Connect with us

ጦርነትን ለመከላከል፤ለጦርነት መዘጋጀት…

ጦርነትን ለመከላከል፤ለጦርነት መዘጋጀት…
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ጦርነትን ለመከላከል፤ለጦርነት መዘጋጀት…

ጦርነትን ለመከላከል፤ለጦርነት መዘጋጀት…

 (እስክንድር ከበደ)

በቅርቡ “ብቸኛዋ ሴት አየርወለድ” በሚል ሰይፉ ፋንታሁን አቅርቦ ነበር። አርቲስቶች ፊልም ለማስተዋወቅ የሚወጡበት መድረክ ላይ አየርወለዷን ስመለከት ገርሞኝ ነበር። ለምን ቀረበች ብዬ ሳስብ ወጣቶችን ወደ ውትድርና አለም ለመሳብ ይሆናል ብዬ ገመትኩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ 10ሺ ወጣቶችን   የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ምረቃ ላይ ንግግር አድርገው ነበር። ሀገራችን በአድዋና በካራማራ የተገኙ ድሎች ለማስጠበቅና የሀገሪቱን እድገት ለማስቀጠል ወጣቶች  የውትድርና አገልግሎት በፍቃደኝነት መሳተፍ እንዳለባቸው ጠቁመዋል። በተደጋጋሚ እንደሚናገሩት ወጣቱ ወደ ውትድርና ለመግባት ፍቃደኝነቱ አናሳ እንደሆነ ሲናገሩ ሰምቻለሁ። እኔ ከዚህ እለያለሁ። 

ባለፉት 30 አመታት ወጣቶች የሀገር መከላከያ ኃይል እንዲቀላቀሉ በየጊዜው ቅጥር ባልወጣበት ሁኔታ ወጣቱን መውቀስ አይቻልም። የመከላከያ ኃይል አባል ሆኖ ለሀገር መስራት መብትም ግዴታም ቢሆን ከመስፈርቱ ጀምሮ እና ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የተመጣጠነ የወጣቶች ስብጥር እንዲኖር ሚኒስቴሩ ምን ሰርቷል?

ለአብነት በሚሊዮኖች የሚሆኑ  ብቁ ወጣት ሴቶች እያሉ ውትድርና ሙያና የላቀ ክብር መሆኑን በሚያነቃቃ  መልኩ  ‘ኢሊት ፎርስ”,ለመገንባት አልተሞከረም ። ወጣቱ በልዪ ኃይል በብዛት የሚሳተፍበት ሁኔታ ከተመለከትን የመልማዮቹ ችግር እንጂ ወጣቱ ለውትድርና በተለይ ከፍ ያለ “ወታደራዊ ኤሊት ሰራዊት “በሚያፈራ መልኩ ከተቃኘ በርካታ ፍቃደኞች ማግኘት አይቸግረውም።

ቀዳማዊ ኃይለስላሴ የሐረር ጦር አካዳሚ በ1950 ሲመሰርቱ እድሜያቸው 17 እስከ 19 የሆኑ ወጣቶችን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሳምነው እንዲገቡ አደረጉደ ሲመረቁ ከጓደኞቻቸው የማያንስ ደሞዝ እንደሚያገኙ ነገረው አስገቧቸው። በሚቀጥለው ዙር ከሀገሪቱ 65 ሁለተኛ ደረጃ ጎበዝ ተማሪዎች መልምለው የቀለም ትምህርትና ውትድርና ሙያ አሰልጥነው ነበር። 

ደርግ ወደ ስልጣን ሲመጣ  የሐረር ጦር ትምህርት ቤትን የመጨረሻ ዙር አስመርቆ አካዳሚውን ሆን ብሎ ረሳው።

የሱማሊያ ወረራ በለብ ለብለብ 300ሺ ሚኒሻ አሰልጥኖ ፣ በኩባና ደቡብ የመን እገዛ ጭምር ተወጣው።

ፈረንጆቹ “ጦርነትን ለማስቀረት ለጦርነት መዘጋጀት”” እንደሚሉት ኢትዮጵያም  አዲሱን ጦርነት ለማስቀረት፤ አዲስ ወታደራዊ ኃይል መገንባት ያስፈልጋታል።  የሀገሪቱን ያህል የሰፋ መከላከያ በወጣቶቿ መገንባት ይኖርባታል፡፡ 

ህዳሴን የሚህል ግዙፍ ፕሮጀክትና ታላላቅ የልማት አውታሮቿን ከጠላት ግልጽና ሰውር ሴራ ጥቃት እንዲሁም የጥቃት ሙከራዎች መከላከልና  መመከት የሚችል  የዘመነ ሰራዊት መገንባት ለነገ የማይባል ስራዋ መሆን አለበት፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top