Connect with us

ለህልውናዬ ሰጋሁ ያለችው አሜሪካ ሱማሊያ ልካ እንዳላዋጋችን ዛሬ ህግ ለማስከበር በሚደረግ የውስጥ ጉዳይ አንድን ሀገር እንደሁለት ተመለከተች፡፡

ለህልውናዬ ሰጋሁ ያለችው አሜሪካ ሱማሊያ ልካ እንዳላዋጋችን ዛሬ ህግ ለማስከበር በሚደረግ የውስጥ ጉዳይ አንድን ሀገር እንደሁለት ተመለከተች፡፡
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ለህልውናዬ ሰጋሁ ያለችው አሜሪካ ሱማሊያ ልካ እንዳላዋጋችን ዛሬ ህግ ለማስከበር በሚደረግ የውስጥ ጉዳይ አንድን ሀገር እንደሁለት ተመለከተች፡፡

ለህልውናዬ ሰጋሁ ያለችው አሜሪካ ሱማሊያ ልካ እንዳላዋጋችን ዛሬ ህግ ለማስከበር በሚደረግ የውስጥ ጉዳይ አንድን ሀገር እንደሁለት ተመለከተች፡፡

ኢትዮጵያ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች፡፡

(እሱባለው ካሳ)

የተመድ ምክር ቤት ያለ መግባባት ተበተነ፡፡ በኢትዮጵያ ጉዳይ ገና ዓለም ቋንቋው እንደባቢሎን ይደበላለቃል፡፡ አሜሪካን በትግራይ ያለውን ሁኔታ ያየችበት ዓይን የተንሸዋረረ ነው፡፡ እንደ አሜሪካ ያለ የትም እየገባ የሚያምስ መርህ አልባ ሀገር ኤርትራንም ሆነ ኢትዮጵያን አሁን ባሉበት ሁኔታ ለመውቀስ ሞራል የለውም፡፡

የኤርትራ ወታደሮች ወደ ትግራይ ገብተው ከሆነ ጉዳዩ መታየት ያለበት ከመሰረቱ ነው፡፡ የኤርትራ መንግስት በትግራይ የመሸገው ወንበዴ የደህንነቴና የብሔራዊ ጥቅሜ ስጋት ነው ብሎ አምኗል፡፡ በኢትዮጵያ በኩል ይህ ወንበዴ የትም አይደርስምና አያሳስብም እኔ ሃላፊነት እወስዳለሁ ያለ መንግስት የለም፡፡ ህወሃት ሃላፊነት የሚወሰድለት መንግስት አይደለም፡፡ 

ታሪክ አንድ ዜጋ አደረገን እንጂ ኢትዮጵያን ቀብሮ በመቃብሯ ላይ ለመጨፈር ሙዘቃውን ያሳናዳ የታሪክ አራሙቻ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም አሜሪካ አፍጋኒስታን ድረስ የወሰዳት የአፍጋን መንግስት አልቃይዳ የተባለውን አሸባሪ ቡድን መጥረግ የማይችል ስለሆነና እሷ ለደህንነቴ ሰጋሁ ስላለች ነው፡፡ አሜሪካ ብዙ አህጉር አቋርጣ አንድን አሸባሪ ቡድን ለማጥፋት ጦር ከሰበቀች፡፡ ኤርትራ ድንበሯ ስር የተሸጎጠውንና የሀገሩ መንግስት ጭምር የተቸገረበትን ቡድን ለማጥፋት ብትሞክር ጥፋቱ ምንድን ነው?

