ክልል 10  ውስጥ ነው፡፡

በግል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዕጩነት የቀረቡት ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት  የምርጫ ምልክታቸው ፊደል “ሐ” ስትኾን፣ የምርጫ ቅስቀሳው መሪ ቃል፣ “ኢትዮጵያዊነት በርቱዓዊነት!!” የሚል እንደሆነም ታውቋል፡፡

ሙሐዘ ጥበበባት ዲያቆን ዳንኤል ቅዳሜ መጋቢት 18 ቀን 2013 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል በሚያካሂዱት የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርሃግብር ላይ ስለምርጫ ምልክታቸው፣ ስለመሪ ቃሉ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡም የደረሰን ዜና ጠቁሟል፡፡

በካር ጸሐፊው ዳንኤል ክብረት፣ ከስምንት በላይ የወግ መጻሕፍትን ለንባብ ያበቁ ደራሲ ናቸው። ከወግ ሥራዎቻቸው በተጨማሪም፣ በሃይማኖት እና በምርምር ላይ ያተኮሩ ከኻያ አምስት በላይ የኾኑ መጻሕፍት ደራሲ ናቸው፡፡ 

በቤተ ክርስቲያን የዐውደ ምሕረት ጉባኤ ላይ ብቻ ሳይወሰኑ በየመድረኩ፣ ለትውልዱ ይበጃሉ የሚሏቸውን ሐሳቦች ለማካፈል የማያመነቱ፣ በዚኽም በጎነታቸው መልካም ስምን የተጎናጸፉ ብርቱ የዐደባባይ ሰው መሆናቸው ይታወቃል፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top