Connect with us

የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠ/ሚኒስትር ዐብይን ሸለመ

የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠ/ሚኒስትር ዐብይን ሸለመ
EOTC TV

ዜና

የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠ/ሚኒስትር ዐብይን ሸለመ

የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠ/ሚኒስትር ዐብይን ሸለመ

፲ኛ ዓመት ምስረታውን እያከበረ የሚገኘው

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ሽልማት አበረከተ፡፡

የኢትዮጵያ  የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ከመጡ ጀምሮ ለእምነት ተቋማት ላደረጉት አስተዋፅኦ፣ በጉባዔው ‹‹ትልቅ›› የተባለውን ሽልማት አበርክቶላቸዋል።

ጉባዔው ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሸለማቸው፣ በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን  ውስጥ ተፈጥሮ የነበረውን ክፍፍል በውይይት እንዲፈታ ላደረጉት ጥረት፣ በእስልምና እምነት አማኞች ሲጠይቁ የነበሩ ታላላቅ ጥያቄዎችን እንዲመለሱ  በማድረጋቸውና በፕሮቴስታንት ወንጌላውያን አማኞች መካከል ከተናጥል ጉዞ ይልቅ በጋራ በመሰባሰብ እንዲሠሩ ላደረጉት አስተዋፅኦ  እንደሆነ ተገልጿል።

የምሥረታ አሥረኛ ዓመቱን እያከበረ ያለው ጉባዔው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያበረከተው፣  ከሽልማቶች ሁሉ ‹‹ልዩ ነው›› ያለውን  ‹‹መጽሐፍ ቅዱስ›› እና ‹‹ቅዱስ ቁርዓን›› ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በተገኙበት አበርክቶላቸዋል።

© EOTC TV

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top