Connect with us

የደምበጫ-ሰቀላ እና የቢቡኝ ወረዳ አገናኝ  የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ስራ ዛሬ በይፋ ተጀመረ፡፡ 

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የደምበጫ-ሰቀላ እና የቢቡኝ ወረዳ አገናኝ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ስራን ዛሬ በይፋ አስጀመሩ፡፡
ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን

ዜና

የደምበጫ-ሰቀላ እና የቢቡኝ ወረዳ አገናኝ  የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ስራ ዛሬ በይፋ ተጀመረ፡፡ 

የደምበጫ-ሰቀላ እና የቢቡኝ ወረዳ አገናኝ  የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ስራ ዛሬ በይፋ ተጀመረ፡፡ 

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የደምበጫ-ሰቀላ እና የቢቡኝ ወረዳ አገናኝ  የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ስራን ዛሬ በይፋ አስጀመሩ፡፡ 

በደጋዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ በተካሄደው  የፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር  ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘው ተሻገር ፣የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ ብናርፍ አንዱአለም ፣ የምክር ቤት አባላት የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ  ታድመዋል፡፡ 

በመርሃ ግብሩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን መንግስት በመደበው ከ1 ነጥብ  7ቢልየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባው የደምበጫ-ሰቀላ እና የቢቡኝ ወረዳ አገናኝ 70 ኪ.ሜ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የህዝቡን የአመታት ጥያቄ ምላሽ የሰጠ ነው ብለዋል።

ደረጃውን የጠበቀ  የመንገድ መሰረተ ልማት ባለመኖሩ የአካባቢው ነዋሪ ሲቸገር መቆየቱን አስታውሰው  ይህ ታሪክ ሊሆን በመቃረቡ ለመላው ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ 

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘው ተሻገር የክልላችን የመንገድ ጥያቄ ደረጃ በደረጃ ምላሽ እያገኘ ነው ለዚህም በዛሬው እለት የተጀመረው የደምበጫ-ሰቀላ እና ቢቡኝ አገናኝ መንገድ አንዱ ማሳያ በመሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል ፡፡ 

መንገዱን ዛሬ በይፍ እንዳስጀመርነው ሁሉ ፍጻሜውን ያገኘ ዘንድ መላው የአካባቢው ህዝብ እንዲሁም አመራሩ ያልተቆጠበ ትብብርና ድጋፉን እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኘ በበኩላቸው የደምበጫ-ሰቀላ እና የቢቡኝ ወረዳ አገናኝ ኮንትራት 1 መንገድ በተባለው ጥራትና ጊዜ እንዲጠናቀቅ ኢመባ  አስፈላጊውን ድጋፍ ክትትል እና ቁጥጥር እንደሚደረግ አረጋግጠዋል፡፡ 

በዚሁ መርሀ ግብር ላይም ከሰቀላ -አዴት የሚዘልቀው 60 ኪ.ሜትር መንገድ በቀጣይ ወደ ስራ ለማስገባት በሂደት ላይ እንደሚገኘ ጠቁመዋል።

መላው የአካባቢው ነዋሪ የስራ ተቋራጩም ሆነ አማካሪ ድርጅቱ ፕሮጀክቱን በጥራትና በብቃት እንዲያጠናቅቅ  የተጣለባቸውን ሀላፊነት እንዲወጡም አሳስበዋል፡፡ 

 የመንገድ ግንባታውን  የሚያካሂደው  የአማራ መንገድ ስራዎች  ድርጅት ሃላፊ አቶ  አስማማው አለማየው ተቋማቸው ግንባታውን በጥራትና በቅልጥፍና ሰርቶ እንደሚያስረክብ ቃል ገብተዋል ፡፡ 

አገር በቀሉ ኮር ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ የመንገዱን ጥራት በመቆጣጠር እና በማማከር  ይሳተፋል፡፡

የደምበጫ- ሰቀላ እና ቢቡኝ አገናኝ ኮንትራት 1  የጠጠር መንገድ በአገልግሎት ሳቢያ በከፍተኛ ሁኔታ የተበላሸ ነው።

ፕሮጀክቱ በቀጣይ ከሚኖረው  ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አንጻር  የመንገዱ የጎን ስፋት በወረዳ ከተሞች 29.5 ሜትር በቀበሌ 12 ሜትር  እንዲሁም በገጠሩ ክፍል 10 ሜትር ስፋት  እንዲኖረው ተደርጎ  ደረጃውን ጠበቆ  ይገነባል፡፡ 

ግንባታው ሲጠናቀቅ አካባቢው ከፍተኛ የግብርና ምርቶች ፣ የቁም እንስሳት እና

 የቀርክሃ ምርት ውጤቶች ወደገበያ አውጥቶ በመሸጥ አምታችንና ሸማችን የጋራ ተጠቃሚ ያደርጋል ፡፡ 

የመንገድ ፕሮጀክቱ ከአዲስ አበባ በደጀን ደብረማርቆስ በዳንግላ አድረጎ ባህርዳር የሚገባው መንገድ እና በአዲስ አበባ ደጀን ደብረወርቅ መርጦ ለማርያም ወደ ባህርዳር የሚዘልቀውን ሌላኛውን ዋና መንገድ በአቋራጭ የሚያገናኝ ግዙፍ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለው የመንገድ ፕሮጀክት ክፍል ነው ፡፡ 

በመስመሩ የሚገኙትን ዞኖችና ወረዳዎች በቅርበት በማስተሳሰር  ከዚህ ቀደም ከደምበጫ ተነስቶ ሰቀላ ድረስ 70 ኪ. ሜትሩን በተሽከርካሪ ለመጓዝ ይፈጅ የነበረውን አራት ሰዓት ከግማሽ በታች ያሳጥረዋል፡፡ 

 የመንገድ ፕሮጀክቱ በሚገነባበት አካባቢ የሚገኙትን ጥንታዊ እና ታሪካዊ ገዳማት፣ የአባይ ተፋሰስ የውሃ ማማ የሚል ስያሚ የተሰጠው 4100 ሜትር ሚረዝመው   የጮኬ ተራራ  መገኛ ስፍራ  በመሆኑ የመንገዱ ደረጃ ማደግ የቱሪስት ፍሰቱን ከመጨመር አኳያ የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረክታል ፡፡ 

ፕሮጀክቱ በውል ስምምነቱ መሰረት በሶስት አመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል፡፡(ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top