Connect with us

ደንቢያ በታች ወርዶ የለመደው መንግሥት፤ጎርጎራ መልማት አለበት ብሎ ማመን ብቻውን ያስመሰግናል፡፡

ደንቢያ በታች ወርዶ የለመደው መንግሥት፤ ጎርጎራ መልማት አለበት ብሎ ማመን ብቻውን ያስመሰግናል፡፡ ማስጀመር ደግሞ ትርጉሙ ብዙ ነው
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ደንቢያ በታች ወርዶ የለመደው መንግሥት፤ጎርጎራ መልማት አለበት ብሎ ማመን ብቻውን ያስመሰግናል፡፡

ደንቢያ በታች ወርዶ የለመደው መንግሥት፤ጎርጎራ መልማት አለበት ብሎ ማመን ብቻውን ያስመሰግናል፡፡ ማስጀመር ደግሞ ትርጉሙ ብዙ ነው

(ሄኖክ ስዩም ~ ድሬቲዩብ)

አትውረጂ አላልኩም ከአዘዞ በታች

ደንቢያ ከብት ያለምዳል እንኳን የሰው ልጅ፤

መንግስት ደንቢያ ወርዶ ለምዶ ቀርቷል፡፡ በአስገራሚ ሁኔታ ከ66 አብዮት መፈንዳት በኋላ ተዳፍኖ የኖረው የደንቢያ ልማት ነበር፡፡ ማር ዘነቡ ደንቢያ እሬት ኑሮ እንዲገፋ ተደርጓል፡፡ መሰረተ ልማቱ ወድቆ ሀገሩ ሁሉ እያለው ሁሉን ያጣ ሆኖ ኖሯል፡፡

 የኢትዮጵያ ጠላት የተባለው ጣሊያን እንኳን ሀገር ወርሮ ለደንቢያ ግን ያሰበው መልካም ሀሳብ ነበር፡፡ ከሱሲኒዮስ እስከ ዛሬ ደንቢያ የታሪክ ሌማት፣ የጥጋብ ምድር፣ የልግስና ርስት ነበር፡፡

የጎርጎራ ፕሮጀክት ለአማራ ክልል ልማት አነቃቂ ዕጽ ነው፡፡ የፈዘዘው ሹም ይነቃል፡፡ ቀጥሎ የጎደለውን ለመሙላት ጎርጎራ ብርታትና ጉልበት ይሆናል፡፡ ያን የመሰለ ውብ ስፍራ እንዳይለማም እንዳይታይም በማድረግ በኩል ቀዳሚው ጥፋተኛ የምለው ባህር ዳር ተቀምጦ  “ሆዴን ከሞላሁ ወገኔ መራቡ ምኔ ነው?” ያለ ሹም እንደሆነ ተጠራጥሬ አላውቅም፡፡

ዛሬ በገበታ ለሀገር ጎርጎራ አንዱ ተጠቃሚ መዳረሻ ሆኗል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮጀክቱን አስጀምረዋል፡፡ የጎርጎራ ተስፋ ብዙ ነው፡፡ ገበታ ለሀገርን የክልሉ መንግስት እንደ ፈረስ ሊቆጥረው ይገባል፡፡

ይደርስበታል እንጂ አይዋጋበትም፡፡ የሚበልጠው የሚሰራው ከዚህ በሚያልፍ ከደንቢያ አላፋ፣ ከባህር ዳር ፎገራ ከቁንዝላ ማንጌ በሚዘረጋ እጅግ እልፍ ህዝብ ጠቃሚ የልማት እቅድ ነው፡፡

እንዲህ ያለው መንፈስ የትም መዳረስ እንዲችል በጋራ መስራት በጋራ ማሰብ በጋራ መነሳት ይፈልጋል፡፡ ያ ከሆነ ጦሳ ላይ ተአምር እናያለን፤ ከአሸተን አቡነ ዮሴፍ ድንቅ ነገር ይሆናል፡፡ ባህር ዳር የውበትም የገንዘብም ዳርቻ ትሆናለች፡፡

የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ተጠቃሚዋ ጎርጎራ ትናንት ስትመኘው የኖረችው የልማት እቅድ ተበስሮባታል፡፡ በእኔ እምነት ጎርጎራ መልማት አለበትና ይገባዋል ብሎ ማሰብ ብቻውን መልካም ነገር ነው፡፡ ጎርጎራ ምን እንደሆነ ሳይገዳቸው በኖሩ ሹሞች ጫንቃው ለጎበጠው የክልሉ ህዝብ መልማት አለበት የሚለው በራሱ ልግስና ነው፡፡ 

ቀጥሎ እንዲለማ መሰረተ ድንጋይ ማኖር ማቀድ ገንዘብ መሰብሰብና ዘመቻውን ማስጀመር ትርጉሙ ብዙ ስለሆነ ያስመሰግናል፡፡ ቀጣዮ እንደ ጠቅላዮ የአቶ አገኘሁ ተሻገር እቅድ ሌሎች ስፍራዎችን በክልሉ ህዝብ ንቅናቄ ማልማት ነው፡፡ ጎርጎራን ለመታደግ የተጀመረው ዘመቻና የክልሉ መንግስት ተሳትፎና መነሳሳት እጅግ ያስመሰግናል፡፡

እንኳን ለልማት ለጥፋትም ተባብረን የኖርን ህዝቦች ነን፤ ስንገፋ ዝም እንደማለት ለጥፋት መተባበር የለም፡፡ ዛሬ ስንለማ አብሮ መቆም ውጤቱን ሸጋ ያደርገዋል፡፡ ያኔ የጎርጎራ ልማት ዙሪያ ገባውን ከገባበት የችግር ህመም የሚያድን ልማት ይሆናል፡፡ 

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top