Connect with us

“የተፈፀመው ግፍ የሚወገዝ ነው” የኦሮሚያ ፖሊስ

"የተፈፀመው ግፍ የሚወገዝ ነው" የኦሮሚያ ፖሊስ
OBN

ዜና

“የተፈፀመው ግፍ የሚወገዝ ነው” የኦሮሚያ ፖሊስ

“የተፈፀመው ግፍ የሚወገዝ ነው” የኦሮሚያ ፖሊስ

በጸረ ሠላም ሐይሎች ሴራና ተንኮል የሕዝቦች አንድነትና ወንድማማችነት የማይደናቀፍ መሆኑን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ። 

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነርና ዕጩ ዶ/ር ጌታቸዉ ኢታና ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ሰሞኑን በምዕራብ ጉጂና በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ በታጣቂዎች የተፈጸመዉ የግድያ ተግባር ፍጹም የሚወገዝ ነዉ ብዋል። 

ጥቃቱን የፈጸሙት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መሆናቸዉን የተናገሩት ምክትል ኮሚሽነሩ ጥቃቱ የተፈጸመዉ በእርቀ ሰላም ስብሰባ ላይ በነበሩ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ላይ መሆኑንም ገልጸዋል።

 በጥቃቱ እስካሁን ድረስ በዘጠኝ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንና ከነዚህም መካከል የሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የተናገሩት ምክትል ኮሚሽነሩ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ በጽኑ መጎዳታቸዉንና ሕክምና እየተደረገላቸዉ እንደሚገኝም ተናግረዋል። 

የግድያ ወንጀሉን የፈጸሙት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ዋና አላማ በኦሮሞና በአማሮ ሕዝቦች መካከል ያለዉን ወንድማማችነትና አንድነት ለማደናቀፍ ነዉ ያሉት ረዳት ኮሚሽነሩ የሁለቱ ወንድማማች ክልሎች አንድነትም በነዚህ ጸረ ሠላም ሐይሎች ሴራና ተንኮል አይደናቀፍም ብለዋል። 

የሁለቱ ክልሎች የጸጥታ አካላትና ነዋሪዎችም የግድያ ወንጀሉን የፈጸሙትን ታጣቂዎች ለመያዝና ለሕግ ለማቅረብ በጋራ እየሠሩ መሆናቸዉን ተናግረዋል። 

ጸረ ሠላም ሐይሎች የዘንድሮዉን ሐገራዊ ምርጫ ከማደናቀፍ ወደ ኋላ እንደማይመለሱ የተናገሩት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሕብረተሰቡ የነዚህን ጸረ ሰላም ሐይሎች ሴራና ተንኮል ሊያወግዝና ተጠርጣሪዎችን ከፖሊስና ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ለሕግ ሊያቀርብ እንደሚገባም ተናግረዋል። (OBN)

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top