Connect with us

ጉዳቱ እንጂ ጥቅሙ ያልታወቀው የኮቪድ-19 የሙከራ ክትባት

ጉዳቱ እንጂ ጥቅሙ ያልታወቀው የኮቪድ-19 የሙከራ ክትባት
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ጉዳቱ እንጂ ጥቅሙ ያልታወቀው የኮቪድ-19 የሙከራ ክትባት

ጉዳቱ እንጂ ጥቅሙ ያልታወቀው የኮቪድ-19 የሙከራ ክትባት

አምኃየስ ታደሰ (amhayest@gmail.com)

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ የአስትራዜኔካ የኮቪድ-19 የሙከራ ክትባት በአገራችን ለቫይረሱ ተጋላጮች መሰጠት መጀመሩን ያበሰሩን በርካታ የአውሮፖ መንግስታት ለዜጐቻቸው እንዳይሰጥ በማገድ ላይ መሆናቸውን እያወቁ ነው፡፡ 

በአሁኑ ወቅት ከሞላ ጐደል ከሁሉም የአውሮፓ ሕብረት አባላት በተጨማሪ በአንዳንድ የኤስያ እና የደቡብ አሜሪካ አገራት ጭምር የሙከራ ክትባቱ ለሰው ልጅ እንዳይሰጥ እየተከለከለ ሲሆን የኮንጐ መንግስትም ውሣኔውን በመደገፍ ከአህጉራችን ቀዳሚነቱን ይዟል፡፡

አስትራዜኔካ የተባለው የእንግሊዝ እና የስዊድን ኩባንያ ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጥምረት ያዘጋጀውን ይኸው የሙከራ ክትባት በሁኔታዎች ላይ ተመስርቶ ኮቪድ-19ን ለመከላከል እንዲሰጥ የአውሮፓ ሜዲካል ኤጀንሲ ከፈቀደ ከሁለት ተኩል ወራት አይበልጥም፡፡ 

ነገር ግን ከአሕጉራዊ ሕብረቱ 27 አባል አገራት ከ20 የሚበልጡት ከስርጭት ሊያግዱት የወሰኑት የተከተቡ ሰዎች በደም መርጋት እና ኘላትሌት በተባሉት የቀይ የደም ሕዋሳት መጠን መዛባት የተነሳ ለከፋ የጤና ችግር መዳረጋቸው መታወቁን ተከትሎ ነው፡፡

በዴንማርክ የተጀመረውን ይኽንኑ እገዳ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያን፣ ስፔን፣ ስዊድን፣ ኖርዌይ፣ ኔዘርላንድስ፣ አየርላንድ፣ አይስላንድ፣ ቡልጋሪያ፣ ፖርቹጋል፣ ስሎቬንያ፣ ቆጵሮስ፣ ላቲቪያ፣ ኢስቶንያ፣ ሊቱንያ፣ ሉክሰምበርግ እና አውስትሪያ የተቀላቀሉት ከአንድ ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ መሆኑ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ያቀነቀነለት የሙከራ ክትባት ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን የሚያመላክት ይመስለኛል፡፡

በአንፃሩ የአሜሪካው የመድሃኒት አስተዳደር ወይም ኤፍዲኤ ጨርሶ ሊቀበለው ያልቻለው ይኸው የአስትራዜኒካ ክትባት አሁንም በሙከራ ሂደት ላይ ያለ እንጂ መደበኛውን ፈቃድ በአውሮፓ ጭምር አለማግኘቱን የሚገነዘቡት እነ ዶ/ር ሊያ ክትባቱ የሚሞከርባቸውን ወገኖቻችንን እንደ ሰብአዊ የጊኒ አሳማ ማድረጋቸው በዝምታ የማይታለፈው ያለ ምክንያት አይደለም፡፡

የትኛውም የኮቪድ-19 ክትባት በሰዎች ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት ያመረተው ፋርማሲያዊ ኩባንያም ሆነ ለተጠቃሚዎች እንዲታደል የተስማማው ተቆጣጣሪ አካል ተጠያቂ አይደሉም፡፡ በሌላ አነጋገር የክትባቱ እየተሰጠ የሚገኘው አሁንም የምርምሩ ተሳታፊ እንጂ የመድሃኒቱ ተጠቃሚ ተደርገው ለማይቆጠሩ ሰዎች ነው ማለት ነው፡፡  

