Connect with us

ኘሬዚደንት ሳሀለወርቅ ዘውዴ፤ በኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣውን የጎጠኝነት እና ራስ ወዳድነት ችግር ዜጎች በአንድ ልብ ሊቃወሙት ይገባል አሉ

ኘሬዚደንት ሳሀለወርቅ ዘውዴ፤ በኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣውን የጎጠኝነት እና ራስ ወዳድነት ችግር ዜጎች በአንድ ልብ ሊቃወሙት ይገባል አሉ
Ethiopian Broadcasting Corporation

ዜና

ኘሬዚደንት ሳሀለወርቅ ዘውዴ፤ በኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣውን የጎጠኝነት እና ራስ ወዳድነት ችግር ዜጎች በአንድ ልብ ሊቃወሙት ይገባል አሉ

ኘሬዚደንት ሳሀለወርቅ ዘውዴ፤ በኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣውን የጎጠኝነት እና ራስ ወዳድነት ችግር ዜጎች በአንድ ልብ ሊቃወሙት ይገባል አሉ

በጎጠኝነት እና በራስ ወዳድነት ተተብትቦ እርስ በእርስ በመጋጨት ለዓለም መዘባበቻ መሆን ለኢትዮጵያ እና ለዜጎቿ የሚመጥን አይደለም ሲሉ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ። 

የአስተዳደር ወሰን እና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ከሰላም ሚንስቴር እና ከደህንነት ጥናት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ሀገር አቀፍ የጥናት እና ምርምር ሲምፖዚየም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በዚሁ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ሳህለወረቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ እየተጠናወተ የመጣውን የጎጠኝነት እና ራስ ወዳድነት ችግር ዜጎች በአንድ ልብ በመቃወም ከእንዲህ አይነቱ አባዜ መውጣት የግድ ይለናል ብለዋል። 

ኢትዮጵያ የብዝሀነት ሀገር ናት ያሉት ፕሬዝዳንቷ የዜጎች በሰፈሩበት መልክዐምድር ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር መብትም በህገ መንግስቱ ስለመደንገጉ ጠቅሰዋል።

ይሁንና ይህ መብት ሳይሸራረፍ በተግባር ሳይተገበር ቆይቶ ወቅታዊና ሳይንሳዊ ምላሽ ሳያገኝ ቀርቷልም ብለዋል። 

በዚህም የማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጉዳይ ለነጋሪ የሚያሳፍር ግጭት፣ አሰቃቂ ሞትና የንብረት መውደም እንዲሁም መፈናቀል ማስከተሉ የአደባባይ ሀቅ ነው ሲሉ ፕሬዚዳንቷ ገልፀዋል። 

ይህንን ችግር በዘላቂነት ለማስቀረትም መንግስት ከአስተዳደር ወሰንና ማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ሳይንሳዊ ምክረ ሀሳብን የሚያቀረብ ኮሚሽን አቋቁሞ ወደ ስራ አስገብቷል ነው ያሉት። 

ኮሚሽኑ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር በሚፈለገው ልክ እንዲከውንም በየደረጃው ያሉ የመንግስት አካላት ትብብር እንዲያደርጉ ፕሬዝዳንቷ በአፅንኦት አሳስበዋል።(EBC)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top