Connect with us

የንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ማስጠንቀቂያ

የንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ማስጠንቀቂያ
ንግድና ኢንደስትሪ ሚ/ር

ዜና

የንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ማስጠንቀቂያ

የንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ማስጠንቀቂያ

የሲሚንቶ አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች ወደ ትክክለኛው የንግድ መስመር የማይገቡ ከሆነ መንግሥት ጣልቃ ገብቶ የዘርፉን ችግር ይፈታል ሲል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሲሚንቶ አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች የንግድ ሕጉ በሚፈቅደው አግባብ ሀገርንና ህዝብን የማገልገል ግዴታቸውን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የማይወጡ ከሆነ የህብረተሰቡን የኑሮ ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል መንግስት አዋጭ ያለውን እና የዘርፉን ችግር ሊፈታ የሚችል ውሳኔ የሚወስን መሆኑን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስጠነቀቀ፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት፣ ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከክልልና ከተማ አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊዎች፣ ከሲሚንቶ አምራቾች፣ አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች ጋር በሲሚንቶ ምርት አቅርቦትና ስርጭት ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡

አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎቹ በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ወደ ትክክለኛው የንግድ መስመር የማይገቡ ከሆነ መንግሥት ጣልቃ ገብቶ የኮንስትራክሽን ዘርፉ በሲሚንቶ እጥረት ምክንያት የተደቀነበትን ችግር በመፍታት ምርቱ በቀጥታ ለተጠቃሚው እንዲደርስ ለማድረግ እንደሚሰራ ውይይቱን የመሩት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ጠቁመዋል፡፡

መንግስት አጥንቶ ካልፈቀደ በስተቀር በሲሚንቶ ምርት የመሸጫ ዋጋ ላይ ምንም ዓይነት ጭማሪ ማድረግ በሕግ እንደሚያሥጠይቅ አቶ መላኩ ማስጠንቀቃቸውን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡(ንግድና ኢንደስትሪ ሚ/ር)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top