የአስትራዜኔካ ክትባት ቀደም ሲል እስከ 45 በመቶ በሚደርሱት ፈቃደኛ እንግሊዛውያን ላይ ሲሞከር የተለያየ የጤና ችግር መከሰቱን ቢቢሲ ሲዘግብ በብራዚል እና ደቡብ አፍሪካ በተካሄደው ምርምር ደግሞ ከብግነት እና የድካም ስሜት፣ ራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽ እና የመገጣጠሚያ ሕመም አንስቶ እስከ የቆዳ ቁጣ የገጠማቸው እስከ አስር በመቶ የሚደርሱ ተሳታፊዎች በመሆናቸው የሙከራ ሂደቱ ተቋርጦ እንደነበር እዚህ ላይ ልብ ይሏል፡፡

ይልቁንም እውነት ኮቪድ-19 እንደሚባለው ወረርሽኝ ሆኖ ቢገኝ እንኳን ክትባቱ መፍትሄ ሊሆን የማይችለው ዛሬም ቢሆን ጉዳቱን እንጂ ጥቅሙን አስረግጦ የሚያውቅ ባለመኖሩ የተነሳ ነው፡፡  ለአብነትም ፈቃድ የሰጠው የአውሮፖ ሜዲካል ኤጀንሲ ድረ-ገጽ በማያሻማ ቋንቋ እንደሚገልጸው የአስትራዜኔካን “ክትባት የወሰዱ ሰዎች ምን ያህል በቫይረሱ መያዝ መቻላቸውም ሆነ ወደ ሌሎች ማስተላለፋቸው አይታወቅም፡፡” (It is not yet known how much vaccinated people may still be able to carry and spread the virus.)

በአሁኑ ወቅት 2.2 ሚሊዮን ያህል ወገኖቻችን እንዲቋደሱ የተፈረደባቸው የአስትራዜኔካ የሙከራ ክትባት ከመነሻው በተለይ ከ65 ዓመት በላይ ለሆኑ አረጋውያን ዜጐቻቸው እንዳይሰጥ ሲሞግቱ በነበሩት ጀርመን፣ ፈረንሳይ እና ጣሊያን ተከማችቶ በመቆየቱ የአገልግሎት ጊዜው ለማብቃት በመቃረቡ እንጂ ኮቪድ-19 በአገራችን የጤና ችግር ሆኖ በመገኘቱ እንዳልሆነ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተሻለ ዋቢ የለም፡፡

በርግጥም እስከ ዛሬ ድረስ በምርመራ የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው የተባለው ከ180 ሺ በታች ወይም 0.15 በመቶ ያኽሉ ወገኖቻችን ቢሆኑም በኮቫክስ መርኃ-ግብር አማካይነት ከሕንድና ባንግላዴሽ ቀጥሎ ከፍተኛ የተባለው 8,928,000 የሙከራ ክትባት የተመደበው ለኢትዮጵያ መሆኑን ጋቪ የተባለው ጥምረት ዓለም-አቀፍ ድልድል ማመልከቱ የአገራችንን ዜጐች የመርዛማ ፋርማሲዩቲካል ንጥረ-ነገሮች የገበያ ስፍራ ለማድረግ ያለመ ብቻ አይደለም፡፡

በኮቪድ-19 የመሞት ስጋት በመብረቅ ከመገደል ያልበለጠ ስጋት ለማይፈጥርበት ማንኛውም ሰው የትኛውንም የሙከራ ክትባት ከመታደም የመብረቅ መከላከያ ይዞ ራሱን እንደመጠበቅ የሚቆጠር ነው፡፡  በበኩሌ ክትባቱን ከመውሰድ ሞቴን ጨምሮ የሚመጣውን መቀበልን እመርጣለሁ፡፡

በነገራችን ላይ በማስረጃ ማስደገፍ በምችለው በዚህ ጽሁፌ የደረስኩበትን ማሳወቅ እንጂ ማንንም የማሳሳት ዓላማ የለኝም፡፡ ናታን ፍሬዘር አሉ ከሚላቸው ሁለት አይነት ሰዎች መካከል መንግስት የሚያስብላቸው ለሚመስላቸው ሳይሆን ራሳቸው ለሚያስቡት ያዘጋጀሁትን አጭር ዘገባ የምደመድመው ከመከተብ መገንዘብ ይቅደም እያልኩ ነው፡፡

(ማስታወሻ፡- ይህ መጣጥፍ የጸሐፊውን እንጂ የድሬቲዩብን ኤዲቶሪያል አቋም አያሳይም፡፡ በጉዳዩ ላይ በድጋፍም ሆነ በተቃውሞ የተጨበጠ ሀሳብ ያላችሁ ወገኖች በኢሜይል አድራሻችን (admin@diretube.com) ጹሑፎቹን ብታደርሱን ለማስተናገድ ዝግጁ ነን፡፡)

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top