Connect with us

የማውቀው እውነት …

የማውቀው እውነት ...
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የማውቀው እውነት …

የማውቀው እውነት …

(ኤርሚያስ በጋሻው)

ከሶስት ዓመት በላይ በ#ebs ቴለቪዥን ጣቢያ በጋዜጠኝነት እየሰራሁ እገኛለሁ ።የኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ዕምነት ተከታይ ነኝ።የምሰራበት ጣቢያ በሃይማኖቴ ምክንያት ምንም አይነት ተጽዕኖ አድርጎብኝ አያውቅም ።በእኔ ላይ ብቻ ሳይሆን የትኛውንም ሃይማኖት የሚከተሉ ሰራተኞች ላይ በሃይማኖት መነሻ ተጽዕኖ አይደረግም ።የሚደረግበት ምክንያትም የለም።

በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተቋም ላይ እንደጣቢያ እንደውም የተሻለ እይታ ነው ያለዉ ።ከፕሮግራምና ዜና ዘገባ አንጻር የሰራቸውን እና እየሰራ የሚያገኛቸው ነገሮች ለተመልካች የተደበቀ አይደለም ።ከስሜት ወጥተን ነገሩን ለመመልከት ከሞከርን እንደ ንግድ ብሮድካስተር ጣቢያው በሚሊዮን የሚቆጠር ተከታይ ያላትን ግዙፍ የእምነት ተቋም ጸር ሆኖ መቆም አይችልም ።አልቆመምም።

እንደ ማንኛውም ገለልተኛ (secular ) የሚዲያ ተቋም ግን ከአለባበስ እስከ ይዘት ለየትኛውም የእምነት ተቋም ላለማድላት መጣር አለበት ።የጣቢያው የቀድሞ ሰራተኞች ከገለፁት ነገር ጋር በተያያዘ የማተብ ጉዳይ በebs ላይ አላግባብ መነጋገርያ እነዲሆን ወቀሳ እንዲነሳበት አደረገ እንጂ የትኛውም የአገር ውስጥዎ ሆነ የውጭ ገለልተኛ (secular )ሚዲያ ከአለባበስ እስከ ይዘት ገለልተኝነት ይጠብቃል ።

በአጭር ቋንቋ በተለይ ሴት አቅራቢዎች የተገላለጠ ልብስ ሲለብሱ የኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ መለያ የሆነውን ማተብ አያደርጉም ።የሌላ ሃይማኖት ተቋም መለያም አያደርጉም ።ለሁሉም አይነት የህበረተሰብ ክፍል ስለሚሰሩ(በበዓላት ጊዜ ከሚደረገው በስተቀር) አንዱን ነጥሎ የሚያንጸባርቅ ነገር ማድረግ የለባቸውም ።

ይህ የሚደረገው በተለየ ፍቅር ወይም ጥላቻ ሳይሆን ሙያዊ የዘርፉ መርህ ስለሆነ ነው።

….

ይህን የምለው እውነትን የመግለጽ ሃይማኖታዊ ሞራላዊ ሙያዊ ግዴታ ስላለብኝ ብቻ ነዉ ።

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top