Connect with us

በአዲስአበባ የትራፊክ አደጋ የሞት መጠን ቀነሰ

በአዲስአበባ የትራፊክ አደጋ የሞት መጠን ቀነሰ
TMA የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው

ዜና

በአዲስአበባ የትራፊክ አደጋ የሞት መጠን ቀነሰ

በአዲስአበባ የትራፊክ አደጋ የሞት መጠን ቀነሰ

በአዲስአበባ ከተማ በ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት በትራፊክ ግጭት የሞት መጠን በ 17 በመቶ ቀነሰ፡፡

ከሀምሌ 1/2012 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30/2013 ዓ.ም ባለው ስድስት ወራት በከተማዋ በትራፊክ ግጭት የተመዘገበው አደጋ ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ሞት 17 በመቶ በቁጥር የ39 ሰዎች ህይወትን ታድጓል፡፡

እንዲሁም ከባድ የአካል ጉዳት 14 በመቶ በቁጥር 144 ሰዎች ከጉዳት መታደግ ተችሏል፡፡

የ2013 ዓ.ም የ2ኛ ሩብ ዓመት የትራፊክ ግጭት ጉዳቶች ከመጀመሪያው ሩብ ዓመት ጋር ሲነፃፀር ደግሞ ሞት በቁጥር የ14 ሰዎች በመቶኛ 14 ፐርሰንት እንዲሁም ቀላል የአካል ጉዳት በቁጥር 20 እና በመቶኛ ስምንት በመቶኛ መቀነስ ተችሏል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ በመጨመር ላይ የሚገኘውን የትራፊክ ግጭት አደጋዎችና ጉዳት በከተማ ደረጃ መቀነስ የተቻለው የከተማዋ የመንገድ ደህንነት ስትራቴጂ ተነድፎ ተግባራዊ በመደረጉ ነው፡፡

በተለይ በከተማችን ከሚደርሱት የትራፊክ አደጋዎች 80 ከመቶ የሚሆኑት እግረኞች ላይ በመሆኑ ይህንን ባማከለ መልኩ አደጋ በሚበዛባቸው ዋና ዋና መንገዶች ላይ የምህንድስና ማሻሻያዎችን በማድረግ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በማከናወን እና በግንዛቤ የተደገፈ ቁልፍ የትራፊክ ህጎችን የማስከበር ስራን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ማከናወኑ ለመጣው ውጤት ጉልህ ሚና ነበራቸው፡፡

የእግረኞችን ደህንነት ለማሻሻል የተከናወኑ ተግባራት የትራፊክ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች ትግበራ፤ የእግረኛ መሠረተ ልማት ማሻሻያ እና ጥበቃ፤ የተለያዩ መጋጣሚያዎች ማሻሻያ እና የእግረኞች ትራፊክ መብራት ትግበራ፣ አደባባዮችን ወደ ትራፊክ መብራት መቀየር፣ የፍጥነት ማብረጃ እና መቀነሻ ጉብታዎች ግንባታ፣ የትራፊክ ምልክቶች ተከላ እና እድሳት፣ የቦላርዶች ተከላ፣ የእግረኛ መከላከያ የብረት አጥሮች፣ የሌሊት እይታን የሚጨምሩ አንፀባራቂ ምልክቶች፣ ሴፍቲ ሮለር፣ የመንገድ ቀለም ቅቦች፣ ለነባር እና አዳዲስ የትራፊክ መብራቶች ጥገና እና የሰዓት ማሻሻያዎችን ማድረግ ተጠቃሾች ናቸው፡፡

በከተማዋ ለሚደርሱ የትራፊክ ግጭት መንስኤ ከሆኑት ከተፈቀደው የፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር አንዱ በመሆኑ በተደጋጋሚ ሞት ይደርስባቸው በነበሩ መንገዶች ላይ ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በመሆን የፍጥነት ቁጥጥር ስራ ተከናውኗል፡፡

በ2013 በጀት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት 49 ሺ 043 አሽከርካሪዎች ከተፈቀደው የፍጥነት ወሰን በላይ ሲያሽከረክሩ ተገኝተው የእርምት ርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡

ሌላው የሞተር ሳይክል የግጭት መከላከያ (ኮፊያ) ሄልሜት አጠቃቀም ቁጥጥር፣ የደህንነት ቀበቶ አጠቃቀም ቁጥጥር ፣ተንቀሳቃሽ ስልክ እያናገሩ ማሽከርከር ቁጥጥር፣ እና ሌሎች የመንገድ ትራፊክ ህጎች እና ደንቦችን ማስከበሩ በጥብቅ ተከናውኗል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የትራፊክ ፍሰቱን እና ደህነትን የሚያውኩ ድርጊቶች እና ቁሶችን ከመንገድ ላይ የማስነሳት ስራ እንዲሁም የፓርኪንግ አጠቃቀም ስርዓት እና አስተዳደርን ለማዘመን የክትትል እና የቁጥጥር ስራዎች በስፋት ተከናውነዋል፡፡

የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 395/2009 ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ በመደረጉ በደንቡ ድንጋጌ መሠረት የፖይንት ፔናሊት ተግባራዊ በመሆኑ በከተማዋ የትራፊክ ግጭት አደጋ በማድረስ በሰው ህይወት እና በአካል ላይ ጉዳት ያደረሱ 453 አሽከርካሪዎች፣ 526 አሽከርካሪዎች በተደጋጋሚ የትራፊክ ደንብ ጥሰት ጥፋቶችን በመፈጸም የተያዘባቸው ነጥብ ከ17 በመብለጡ የተሃድስ ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ ይገኛል፡፡

በዚህ ስራም አሽከርካሪዎች የፖይንት ፔናሊት ስርዓት በመጀመሩ አደጋ ላለማድረስ በጥንቃቄ እና በትኩረት እንዲያሽከረክሩ አድርጓል፡፡

አብዛኛውን ጊዜ አደጋ የሚያደርሱ በከተማዋ የምንቀሳቀሱ ሞተር ብስክሌቶችን በዘመናዊ መቆጣጠሪያና መከታተያ ሲስተም ጂፒ ኤስን በመጠቀም መቆጣጠር መጀመሩም በከተማዋ የሚደርሰውን አደጋ በመቀነስ ረገድ የራሱን አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የትራፊክ ቅጣት ክፍያን ዘመናዊ፣ ቀላል፣ ተደራሽ እና ቀልጣፋ ለማድግ በተሰራው ስራ በኤጀንሲው ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ብቻ ሲሰበሰብ የነበረውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በአራት የግል ባንኮች (አዋሽ፣ አቢሲኒያ፣ ዳሽን እና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንኮች) እንዲከፈል መደረጉ ጊዜንና ጥራትን በማስጠበቅ ተደራሽ ማድረግ ተችሏል፡፡

(መረጃው TMA የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top