Connect with us

“የውጭ ኃይል ጣልቃ ገብነት ተቀባይነት የለውም”

"የውጭ ኃይል ጣልቃ ገብነት ተቀባይነት የለውም"
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ዜና

“የውጭ ኃይል ጣልቃ ገብነት ተቀባይነት የለውም”

“የውጭ ኃይል ጣልቃ ገብነት ተቀባይነት የለውም”

የኢፌድሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ፤ በተለይም የአማራ ልዩ ኃይልን በሚመለከት ያወጣው መግለጫ ተገቢነት የሌለው ነው አለ።

ኢትዮጵያ ሉዓላዊት ሀገር ናት ያለው ሚኒስቴሩ የውስጥ ችግሮቿን በራሷ ትፈታለች እንጂ የሕዝቦቿን እና የመንግሥትን ሉዓላዊነት የሚጥስ የውጭ ኀይል ጣልቃ ገብነት ፈፅሞ ተቀባይነት የለውም ብሏል።

ዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ በክልሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተፈፅመዋል በማለት ከማላዘን ይልቅ ለዜጎች አስቸኳይ ድጋፎችን በማሰባሰብ ሊተባበር ይገባል።

በክልሉ ተፈፀሙ ስለተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መንግሥት አስፈላጊውን ማጣራት እያካሄደ መሆኑንና የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት ለማስጠበቅ እየሠራ እንደሚገኝም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በጉዳዩ ላይ መንግሥት ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ወርደው በነፃነት እንዲያጣሩ ብቻ ሳይሆን በትብብር ለመሥራትም ዝግጁ መሆኑንም ገልጿል።

በትግራይ ክልል የሰብዓዊ አገልግሎት ድጋፍ ለሚያደርሱ እና ተፈጠረ ስለተባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለሚያጣሩ የዓለም አቀፍ ማኀበረሰብ አባላትም መንግሥት ቀና ትብብር እንዳለው ተመላክቷል።

መንግሥትም በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል ለሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት ቅድሚያ በመስጠት ከአጋር አካላት ጋር በትብብር እየሠራ መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ያስታወቀው።

በትግራይ ክልል እየተደረገ ያለው የሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት 70 በመቶው በመንግሥት፤ ቀሪው 30 በመቶ ደግሞ ከዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ በተገኘ ድጋፍ እየተሸፈነ መሆኑም ተገልጿል።

የድጋፍ አገልግሎት በክልሉ ለሚገኙ 3 ሚሊዮን ዜጎች ተደራሽ መሆኑን የጠቆመው የሚኒስቴሩ  ሴቶች እና ህፃናት ቅድሚያ የተሰጣቸው የኀብረተሰብ ክፍሎች መሆናቸውን ጠቅሷል።

በክልሉ እየታየ ያለው ሰላም እና መረጋጋት የሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎቱ ሳይስተጓጎል እንዲደርስ ምቹ ሁኔታን እንደፈጠረም መግለጫው አብራርቷል።

ሚኒስቴሩ በመጨረሻም በክልሉ ተንቀሳቅሰው የሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎቱን የተመለከቱት የዓለም የምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዲቢድ ቢስያል የድጋፍ አገልግሎት አበረታች መሆኑን አረጋግጠዋል ብሏል።

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top