እኛ ለኢትዮጵያ ብለን ግራችንን ሲመቱን ቀኛችንን ሰጠን፤ ጁንታዎች ግን ለምን ተቆጣችሁ ብለው ዓለም አደባባይ ወጡ፡፡አደባባይ ወጥቶ ማድመቁንማ እድሜ ለእናንተ እኛም እናውቅበታለን፤
(ስናፍቅሽ አዲስ – ድሬቲዩብ)
የዓለም ፊት እንኳን ሀሰት ይዘው እውነት አንግበውም ይጋረፋል፡፡ ከትግል ዘመናቸው እስከ ማይካድራ በኢትዮጵያውያን ደም ሲጨማለቁ ለኢትዮጵያዊነት ነበር ሁሉ የታለፈው፡፡ አሰቃቂ ነገር በመፈጸም በዓለም ታሪክ ጁንታው ላይ የሚደርስ ተፈጥሮ አያውቅም፡፡ እግረኛ ወታደር በታንክ ረፍርፎ የታመንን ሠራዊት አርዶ እኛ ዓለም ፊት የራሳችንን ነውር ለማውገዝ አልወጣንም ነበር፡፡
ንጹሃንን በመጨፍጨፍ ከጥንት እስከ ዛሬ ባለታሪክ የሆነውን ህወሃት ለማዋረድ የአለም አደባባዮች ያላደረግንው ምናልባትም የአንድ ሀገር ገመና በሚል ነበር፡፡ ሰሞኑን በተቃራኒው ተበዳይ መስለው ኢትዮጵያን በዓለም ፊት ለማሳጣት ጎዳና ወጡ፡፡
እውነት እንነጋገር ከተባለ ለተፈናቀለው ወገናችን ላሉት መች ደረሱ? ገንዘብ አዋጥተው ዳቦ መግዛትን መች ደፈሩት? ዛሬም አዲስ አበባና አራት ኪሎን ተቆጣጥሮ ለመዝረፍ ዳግም ትጥቅ ስለማንገብ ሲዘምሩ ሰምተናል፡፡
የትግራይ ልዩ ሃይል ያወደማትና የዘረፋት ትግራይ ከማን የተሰወረች ናት? እኛ እኮ ግራችንን ሲመቱን ቀኛችንን ሰጥተን ነበር፡፡ እንደ ሀገር ለመቀጠል በእነሱ ምክንያትና ምኞት ብዙሃኑና እውነተኛውን የትግራይ ህዝብ ላለማጣት የተከፈለ መስዋዕትነት ነው፡፡ ያንን መስዋዕትነት አራከሱት፡፡ ጥቂት ሆነው በአውሮፓ ጎዳና ላይ ሌባን ለማሳደድ እና ህግ ለማስከበር የተደረገን ዘመቻ እንደ ቅኝ ግዛት ሊያብጠለጥሉት ሞከሩ፡፡
ትናንት ሀውዜን ገበያ ተሸሽገው፣ ገብተናል የሚል መረጃ ለደርግ ሰጥተው፤ የሠራዊት ቁጥርና የቀለብ ድጋፍ ለማግኘት ያንን ንጹህ ህዝብ በአየር ያስደበደቡ ቲያትረኞች ወደ አስመራ ሮኬት ሲተኩሱ ሊሆን የሚችለው ጠፍቷቸው አይደለም፡፡ ቁርሳቸውን ከሚዘሉ ድፍን ትግራይ ዶግ አመድ ብትሆን ስለሚመርጡ ነው፡፡
እኛ ላይ ካደረጉት ነገር አንጻር ወያኔዎች የሆነባቸው የቁጣ ያህል ተራ ነገር ነበር፡፡ የማይመቱት ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል ነውና ብሂሉ ያንን የመሰለ ህዝብ ለስደት ለስቃይ ለረሃብና ለችግር አጋልጠውት እነሱ በአውሮጳ ጎዳና በርገር በልተው አደባባይ መንደባለልን እንደ ትግል ቆጠሩት፡፡
ሰሞኑን በሰልፍ እውነታውን ለመቀየር ሲሞክሩ ታዝበናል፡፡ አደባባይ ወጥተው የለመደባቸውን ሀሰት ለዓለም በመንገር ለማሳመን ሲሞክሩ ተገርመናል፡፡ ግን አደባባዩን እንደ እኛ አያውቁትም፡፡ እድሜ ለእነሱ በደላቸው ጽዋው ሞልቶ ሲፈስ እኮ እኛ ዓለም አደባባይ ስንጮህ ነበር፡፡ አደባባይ መውጣቱንማ እናውቅበታል፡፡
እውነት ይዞ መሟገቱም እድሜ ለወያኔ ችለነው ኖረናል፡፡ የትናንትና የትናንት ወዲያ ሰልፎች ይሄንን ዳግም አሳይተዋል፡፡ ዓለምን ያጨናነቁ የኢትዮጵያውያን ሰልፎች ገና ይቀጥላሉ፡፡ ዓለም ስለ ወያኔ ሸር ተንኮልና የቀጠናው መርዝነት የሚረዳበትን መንገድ እራሳቸው ደጋፊዎቹ ጀምረውታል፡፡ ያንን እንዴት ያለ እውነት እጃችንን ላይ እንዳለ እያሳየን እንቀጥላለን፡፡ ኢትዮጵያና ጠላቶቿ ይወድማሉ፤ ትግራይ ኢትዮጵያ እንደሆነችና ዳግም የወያኔ ቅጥረኞች ታሪክ ሆኖ ነውራቸው ይማሩታል፡፡ እኛ አንድ ህዝብ ነን በሆዳም ቅዠት የሚነጠል ማንነት የለንም፡፡ እውነት ያሸንፋል፡፡