Connect with us

በህዳሴ ግድብ አካባቢ ሆቴል ሊገነባ ነው

በህዳሴ ግድብ አካባቢ ሆቴል ሊገነባ ነው
Ethiopian press agency

ዜና

በህዳሴ ግድብ አካባቢ ሆቴል ሊገነባ ነው

በህዳሴ ግድብ አካባቢ ሆቴል ሊገነባ ነው

 የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሲጠናቀቅ የሚፈጠረውን የቱሪስት መስህብ ለመጠቀም  በአካባቢው የራሱን ሆቴል እንደሚገነባ አስታወቀ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የቱሪዝም ሃብት በስፋት ጥቅም ላይ እንዲውል ልዩ ልዩ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኘም ገለፀ።

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አቶ ከማል አብዱራሂም እንደገለፁት፤ ዩኒቨርሲቲው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሲጠናቀቅ የሚፈጠረውን የቱሪስት ከተማ ተከትሎ በአካባቢው ላይ የራሱን ሆቴል ለመገንባት በአስር ዓመት መሪ እቅዱ ውስጥ አካቶ እየሰራ ይገኛል።

ክልሉ ከቱሪዝም አኳያ እምቅ ሀብት ያለው መሆኑንም የጠቆሙት አቶ ከማል፤ ዩኒቨርሲቲው በቅድሚያ በክልሉ የሚገኙ የባህልና የቱሪዝም ሃብቶችን የማስተዋወቅ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ከነዚህ ውስጥም የበርታ ብሄረሰብ የሚጠቀምበት ‹‹ዙምባራ›› የተሰኘውን የትንፋሽ ሙዚቃ መሳሪያ የክልሉ አንድ መለያ መሆኑን በመለየት አስመዝግቦ ጥናት እንዲካሄድበት እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል። በክልሉ ያሉ የሌሎች ብሄረሰቦችን ባህላዊ መሳሪያዎቻቸውን ለማስተዋወቅ ተመሳሳይ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።(ኢ ፕ ድ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top