Connect with us

ደብረ ብርሃን ዪኒቨርሲቲ  ለሃናፂ መቅደስ መጋቢ ተክለፃዲቅ ሸዋረጋ የክብር ዶክትሬት ሰጠ

ደብረ ብርሃን ዪኒቨርሲቲ ለሃናፂ መቅደስ መጋቢ ተክለፃዲቅ ሸዋረጋ የክብር ዶክትሬት ሰጠ
አብመድ

ዜና

ደብረ ብርሃን ዪኒቨርሲቲ  ለሃናፂ መቅደስ መጋቢ ተክለፃዲቅ ሸዋረጋ የክብር ዶክትሬት ሰጠ

ደብረ ብርሃን ዪኒቨርሲቲ  ለሃናፂ መቅደስ መጋቢ ተክለፃዲቅ ሸዋረጋ የክብር ዶክትሬት ሰጠ

መጋቢ ተክለፃዲቅ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላፍ፣  ለአካባቢው ማሕበረሰብ ብሎም ለሀገር ትልቅ ፋይዳ ያለው የመልካም ምግባር አራያ የሚሆን በኪነ ጥበብ፣ በኪነ ሕንጻ፣ በቱሪዝምና በማኅበረሰብ አገልግሎት ላበረከቱት አስተዋፅዖ ነው የክብር ዶክትሬት መሰጠታቸው የተገለፀው፡፡

የክብር ዶክትሬቱ ለዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያና ልዩ መሆኑም ተነስቷል፡፡ መጋቢ ተክለ ፃዲቅ ሸዋረጋ ትውልዳቸው በሰሜን ሸዋ ሰላ ድንጋይ አካባቢ ነው፡፡ እስከ ስድስተኛ ክፍል ድረስ ዘመናዊ ትምህርት ተምረዋል፡፡ 

ከዚያ በኋላ ዘመናዊ ትምህርታቸውን አቋርጠው  በመንፈሳዊ ትምህርት ያሬዳዊ ዜማና አቋቋም አጠናቅቀዋል፡፡ ያሬዳዊ ዜማውንና አቋቋሙን እንዳጠናቀቁ በጻድቃኔ ማርያም ገዳም ለ14 ዓመታት አገልግለዋል፡፡

የወጣትነት ጊዜያቸውን በመንፈሳዊ አገልግሎት ያሳለፉት መጋቢ ተክለፃዲቅ  በጎልማሳነት እድሜያቸው ከሰላ ድንጋይ ከተማ በስተ ምዕራብ በኩል የመስካበ ቅዱሳን መድኃኔዓለም  ፍልፍል ገዳም  አስራ ሁለት ሴትና አስራ ሁለት ወንድ ምዕምናንን በመያዝ ከአንድ ወጥ ዓለት  አንፀዋል፡፡

ሥራውንም ከ1998 እስከ 2000 ዓ.ም መሥራታቸው ተነግሯል፡፡ የመስካበ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ፍልፍል ዋሻ ቤተ ክርስቲያን ዘመናዊ የህንጻ ጥበብ የሚንፀባረቅበት፣ የአሁኑ ትውልድ ከቀደሙት ወላጆቹ ጥበብን፣ የሕይወት ልምድንና የሥራ ባሕልን በመቅሰም የተሻለ ሕይወት እንዲኖረው በማድረግ ትልቅ አስተዋፅዖ ያለው ነው ተብሏል፡፡

ትውልዱ ያለፈውን በጥበብ በመመርምር ዛሬን በጥበብ ለመኖርና ለነገውም በቂ ዝግጅት ለማድረግ የሚያገለግል ታላቅ ቅርስ ነው ተብሏል፡፡ ቅርሱ አዲስና የተሻለ ለመፍጠር መነሻ እንደሚሆንም ተመላክቷል፡፡ የቱሪስት መዳረሻ በመሆን የጎብኚዎችን ቀልብ በመሳብ ምጣኔ ሀብትን ከፍ ያደርጋልም ነው የተባለው፡፡

ፍልፍል ዋሻው ከዘመናዊ ምህንድስና አንፃር ሲታይ አንድ ሕንጻ ሲገነባ ሟሟላት የሚገባውን ሁሉ ያሟላ እንደሆነም ተነግሯል፡፡ የህንጻው ሠሪዎች መጋቢ ተክለፃዲቅና ሌሎች ረዳቶቻቸው የዘመናዊ ምህንድስና ባለቤት ሳይሆኑ የሠሩት መሆኑም ተመላክቷል፡፡ ሕንጻ ቤተክርስቲያኑ ከአሁን በፊት በኢትዮጵያ ለታነፁ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት በኢትዮጵያዊያን ስለመታነጻቸው ቋሚ ምስክር ነውም ተብሏል፡፡

ይህን ያደረጉትን ታላቅ ሰው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለሥራቸው ክብር የክብር ዶክትሬት ሰጥቷቸዋል፡፡

የክብር ዶክትሬት የተሰጣቸው ሃናፄ መቅደስ መጋቢ ተክለፃዲቅ ‹‹እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፣ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ፣ በውስጣችሁ ፍቅር ይሙላ ይላልና እግዚአብሔር››  ተዋደዱ ብለዋል፡፡ ተማሪዎችም ከአበባ ወደ ፍሬ ስለ ደረሳችሁ ደስ ይበላችሁ ነው ያሉት፡፡ ብዙ መከራ አልፋችሁ ለዚህ ስለበቃችሁም ደስ ይበላችሁ ብለዋቸዋል፡፡  አሁን ፍሬ እንዳፈራችሁ ሁሉ ነገም በምድር ላይ መልካም ፍሬ ማፍራት አለባችሁም  ነው ያሉት መጋቢ ተክለፃዲቅ፡፡

(አብመድ) ዘጋቢ፡-ታርቆ ክንዴ

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top