Connect with us

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመራጮች ምዝገባ ስልጠናዎችን ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመራጮች ምዝገባ ስልጠናዎችን ሰጠ
ምርጫ ቦርድ

ዜና

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመራጮች ምዝገባ ስልጠናዎችን ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመራጮች ምዝገባ ስልጠናዎችን ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሁለት ተከታታይ ቀናት ማለትም የካቲት 26 እና 27 ቀን 2013 ዓ.ም ለመራጮች ምዝገባ የአሠልጣኞች ሥልጠና መስጠቱ ይታወሳል። 

የአሠልጣኞች ሥልጠናው ለምርጫ ክልል ኃላፊዎች፣ ለዞን አስተባባሪዎች፣ ለምርጫ ጣቢያ ሠራተኞችና ለልዮ ምርጫ ጣቢያ ሠራተኞች እንዲሁም ለመሥክ አሠልጣኞች ለመስጠት የታቀደው ሥልጠና አካል የነበረ ሲሆን፤ ለመሥክ አሠልጣኞቹ ደግሞ መጋቢት 4 እና 5 ቀን 2013 ዓ.ም ሥልጠናው ተሰጥቷል።

የምርጫ የሕግ-ማዕቀፎች፣ የምርጫ ጣቢያ አደረጃጀት፣ የመራጮች ምዝገባ ፅንሰ ሃሳብና መሥፈርቶች፣ ለኮቪድ መከላከል ሊወሰዱ የሚገቡ ዕርምጃዎች፣ የሥርዓተ-ፆታና አካል ጉዳተኛ አካታችነት፣ የጊዜ ሠሌዳና የሥራ ሰዓት፣ የምርጫ ጣቢያ ኃላፊዎች ሥነ-ምግባር፣ የምርጫ አስተዳደርና ሚና፣ የእያንዳንዱ የምርጫ ጣቢያ የሥራ መደብ ኃላፊነቶች፣ የምርጫ ታዛቢዎችና ወኪሎች እንዲሁም የብዙኃን መገናኛ ኃላፊነትና ሚና፣ የመራጮች ምዝገባ ቁሳቁስ/የምዝገባ ኪት፣ ለመራጮች መረጃ ስለሚሰጥባቸው ፖስተሮች፣ ከመራጮች ምዝገባ ቀን በፊት ስለሚከናወኑ ተግባራት፣ የምዝገባ ሂደት ቅደም ተከተሎች፣ የምርጫ ጣቢያ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ስለሚቋቋምበት ሂደት፣ ለምርጫ ክልል ሪፖርት አቀራረብ፣ የመራጮች ምዝገባን ወደ ዲጂታል ስለመቀየርበት ሂደት፣ የመራጮች ምዝገባ ሂደት የደኅንነት ሕጎች፣ የምርጫ ቅሬታ አፈታቶች፣ ሎጀስቲክ፣ ኦፕሬሽንና አስተዳደራዊ የሆኑ ጉዳዮች ሥልጠናው ውስጥ ከተካተቱት አጀንዳዎች ውስጥ ይገኙበታል።

እንዲሁም የመጋቢት 11 እና 12 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ፣ በሐረር እና በድሬዳዋ የመራጮች ምዝገባ ላይ የሚሣተፉ የምርጫ ጣቢያ ምርጫ አስፈጻሚዎችን የሥልጠና ሂደት የተከናወነ ሲሆን በዚህ ሳምንትም ስልጠናዎቹ የሚቀጥሉ ይሆናል።(ምርጫ ቦርድ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top