ኦነግ ሸኔነትን የዳቦ ስም ላሉት የከሚሴው እንደራሴ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድንቅ መልስ መልሰዋል፤
ጠቅላዩ ኦነግ ሸኔን የአማራ ጠላት ነው አንበል የኦሮሞም ነው፡፡ ከሰፈራችን ውጪ እናስብ ብለዋል
******
(ስናፍቅሽ አዲስ – ድሬቲዩብ)
አንድ እንደራሴ በዚህ ደረጃ እንዲህ በህግ ጭምር የሚታገድ ጥላቻን መናገራቸውን አነጋግሮ ነበር፡፡ ፓርላማ ላይ የሚነሳ ሀሳብ ያልመሰለን ብዙ ነን፡፡ ምክር ቤቱ ለሻይ ተበትኖ እስኪመለስ እንዲህ ያሉት የፓርላማ ተወካይ ንግግር ያሳቀቀን ብዙ ነበርን፡፡
እርግጥ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሩ መልስ መልሰዋል፡፡ አንድ የፓርላማ አባል በተዘጋና ሆስፒታል አስከሬን ምክር ቤት ቁጭ ብዬ ሸተተኝ ላሉት ሰው መልስ ሰጥተዋል፡፡ የአማራ ክልል ምክር ቤት ግጭቱን ተንተርሶ በሰጠው መግለጫ የኦሮሞና የአማራ ብሔረሰብን ወዳጅነት አጠንክሮ እውቅና ሰጥቷል፡፡ ግጭቱን ሌላ አካል ለሌላ አላማ እያዋለው እዚህ እንዳደረሰውና ኢትዮጵያን ማፈረስ የሚፈልግ ቡድን ህዝብ መሃል እንደመሸገ ገልጾዋል፡፡
የህዝብ እንደ ራሴው ምክር ቤትን ሀሳብ የሰሙት ተከታይ ተናጋሪ በዚህ ደረጃ ከአንድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የማይጠበቅ ንግግር መናገራቸው ያስመሰግናቸዋል፡፡ ሀገርን ያክል በምክር ቤት አባልነት ከሚመራ አንድ ሰው የማይጠበቅ ንግግር እንደሆነ ሁላችንም አፍ ሲከፈት ነውና አይተናል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የወሎን አብሮነት ተናግረዋል፡፡ አካባቢያዊ ትስስሩን አስረድተዋል፡፡ እንዲህ ያሉ ንግግሮችና ጥላቻዎች ትርጉማቸው ምን እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ እኒያን ሌላ ሀሳብና መንፈስ ተናጋሪ የምክር ቤት አባል ክብር የሌለው ጥያቄ ስለማንሳታቸው ከጠቅላዩ የሰፈርተኝነት መንፈስ እንውጣ መልስ መረዳት ይቻላል፡፡
ኦነግ ሸኔ የዳቦ ስም ነው ብለው ጉያቸው የከተቱትን እንደራሴ ኦነግ ሸኔን ለምን የአማራ ጠላት እናደርገዋለን? ብለው እየጠየቁ ኦነግ ሸኔን መደበቁና መሸከሙ እንደማያዋጣ ይልቁንም ኦነግ ሸኔም ለኦሮሞም ቢሆን እንደማይበጅ ይልቁንም የጁንታው ቡችላ መሆኑን አስምረው አስረድተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አስረግጠው የተናገሩትና የመከሩት የሰፈርተኝነትን መንፈስ እናሸንፍና ይህቺ ሀገር የጋራችን ናት ያሉበት አስተሳሰብ የዕለቱ ትልቅ መልእክት ነው፡፡
ኢትዮጵያ የብዙ ህዝቦች ሀገር ናት፡፡ ትከሻቸውን በሚለካኩ ጥቂት የብሔር ልሂቃን ሳቢያ እንደ ሀገር እየታመሰች መኖር የለባትም፡፡ ይሄ የሰፈርተኛነት መንፈስ ነው፡፡
ከሰፈሩ ያልወጣ እንደራሴ ሀገሩ ላይ አለሁ ብሎ የልጅነት ጨዋታ ይጫወታል፡፡ እኔ እና እኛ የሚልበት መንፈስ በጥላቻ የሰከረ ነው፡፡ አሁንም በሰሜን ሸዋና በኦሮሞ ብሔረሰብ አካባቢ የተከሰቱት ግጭቶች አካባቢያዊና ህዝባዊ አይደሉም፡፡ መነሾ ይዘው ዓላማ አንግበው የመሸጉ ሰዎች ናቸው፡፡ እነኚህ ሰዎች ከትግራይ የተረፈውን የትህነግ ጉልበት መሃል ሀገር ድረስ ከትተው ሀገር ለማተራመስ የፈጠሩት እንደሆነ ከሁኔታው ያስታውቃል፡፡