የኢትዮጵያ መንግስት ህዝቡን አስተባብሮ የሀገሩን ጠላትና የብሔራዊ ጥቅሙን እንቅፋት ቢያስወግድ ህግን ለማስከበር ያደረገው ዘመቻ እንጂ እንደ አሜሪካኖቹ ነዳጅ ለመማስ አልያም ቀጠና ለማመስ አይደለም፡፡ ይህ ቡድን የጎረቤት ሀገራትን ጭምር በሮኬት ያጠቃ የቀጠናው ነቀርሳ ነው፡፡ 

ቡድኑን ለማስወገድ የክልል ልዩ ሃይል ፖሊሶችን ከመከላከያ ጋር በማቀናጀት ዘመቻ አውጆ በከፊል አሳክቷል፡፡ ከተሳታፊው ዘማች መካከል ለምን አማራን መርጦ ከትግራይ የአማራ ልዩ ሃይል ይውጣ የሚል መፈክር ማሰማት አስፈለገ? የአማራ ልዩ ሃይል በፌዴራል መንግስቱና በመከላከያ ሠራዊቱ የድጋፍ ተልእኮ ከተሰጠው በሀገር አንድነት ላይ እንቅፋት የሆነን አንድ ሰው አራጅ ቡድን ለማስወገድ መዝመቱ ሌላ ሀገር የገባ ሉዓላዊነት የጣሰ ቡድን ተደርጎስ እንዴት ይቆጠራል?

የትህነግ ቡድን ያስተዳድራቸው የነበሩና በጉልበት ከአማራ ክልል ተወስደዋል በሚባሉ ግዛቶች ቡድኑ በስልጣን ላይ ሳለ ሰዎች ታርደዋል፡፡ በጅምላ ተቀብረዋል፡፡ ዛሬ በምንም ሁኔታ ለዚህ ቡድን ማንሰራራት ድጋሚ እድል መስጠት የለብኝም ብሎ ቁርጥ አቋም የያዘው የኢትዮጵያ መንግስት እንደ አሜሪካ ባሉ ሃይሎች ሀገሩን እንዲያፈርስ ግብዣ ቀርቦለታል፡፡

በኢትዮጵያ የህግ ማስከበር ዘመቻ የኢትዮጵያ ነቀርሳ የሆነውን ህወሃት በመደምሰስ ሂደት ንጹሃን ከተጎዱ ይሄ በምርመራ መጣራት አለበት፡፡ የትህነግ አጥፊ ቡድን መሪዎች ግን ለወጣቱ በጩቤና በገጀራ ጭምር ከሀገሩ ሰራዊት ጋር እንዲፋለም ባቀረቡት ጥሪ መሰረት ጥሪውን ተከትሎ እድሉን ሲሞክር መስዋዕት ለሆነው ሃይል ንጹሃን ተገደሉ ብሎ ሽፋን መስጠትም ልክ አይደለም፡፡

ወጣቶችን ለጦርነት አሰልፎ እጅግ በሚዘገንን የጦር ስልት ያስፈጀ ሽብርተኛ ሽንፈቱን ተከትሎ ከዝርፊያው ባቃመሳቸው የውጪ ቡድኖቹ አማካይነት እየፈጠረ ያለው ዓለም አቀፍ ድራማ ከጩኽት ያለፈ ትርጉም እንደማይኖረው ለመረዳት መሬት ላይ ያለውን እውነታ መመልከቱ በቂ ነው፡፡

ኢራን ከገባ ሰጋሁ ብሎ በሶሪያ ጉዳይ እጁን ከሰደደ አፍጋኒስታንን ካመሰ የመን ስትወድም ፈገግታ ከለገሰ ሃያል ሀገር እንዲህ ያለው ተጽእኖ ለምን እንደመጣ ማወቅ ከባድ አይደለም፡፡ ሀገር የሰራነው እንዲህ ያለ ዓለም አቀፍ የሃያልንን ሴራ በየጊዜው በጣጥሰን ነውና፤

በዚህ ሂደት የተፈጠረ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዝርፊያ አስገድዶ መድፈርና ሌሎች ወንጀሎች በአሜሪካን ሀገር እንደሚፈጠሩና የእኛን ጣልቃ ገብነት እንዳልፈለጉ ወንጀሎች በውስጥ አሰራር የሚፈቱ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች፡፡ 

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top