ጅማ እንደሆን ጀግና ማውጣት ታውቅበታለች!!
(አቡ ኃ/ሚካኤል)
ይሄን ሰው በደንብ ተዋወቁልኝማ፡፡የጊቤ ወንዝ ማዶው የሀገር ባለውለታ ሱልጣን አባ-ጊሳ ይባላል፡፡ዲፕሎማት ነው፡፡ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ላይ ከ 13 ዓመት በላይ ሰርቷል፡፡አሁን በብዙ መልኩ ኢትዮጵያ በዲጂታል ዲፕሎማሲ በጠላቶቿ ብልጫ እየተወሰደባት ባለበት ጊዜ ጥርሱን ነክሶ የተነሳ ተሟጋች ነው፡፡
ከጉባ ተራራ ስር ኢትዮጵያውያን እያስቀመጡት ያለው ብሄራዊ አርማ ለግብፅ የልብ ውጋት ነው፡፡”እኔ ከወተቱ እንጂ ስለ ላሚቷ ግድ አይሰጠኝም” የሚል አቋምን ምታራምደው ጥንተ ጠላታችን ግብፅ ፡ ያገኘቸውን አጋጣሚ በመጠቀም የግድቡን ግንባታ ለማስቆም የማትምስብን ጉድጓድ የለም፡፡ፈርኦኖቹ ይህን የዘመናት የቁጭትና ብስጭት ዋጋ የሆነውን ግድብ ከጎሮሯችን ለመንጠቅ በየአለማቀፍ ተቋማትና ሚዲያዎች ምስለኔያቸውን ሰግስገው ጫና ሲያሳድሩ ከርመዋል፡፡እዚጋ ነው የጅማው ፍሬ ከፍ ብሎ የታየው፡፡
ግብፅ ቀለብ እየሰፈረች በየቦታው የወሸቀቻቸውን መርዝ አርከፍካፊዎች የሚመክቱ የዲጂታል ሰራዊቶችን አሰባስቦ ዘመቻ ከወጣ ሰነባብቷል፡፡
ከዚህ ቀደም በተናጠል ለሀገራቸው የሚሟገቱ ዜጎቻችን እያደነ ያሰባስባል፡፡መሃመድ አል-አሩሲ ፡ መቅደላዊት፡ ጋዜጠኛ ሰላም ፡ስላባት ፡ሀሊፊያን ጨምሮ አያሌ የዲጂታል ሰራዊቶችን እያስተባበረ ስለ ብሄራዊ አርማችን አባይ ሌተ ቀን ይለፋል፡፡
ግድቡን በሚመለከት የአለም ህዝብ ትክክለኛ መረጃ እንዲኖራቸው በተለያዩ አለማቀፍ ቋንቋዎች በርካቶች ወጥተው እንዲናገሩ ትክክለኛ ትጥቅ ያስጣጥቃቸዋል፡፡ዛሬ የ”ሱልጣን ልጆች ” ተፅዕኗቸው በርትቷል፡፡ግብፅና ወዳጆቿ የሚያሰራጩትን ፀረ-ኢትዮጽያ መረጃዎች እያነፈነፉ ተገቢ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡በየማህበራዊ ሚዲያዎቻቸው ቀፎው እንደተነካ ንብ ሆሆሆ ብለው የፈርኦኖቹን አይነስብ ያጠፋሉ፡፡በትላልቅ ሚዲያዎችም (በተለይ አረቡ አለም ተፅዕኖ ባላቸው)
የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም የሚያስከብሩ የቁርጥ ቀን ልጆችን መረጃ እያደረጀ በመስጠት ያሰልፋቸዋል፡፡ስራቸውን እየቆጠረም “በርቱ ለሀገራችሁ” እያለ ያጀግናቸዋል፡፡የግብፅን መርዘኛ አካሄድ በደንብ የተረዳው ይህ ጀግና በሁሉም ረገድ መፈናፈኛ የማይሰጡ ጠንካራ ሰራዊት አደራጅቷል፡፡ግብፆች ስለ አባይ ትንፍሸ ባሉ ቁጥር የ”ሱልጣን ልጆች” ፈጥኖ ደራሽ ናቸው፡
የሰውየው ሀገራዊ ጥብቅና በዚህ ብቻ የሚያበቃ አይደለም፡፡በተለያዩ አለማት ያሉ ተፅዕኖ አሳዳሪ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ከያሉበት አነፍንፎ በማሰባሰብ ለዘመቻ አሰማርቷል፡፡
ባለቅኔው ለምን ሲሳይ አቀንቃኙ አቤል “ዘ ዊኬንድ”ን ጨምሮ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ሰዎችን ስለ ግድቡ ባገኙት አጋጣሚ እንዲናገሩና በቲዊተር ገፃቸው እንዲፅፉ አድርጓል፡፡አሜሪካንን ጨምሮ በተለያዩ ተፅዕኖ አሳዳሪ ሀገራት ያሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ግድቡን በተመለከተ የኢትዮጵያን እውነተኛ አቋም እንዲገለፁ አስደርጓል፡፡አሁንም ይሄን እያደረገ ነው፡፡
ለዘመናት ጠላታችን ግብፅ ህመም የሆነ ልጆችን እያሰባሰብ ብሄራዊ አርማችንን እንድናቆም ሳትሰለች የምትደክው ወንድማችን በርታልን፡፡ላደረከውም ለምታደርገውሁሉ እናመሰግናለን፡፡ ጀባdhu!!!!