Connect with us

የህዝቡ ምሳሌ ማን ነው? መሪዎች አርአያ ያልሆኑበት የኮሮና መከላከል ዘመቻ፡፡ 

የህዝቡ ምሳሌ ማን ነው? መሪዎች አርአያ ያልሆኑበት የኮሮና መከላከል ዘመቻ፡፡
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የህዝቡ ምሳሌ ማን ነው? መሪዎች አርአያ ያልሆኑበት የኮሮና መከላከል ዘመቻ፡፡ 

የህዝቡ ምሳሌ ማን ነው? መሪዎች አርአያ ያልሆኑበት የኮሮና መከላከል ዘመቻ፡፡ 

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ ድሬቲዩብ)

የህዝብ ምሳሌው መሪ ነው፤ መሪዎች አሁን እንኳን ምሳሌ ሊሆኑ ቀርቶ እንደ ህዝቡ አስቸጋሪ ጠባይ እየታየባቸው ነው፡፡ ኮሮናን በመከላከል ረገድ ጥሩ የሚባለው ጅምር አፈር ድሜ የበላው በፖለቲከኞች ዝንጉነት ነው፡፡

አደባባይ ወጥተው ህዝቡን ተከላከሉ እያሉ እንዳልቀሰቀሱ አሁን ደግሞ አደባባይ ወጥተው ህዝቡ ይዘናጋ ዘንድ ምክንያት እየሆኑ ነው፡፡

በቅርብ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ድጋፍ በሚል ሀገር ተቃቅፎ ሆ ሲል ጠቅላያችን በእኔ ጦስ ችግር እንዳይገጥማችሁ እባካችሁ ተጠንቀቁ አላሉም፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ ግን ዝንጉነታችን ያሳስበኛል ሲሉ ጽፈው አነበብን፡፡

መሪዎች ሲሆን አርአያ መሆን በተገባቸው ነበር፡፡ አልሆኑም መጨባበጡን ያሳዩን፣ መተቃቀፉን ያስለመዱን እነሱ ናቸው፡፡ ያ ሲገርመን ደግሞ በአንድ እቃ በጋራ መጠጣት አየን፡፡

ሀዋሳ ላይ እየተከበረ ያለው የሲዳማ ክልል የምስረታ አመታዊ በዓል እንዲህ ባለው ዝግጅት መድመቁና መከበሩ በራሱ ችግር የለውም፡፡ 

ከጥንቃቄ ጋር የሚሆኑ ነገሮች ቢያንስ ምክንያታዊ ናቸው፡፡ በአዘቦት ቢደረግ ውብ የሆነው በጋራ የመጠጣት የሲዳማ እሴት እንዲህ ባለው አስፈሪ የኮሮና ዘመን ቢቀር ግን ምንም አያጎድልም፡፡ በጤና ስንኖር ከርሞ ሁሉን ማድረግ እንችላለንና፤

ፖለቲከኞቹ በአንድ እቃ በጋራ መጠጣታቸው ብቻ ችግሩን አያከብደውም፤ እንደ መሪ የጤናቸው እክል እርግጥ ነው ህዝብ ይጎዳል፡፡ ከዚያ ሲያልፍ ግን የሚመለከትም ምን ይማራል ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡

 በቅርቡ የጤና ሚኒስትሯ በመንግስት የስራ ሃላፊዎች በኩል ኮሮናን ለመከላከል እየተሰራ ባለው ስራ ችግር ፈጣሪ ሆነው መታየታቸውን ጠቁመዋል፡፡ 

አስቸጋሪ አመራሮች ግዴለሽነታቸው መኮነኑ ልክ እንደ ነበር ለመረዳት ግን የሲዳማን የክልል ምስረታ አንደኛ አመት አመታዊ በዓል ኩነት ለተመለከተ ይረዳዋል፡፡

መገናኛ ብዙሃንም ሆኖ ምስልና ቪዲዮውን የሚያጋሩ ሰዎችም ቢሆኑ እንዲህ ያለ የመከላከል ስራው ላይ መዘናጋትን የሚጭን ተግባር ባያሳዩት ይመረጣል፡፡ ባይደረግ መልካም የሆነውን ያህል ቢደረግም እንኳን እንዳይታይ ማድረግ ደግሞ ጥሩ ነበር፡፡

ለማንኛውም ነገ ህዝቡን እንዲህ አታደርግም ለማለት አድርጎ ማሳየት ከመሪ የሚጠበቅ ነው፡፡ መሪ ያደረገውን ህዝብ ቢከተል ለመኮነን አይመችም፡፡ እናም መሪዎች ሆይ አርአያ ሁኑ፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top