Connect with us

ኦፌኮ ለመጪው ምርጫ ዕጩ አላቀረበም

ኦፌኮ ለመጪው ምርጫ ዕጩ አላቀረበም
ፎቶ :- ኘሮፌሰር መረራ ጉዲና

ዜና

ኦፌኮ ለመጪው ምርጫ ዕጩ አላቀረበም

ኦፌኮ ለመጪው ምርጫ ዕጩ አላቀረበም

~የዕጩዎች ምዝገባ ትላንት ተጠናቋል፣

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ፓርቲ (ኦፌኮ) በመጪው ምርጫ እንደማይሳተፍ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና አስታወቁ፡፡

የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ለሸገር ራዲዮ እንደተናገሩት ብሔራዊ መግባባት ሳይኖር ምርጫ እናካሂዳለን ማለት ጥቅም የለሽ ነው ብለዋል፡፡ ፓርቲው በእስካሁን ቆይታው አንድም ዕጩ አባል ለውድድሩ አለማስመዝገቡን በመጥቀስ ቴክኒካሊ ከምርጫው ወጥተናል ማለታቸው ተዘግቧል፡፡

በምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት ሰሞኑን በተካሄደው የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብሰባ ላይ አንዳንድ ፓርቲዎች ለመጪው ምርጫ ተንቀሳቅሶ ለመስራት ምህዳሩ አመቺ አለመሆኑንና በገዥው ፓርቲ ተጽዕኖ እየተደረገባቸው በመሆኑ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ ይሆናል ብለው እንደማይጠብቁ በቅሬታ መልክ ሃሳባቸውን አቅርበዋል፡፡

ገዥውን ፓርቲ በመወከል የተገኙነት አቶ ዛዲግ አብርሃ በበኩላቸው የብልጽግና ፓርቲ ምርጫው ካለፈው የተሻለ ነጻና ዴሞክራሲያዊ በማድረግ ካሸነፈ ለመቀጠል፤ ካላሸነፈ በተቀናቃኝ ፓርቲነት ለመቀጠል ወስኖ እየተንቀሳቀሰ ነው ብለዋል፡፡

 አያይዘውም ፓርቲው የስነምግባር ደንብ አውጥቶ በማሳተም ለአባላቱ እያሰራጨ መሆኑን ፣ ለአባለቱ ተገቢውን ስልጠና እየሰጠ በመሆኑ አባሎቹ በዚሁ መሰረት ሕግና ስርዓትን አክበረው እንደሚንቀሳቀሱ አስረድተዋል ሲል ሸገር ዘግቧል፡፡

ምርጫ ቦርድ በዚሁ የውይይት መድረክ ላይ የምርጫ ምልክት ከወሰዱ 54 ፓርቲዎች እስካሁን ዕጩዎቻቸውን ያስመዘገቡ ፓርቲዎች 15  ብቻ መሆናቸውን ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የቦርዱ ሰብሳቢ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡

ምርጫ ቦርድ ቀደም ሲል ያወጣውን የዕጩዎች ምዝገባ የጊዜ ሰሌዳ  በአራት ቀናት ያራዘመ ሲሆን ቦርዱ ከዚህ በኋላ በድጋሚ ለማራዘም ፍላጎት እንደሌለው የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን መናገራቸው ተሰምቷል፡፡ በመሆኑም በቦርዱ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የእጩዎች ምዝገባ ስራው በትላንትናው  ዕለት ማለትም የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡

በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫን ለማስፈጸም 140 ሺህ በላይ አስፈጻሚ ለመሆን የሚችሉ ሰዎችን ምልመላ የሚያከናውንበት ሂደት በማጠናቀቅ የአስፈጻሚዎችን ፍቃደኝነትን፣ ገለልተኝነትን እና ብቃትን በማረጋገጥ ስራ ላይ አንደሆነ በመግለጽ በምርጫ አስፈጻሚነት ስራ አገራቸውን ማገልገል ለሚፈልጉ ኢትዮጵያዊያን ጥሪ አቅርቧል፡፡

በዚሁ መሰረት ለስራው ማመልከት የሚፈልገ ወገኖች ተከተታዮቹን መስፈርቶች ሊያጤኑ ይገባል፡፡

ምርጫ አስፈጻሚዎች የምርጫ ሂደቱ ዋና አካል መሆናቸውን በመረዳት እና ስራውም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ በመሆኑ እንዲሁም የምርጫ ሂደቱ ከተጀመረ በኋላ የሰው ሃይል እጥረት እነዳይፈጠር በማሰብ ተጨማሪ የሰው ሃይል ምልመላ ማከናወን እንዳለበት አምኗል።

በዚህም መሰረት

– ለምርጫ አስፈጻሚነት በገለልተኝነት አገራችሁን ለማገልገል የምትፈልጉ

– ምንም አይነት ፓርቲ አባልነት፣ የዝቅተኛ የአስተዳደር እርከኖች ላይ ሰርታችሁ የማታውቁ

– ከሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ውጪ በሌሎች የቀድሞ ምርጫ የማስፈጻም ተግባራት ላይ ተሳትፋችሁ የማታውቁ

– የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ ረጅም አመት የስራ ልምድ ያላችሁ

የሚከተለውን ፎርም በመጠቀም በሚቀጥሉት አራት ቀናት እስከ የካቲት 27 ድረስ ብቻ ማመልከት ትችላላችሁ።

የስራው ቆይታ ለ4 ወራት ሲሆን፣ የቀን አበል፣ አስፈላጊ የሆኑ ቦታዎች/ ሁኔታዎች ላይ ጥበቃ፣ እንዲሁም ስራውን ለማከናወን የሚያስፈልጉ ማንኛውንም ነገሮች ቦርዱ ያሟላል።

የስራ ልምድ ሰርተፍኬት፣ የድጋፍ ደብዳቤ በቦርዱ የሚሰጥ ይሆናል።

ፎቶ :- ኘሮፌሰር መረራ ጉዲና

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top