Connect with us

ንግድ ባንክ በ2013 የመጀመሪያ ግማሽ በጀት አመት 83 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር የተቀማጭ ገንዘብ ሰበሰበ

ንግድ ባንክ በ2013 የመጀመሪያ ግማሽ በጀት አመት 83 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር የተቀማጭ ገንዘብ ሰበሰበ
የኢት ንግድ ባንክ

ዜና

ንግድ ባንክ በ2013 የመጀመሪያ ግማሽ በጀት አመት 83 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር የተቀማጭ ገንዘብ ሰበሰበ

ንግድ ባንክ በ2013 የመጀመሪያ ግማሽ በጀት አመት 83 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር የተቀማጭ ገንዘብ ሰበሰበ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2013 የመጀመሪያ ግማሽ በጀት ዓመት መልካም ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን አስታወቀ፡፡ 

ባንኩ በ2013 የመጀመሪያ ግማሽ አመት መልካም ውጤት ካስመዘገበባቸው ዘርፎች ዋነኛው የደንበኞች የተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰብ ነው፡፡

በግማሽ ዓመቱ ባንኩ 2.5 ሚሊዮን አዳዲስ የተቀማጭ ሂሳቦችን ያስከፈተ ሲሆን፣ የዕቅዱን 221 በመቶ በማከናወን ተጨማሪ 83.2 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ ሊያሰባስብ ችሏል፡፡

የባንኩ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ ክምችት 678.7 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፤ ይህም ከዕቅድ በላይ የ107 በመቶ ክንውን አሳይቷል፡፡ የባንኩ ደንበኞች ቁጥርም 27.5 ሚሊዮን ደርሷል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀገራችን ለሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች ዋነኛ የፋይናንስ አቅራቢ መሆኑን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በግማሽ በጀት አመት ውስጥ 47.2 ቢሊዮን ብር አዲስ ብድር አቅርቧል፡፡ በተመሳሳይ በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ውስጥ 26.1 ቢሊዮን ብር ከተበዳሪዎች መሰብሰብ ተችሏል፡፡ 

ባንኩ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሠራባቸው ዘርፎች መካከል ለተለያዩ የመንግስትና የግል የልማት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያና ለገቢና ወጪ ንግድ የሚውል የውጭ ምንዛሪ በማሠባሰብ ማቅረብ ሲሆን፣ በግማሽ በጀት አመት የ2.5 ቢሊዮን ዶላር አቅርቦት አድርጓል፡፡

እስከ በጀት ዓመቱ ግማሽ ድረስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠቅላላ ሀብት 903.6 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡ 

የባንኩን አገልግሎቶች ለህብረተሰቡ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈትና የኤሌክትሮኒክ አገልግሎቶችን በማቅረብ ረገድ በግማሽ አመቱ ባንኩ አበረታች አፈፃፀም ያሳየ ሲሆን፣ 42 አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈት የቅርንጫፎቹን ብዛት 1,646 ማድረስ ችሏል፡፡ 

የኤሌክትሮኒክ ባንክ አገልግሎቶችን ለማዳረስ ባንኩ እያደረገ ባለው ጥረት 1.4  ሚሊዮን የኤ.ቲ.ኤም ካርድ ፣ 9,200 የኢንተርኔት ባንኪንግ እና  1.8 ሚሊዮን የሞባይል ባንኪንግ አዳዲስ ተጠቃሚ ደንበኞችን ማፍራት ተችሏል፡፡  ከ2.6 ሚሊዮን በላይ የሲቢኢ ብር ደንበኞች እና ከ7,600 በላይ የሲቢኢ ብር ወኪሎችን በመመልመል ወደ ስራ ማስገባትም ተችሏል፡፡ 

በአጠቃላይ በግማሽ ዓመቱ ባንኩ ያስመዘገበው የሥራ አፈፃፀም መልካም ውጤት የተመዘገበበት ሲሆን፣ ባንኩ ካለፈው አመት ጀምሮ በሀገራችን እና በዓለም  አቀፍ ደረጃ ትልቅ ፈተና የነበረውን የኮቪድ-19 በሽታ በመቋቋም መልካም አፈፃፀም ካሳዩ ባንኮች አንዱ በመሆን በአፍሪካ ከሚገኙ 100 ምርጥ ባንኮች መካከል የ17ኛ፣ ከምስራቅ አፍሪካ ደግሞ 1ኛ ደረጃ በመያዝ አመቱን አጠናቋል፡፡(የኢት ንግድ ባንክ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top