“ኢትዮጵያ በዲጂታል ወታደሮቿ 80 በመቶ ተሳክቶላታል”
– ግብፃዊ ምሁር አንተር አል-አዛብ
በእስሌማ አባይ
“ግብፃዊያን ተኝተናል ወይም የማይረባ ብሽሽቅ ውስጥ ተዘፍቀን የኢትዮጵያ የድረ ገፅ ወታደሮች ስኬት እያስቆጠሩብን ይገኛሉ” ብለዋል ግብፃዊው አንተር ኤል-አዛብ። ከፕሩድ እና አሌክሳንደሪያ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሩት ግብፃዊ ምሁር የአገራቸውን ዜጎች ለመቀስቀስ ተከታዩን ጦማር ለበርካቶች ተደራሽ አድርገዋል።
“ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቡን የመጀመሪያ ሙሌት ዕውን ለማድረግ መናገርና ማሳወቅ የሚችሉ ዜጎቿን ሁሉ መልምላ እንደ ወታደር አሰልፋብናለች። ዜጎቹም የተነገራቸውን ነገር መዝግበው የያዙ ያህል አንድ ባንድ ተመሳሳይ መረጃዎችን ደጋግመው ያስተጋባሉ፡፡
ይህ የሚዲያ ሰራዊት ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የመስኖ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች ጋር የተገናኘ ነው። መሪያቸው ደግሞ ሚስተር አባ ጊሳ የሚባሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመገናኛ ብዙሃን አማካሪ ናቸው” ብለዋል ግብፃዊው (NB: የአቶ ሱልጣን አባ ጊሳ ሃላፊነት የውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ ልዩ ረዳት ነው)
በተጨማሪም በመካከላቸው የሚገኙት የአረብኛ ተናጋሪ ዜጎችን አሰማርተው በአልጀዚራ ቴሌቪዥን እየቀረቡ መልእክታቸውን ለሁሉም አረብ ህዝብና ማህበረሰብ በየቀኑ ተደራሽ ሲያደርጉ ሁለት ዓመት አለፋቸው።
የዚህ ዲጂታል ሰራዊት ዓላማ በማህበራዊ አውታረመረቦች አረብኛ ተናጋሪዎች አእምሮ ውስጥ ስለ ዓባይ ያሉ እውነታዎችን በተመለከተ ግራ መጋባት መፍጠር እና ሱዳንና ግብፅን ለማነጣጠል ነው።
ሌላው ጉዳይ ደግሞ ግብፅ በኢትዮጵያ የቅኝ ገዥ እና የበዝባዥነት እንዲሁም የሴረኝነት ሚና እንዳላት ለማሳየት ነው፡፡
ኢትዮጵያውያኑ ከ 80 % በላይ ተሳክቶላቸዋል። ግብፃውያን (አማተሮች) ግን በማህበራዊ አውታረመረቦች በነበራቸው ሚና 90 % ቃላታቸው (ሀሰተኛና ትኩረትን የሚከፋፍሉ ሰዎች ቢሆኑም) ማንንም በማይሰድቡ ኢትዮጵያውያን ላይ የዘፈቀደ ስድብ መንዛት ነበር ስራ አድርገው የቀጠሉት ፡፡
የተቀረው ግብፃዊ ሚና ደግሞ ከሱዳኖች ጋር በማኅበራዊ አውታረ መረቦች ስድቦችን መለዋወጥ ያሳልፍ ነበር። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ ከግብፅና ሱዳን ጋር የገባችበትን ውጥረት ለማሸነፍ የጠቀማት ወሳኝ አጋጣሚ ነበር የሆነላት፡፡
በግብፅ ላይ በሚደረገው የሚዲያ ዘመቻ በኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶችና ፀኃፍት የሚተገበር ሲሆን በተለይም ሦስቱ ሙስሊምና አረብኛ ተናጋሪዎች ኢትዮጵያዊ ናቸው እንጂ የውጭ ቋንቋ እና አረብኛ ብቻ ተናጋሪ ናቸው ፡፡ አረብኛውም የሳውዲ ዘዬኛ ያለው ነው።
ሌላው በአሜሪካ የሚገኝ ሲሆን የንግግር ፕሮግራሙ “የአባይ ነገስታት” ይባላል፡፡
ሦስተኛው በስዊድን ውስጥ የኖረ ሲሆን “የኢትዮጵያ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ኢንስቲትዩት” የተባለ ተቋም አቋቁሞ ተግባሩ የኢትዮጵያን የናይል ውሃ ተናጠላዊ መብቷን መጠበቅና ግብፅን በመገናኛ ብዙሃን እየቀረበ የማጥቃት ዘመቻ ላይ ተሰማርቶ የሚገኝ ነው፡..”
አንተር አል-አዛብ ማን ናቸው ??
Professor of Materials Engineering, Professor of Nuclear Engineering (by Courtesy), Director, Materials Theory Group, Editor-in-Chief, Materials Theory (Springer-Nature) university of California, los angels