Connect with us

“…እቃወማለሁ!”

"...እቃወማለሁ!"
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

“…እቃወማለሁ!”

“…እቃወማለሁ!”

አርቲስት መቅደስ ፀጋዬ

በማንም ይሁን በማን በትግራይ የሚደርሰው የሴት እህቶቼን መደፈር እቃወማለሁ!!!

ዝምታ ግዴለሽነት ብቻ አይደለም። ዝምታ የሚያደርጉትና የሚናገሩትን አጥቶ ግራ ተጋብቶ መቀመጥም ነው። በትግራይ ከጦርነቱ ወዲህ በደረሰው ሁለንተናዊ ምስቅልቅል የማያዝን ኢትዮጵያዊ የለም። በተለይ ደግሞ በሴት እህቶቻችን ላይ የሚሰማው የመደፈር ወንጀል በያለንበት በሰቀቀን እንድንቀመጥ ያደረገን ጉዳይ ነው።

በእርግጥ ለብዙዎች የሚያስጨንቃቸው የደፋሪዎቹ ማንነት ነው። እኔ ግን:- በማንም ይሁን በማን በትግራይ የሚደርሰው የሴት እህቶቼን መደፈር እቃወማለሁ!!! ቁምነገሩ ወንጀሉ በማንም ይፈጸም በማን የድርጊቱ ፈጻሚዎች ታድነው ለሕግ መቅረብ አለባቸው የሚለው ነው። ተጎጂዎቹም አስፈላጊውን የሕክምና የስነልቦና እርዳታ የሚያገኙበት መንገድ በፍጥነት መመቻቸት ይገባዋል።

አሁን ያለው ትልቁ ፈተና የፖለቲካው ጩኸት ሰብአዊ ድምጾችን እየዋጣቸው መሆኑ ነው። ነገሮችን በሰብአዊነት መንፈስ መረዳት ሞቷል ማለት ይቻላል ። የአንድ ሰው መፈናቀል፣ መሞት ወይም መደፈር ስንሰማ የሚቆጠቁጠን የተጎጅው ብሔር እንጂ የግለሰቡ ጉዳት አለመሆኑ ያሳዝናል።  እንደዚህ ዓይነት ሰዎች በሁሉም ቦታ አሉ።  

በዚህም ላይ በሰብአዊነት የተነገሩ ድምጾችንም ጠልፈው ወደሚፈልጉት አጀንዳ ይቀይሩባችኋል።

እኔ ከኢትዮጵያዊነት አልፌ መስፋት የምመኝ እንጂ ከኢትዮጵያዊነት አንሼ መጥበብ የሚዋጥልኝ ሴት አይደለሁም። የህዝብ ልጅ እንደመሆኔ መጠን በየትኛውም የሀገሬ ክፍል ለሚፈጠር ችግር ባለኝ አቅም ድምፄን አሰማለሁ፡፡ በትግራይ ለሚገኘው ወገኔ ግን ፍቅሬንና አክብሮቴን የምገልጽበት ጊዜ አምላኬ ይሰጠኛል ብዬ በተስፋ እጠብቃለሁ!!

አይዞኝ እህቶቼ በርቱልኝ!!

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top