Connect with us

#ሀገሬን!!

ስለሀገሬን
ሄኖክ ስዩም

ነፃ ሃሳብ

#ሀገሬን!!

#ሀገሬን!!

(ሄኖክ ስዩም)

እነሆ “ለሀገሬ” ሰው “ሀገሬን” እንካችሁ ብያለሁ፡፡

ሦስተኛዋ መጽሐፋችን ታትማለች፡፡ ስሟን “ሀገሬን” ብለናታል፡፡ ወደ ሀገሬ የተደረገ ጉዞ ነው፡፡ አባይ ሸለቆ ውስጥ እንገባለን፤ ጀግኖቹ የጉምዝ ባላባቶችን ለሀገር የተከፈለ ተጋድሎ ባድማቸው ድረስ ሄደን እናያለን፡፡ ደግሞ ወደ ምስጢራዊው ገዳም አብረን ደርሰናል፡፡ ደቅ፤ መተከል ያለው የሥውራን ስፍራ፤

ከእሳት ባህር እስከ ዱሩ-ብዙ ትረካዎችን ይዟል፤ ከዝኆን ጋር የተፋጠጥንባቸው የዱር ሕይወት ትዝታዎችም ተከትበውበታል፡፡ እንስሳቱ የት ገቡ? ብለን የነበረን ነበር ሲሆን አብረን እንሞግታለን፡፡

ስለ ኮማንዶ ምኑን ልንገራችሁ፤ እላያችን ላይ የፈነዳ እሳተ ገሞራን ያስመለጠ አርብቶ አደር እኮ ነው፡፡ እሳት ዳር ቁጭ ብለን ጂኒዎቹ ለምን መጡ? ዛሬም የሚያስፈራ፤ ዛሬም የሚያስቅ ምሽት፤ ጎፋ መርቆኛል፡፡ አህያ ቀንድ እስክታበቅል መስቀልን ኖሬ እመለከት ዘንድ፤ የጎፋው ኢትኖግራፊም፣ ታሪክም፣ ጉዞም ነው፡፡ 

ጉንዳ ጉንዶ መድረስ ጀግንነት መሆኑን አምኜ ጽፌዋለሁ፡፡ ሌሎቹን ምዕራፎች ባልነካቸው ይሻለኛል። ስትገልፁት ድረሱበት።

ተአምረ ምኒልክ፣ መልከአ ምኒልክ፣ ገድለ አበው ዘ አድዋና ገድለ አበው ዘ ኢትዮጵያ በክብር ከነገረ አንበሳ አንድ ምዕራፍ ጋር ታጅበው ቀርበውበታል፡፡ በቦታው የታየውን ስለቦታው ቀድሞ ከተፃፈው ጋር ተዋህዶ ከብዙ ድካም በኋላ እጃችሁ መግባቱን እነግራችኋለሁ፡፡ በእግርም በእጅም የተጻፈ መጻሕፍ ነውና፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top