Connect with us

በመላው ዓለም ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ጦርነትን ደግፋችሁ ሳይሆን የህወሃትን የሀሰት ዘመቻ ተቃውማችሁ ከእናት ሀገራችሁ ጎን ስለቆማችሁ እናመሰግናለን

በመላው ዓለም ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ጦርነትን ደግፋችሁ ሳይሆን የህወሃትን የሀሰት ዘመቻ ተቃውማችሁ ከእናት ሀገራችሁ ጎን ስለቆማችሁ እናመሰግናለን

ነፃ ሃሳብ

በመላው ዓለም ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ጦርነትን ደግፋችሁ ሳይሆን የህወሃትን የሀሰት ዘመቻ ተቃውማችሁ ከእናት ሀገራችሁ ጎን ስለቆማችሁ እናመሰግናለን

በመላው ዓለም ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ጦርነትን ደግፋችሁ ሳይሆን የህወሃትን የሀሰት ዘመቻ ተቃውማችሁ ከእናት ሀገራችሁ ጎን ስለቆማችሁ እናመሰግናለን

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)

በመላው ዓለም ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን እናመሰግናለን፡፡ እናንተ ከሀገራችሁ ጎን ቆማችኋል፡፡ እናንተ ጦርነትን ደግፋችሁ ሳይሆን ሀገር ማፍረስ የፈለገን የማፍያ ቡድን ተቃውማችሁ የዓለም ከተሞችን አጥለቅልቃችኋል፡፡ እናንተ እንደ ታወሩት ወገኖቻችሁ ቂምና ይዛችሁ አደባባይ ባለመውጣታችሁ ኮርተንባችኋል፡፡ 

ህግ የማስከበሩ ዘመቻ ሲጀመር እንደ ህወሃት መሪዎች ክፋት ከየጉሬው ሲለቀሙ የደስታ ሰልፍ ያስፈልገው ነበር እንዲህ ያለ አዙሪት ነውር በመሆኑ ዝምታን መርጣችኋል፡፡ ሌላው ቢቀር የሀገር ክንድ መከላከያ ሠራዊቱ በተኛበት በወገኑ ሲታረድ ጎዳና መውጣት ያስፈልግ ነበር ሆኖም ግን አላደረጋችሁትም፡፡

እነሱ ግን ለምን ዘርፈን አልከበርንም ብለው አኮረፉ፤ ስለሚረግፈውና ሰላም ስለሚያጣው ወገናቸው ውጪው ዓለም ሆነው ማሰብ አቃታቸው፤ ብዙው የህወሃት ደጋፊ ዲያስፖራ ወደ ውጪው ዓለም የሄደው በስልጣን ብልግና ነው፡፡ ያለ ፍትሕ ኢንባሲውን ተጠቅጥቀውበት ኖረዋል፡፡ በኤርትራውያን ስደተኞች ስም ሀሰተኛ ሰነድ አዘጋጅተው ተግዘዋል፡፡ መሬቱን ገንዘቡን ስልጣኑን ተቀራምተው እናት ሀገራቸውን እራቁቷን አስቀርተዋል፡፡ ይሄ ለምን ቀረ ብለው አሁን ዓለም አደባባይ እየወደቁ ሲንከባለሉ አይተናል፡፡

ደብረ ጽዮን ወደ ኢሳያስ የተኮሰው ሮኬት አያሳስባቸውም ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በአጸፋው የትግራይን ከተሞች በአየር ደብድበው የደም መሬት ቢያደርጉት ምንም አይቀርባቸው ለህወሃት ደጋፊ ትግራዋይ ከድፍን ትግራዋይ አንድ በርገር ይበልጥበታል፡፡ 

በተቃራኒው ግን የዶክተር ደብረ ጽዮን ጫካ ለጫካ መንከራተትና የህወሃት መሪዎች ውርደት ያበግናቸዋል፡፡

የሀሰት ዘመቻው የዚህ ውጤት ነው፡፡ ወገናቸውን ቢወዱ ኖሮማ ማረሚያ ቤት ፈትቶ መቀሌን ያዘረፈውን ህወሃት ደግፈው ዛሬም የካቲት 11 እየናፈቁ ከዳቦ ይልቅ ለጥይት መግዣ አያዋጡም ነበር፡፡

የሀሰት ዘመቻውን አይታችሁ አደባባይ በመውጣት የህወሃት ደጋፊ የጁንታው ቅጥረኞችን ነውርና ትንሽነት ለዓለም ህዝብ ስላሳያችሁ፣ ድራማቸውን ስላጋለጣችሁ ልትኮሩ ይገባል፡፡ ህዝባዊ ማዕበሉ ኢትዮጵያ ስትነካ የማይችል ትውልድ እልፍ መሆኑን አሳይታችኋል፡፡ በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ጉርብትና ኮንትሮባንድ ካልነገድን የሚሉ አጭበርባሪዎች ስላኮረፉ እንደማይበላሽ መልስ ሰጥታችኋል፡፡

በትግራይ ያለው ሁኔታ ወደ ሰላም እንዲመለስ የማይፈልግ የለም፤ ትግራዋይ እንዲራብ ፍላጎት ያለው አሉላ እንጂ ታማኝ አይደለም፡፡ ዛሬ አሉላ የሰበሰበውን ገንዘብ የት እንዳደረገው አላወቅንም፤ ታማኝ ሀገሩን ቤቱንና ኑሮውን ጥሎ መጥቶ ገንዘብ ሰብስቦ ሰብዓዊነት ብሎ ትግራይ እንዲደርስ በቀይ መስቀል ልኳል፡፡

አሁንም የኩርፊያ ጫጫታ የትም አያደርስም፡፡ ሌቦች የሚሰረቀው ሰው ነቃ ብለው የፈጠሩትን ግርግር በማያውቁ የሚያደምቁ እየሆነ ያለውን ነገር ደጋግመው ሊያጤኑት ይገባል፡፡ የጋራ ሀገር የሚኖረን የጋራ ዕይታ ሲኖረን ነው፡፡ 

ገዳይ ሌባና ሀገር አፍራሽ ለየትኛውም ወገን አይጠቅምም ከየትኛውም ወገን አይደለም፡፡ ትግራይን መልሶ ለማዳንና ለማልማት በጋራ ለሰላምና ለእርዳታ መረባረብ እንጂ ኢትዮጵያን ለማፍረስ መዶለቱ ቅዠት ቢሆንም ልክ አይደለም፡፡ መላው ኢትዮጵያ በመላው ዓለም ያደረገው ሰልፍ መልእክቱ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያውያን አሉላት ነው፡፡ እናም ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እናመሰግናለን፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top