Connect with us

ኢትዮጵያ አየርላንድን ወቀሰች

ኢትዮጵያ አየርላንድን ወቀሰች
(አዲስ ሚድያ ኔትወርክ (ኤ ኤም ኤን) )

ዜና

ኢትዮጵያ አየርላንድን ወቀሰች

ኢትዮጵያ አየርላንድን ወቀሰች

አየርላንድ በኢትዮጵያ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በውል ሳትረዳ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት እያደረገች ያለው እንቅስቃሴ የሁለቱ ሀገራትን ጥብቅ ትስስር የሚያጠለሽ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ::

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል::

በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ ወደ ነበረበት ለመመለስ በመንግስትና ጊዜያዊ አስተዳደር እየተደረገ ያለውን ርብርብ 40 ለሚደርሱ የሀገራት አምባሳደሮች መቐለ እንዲሄዱ መደረጉን አስታውሰዋል::

ሂደቱን በሚመለከት አምባሳደሮቹ የነበረባቸውን ብዥታ እንዲያጠሩ አድርጓል ያሉት አምባሳደር ዲና ጥቂት የሚባሉ ምዕራባዊያን ሀገራትና ተቋማት ተቀባይነት የሌለው እንቅስቅሴ እያደረጉ ነው ብለዋል::

አየርላንድን ምሳሌ ያደረጉት ቃል አቀባዩ በተመድ የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት የምታደርገው ግፊት ነባራዊ ሁኔታውን በውል ያልተረዳና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ጥብቅ ግንኙነት የሚያሻክር ነው ብለውታል::

አየርላንድ እያደረገች በሚገኘው ጫና ሳቢያ ኢትዮጵያን በስፍራው የሚገኘው አምባሳደር ለምክክር መጥራቷን ገልፀዋል::

ሂደቱ አየርላንድን ያነቃል ብለን እናስባለን ያሉት አምባሳደር ዲና በፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት እያደረገች የምትገኘው እንቅስቃሴ ግን ኢትዮጵያን አስከፍቷል ብለዋል::(አዲስ ሚድያ ኔትወርክ (ኤ ኤም ኤን) )

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top