Connect with us

የሱዳን ወረራና ዘመን አይሽሬው ባንዳነት

የሱዳን ወረራና ዘመን አይሽሬው ባንዳነት
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የሱዳን ወረራና ዘመን አይሽሬው ባንዳነት

የሱዳን ወረራና ዘመን አይሽሬው ባንዳነት

(በፍቱን ታደሰ)

ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር ጥሳ ወረራ ከፈጸመች አራት ሳምንታትን አስቆጥራለች፡፡ ለወረራ ካደፋፈሯቸው ገፊ ምክንያቶች አንዱና ዋነኛው የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝቡ በትግራይ ከህወሓት ጋር የሚያካሂዱት የህግ ማስከበር ጦርነት አቅማቸውን አዳክሞታል የሚል ነው፡፡ 

ከዚህ በተጨማሪም ሃገራችን በአራቱም ማእዘኖች በከፍተኛ የውስጥ ችግር መወጠሯ ሱዳን ወረራ ለመፈጸሟ ተጨማሪ ድፍረት ሰጥቷል፡፡ 

በዚያ ላይ ደግሞ የግብፅ አይዞሽ ባይነትና ማደፋፈር ሲታከልበት የሱዳን ሚዲያዎች “ወታደሮቻችን ጥይት እየተኮሱ ሳይሆን ጥርሳቸውን እየፋቁ ኢትዮጵያ ለዘመናት የያዘችባቸውን መሬት ያስለቅቃሉ” እያሉ ሲፎክሩ ከርመዋል፡፡

የግብፅ ሚዲያዎች በተለይ ግብፃውያን የታሪክና የፖለቲካ ምሁራን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ትልቁ አጀንዳቸው ሱዳን በኢትዮጵያ መሬት ተወስዶባታል የሚል ነው፡፡ የሱዳን ድንበር ጎንደርን እንደሚያካትትና ከዚያም አልፎ የኤርትራ ቆላማው ክፍል በጠቅላላ የሱዳን እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ሰሞኑን ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ መተከል ላይ የተፈጠረውን አለመረጋጋት እንደ ግጭት ማቀጣጠያ በመጠቀም ቤንሻንጉል የሱዳን ግዛት ነው ማለት ጀምረዋል፡፡

ህወሓት ቤንሻንጉል ውስጥ በአምሳሏ ከቀረጸቻቸው የጉሙዝ ተወላጆች አንዱ የሆነው የሱፍ ሃሚድ ቤንሻንጉል የሱዳን ግዛት ነው የሚለውን አጀንዳ በተለይ በኦሮሞ ሚዲያ ኔት ወርክ /OMN/ ቴሌቪዥን እየቀረበ መስበክ ጀምሯል፡፡ የሱፍ ሃሚድን ህወሓት በየመን የኢትዮጵያ አምባሳደር አድርጋ ሾማው ነበር፡፡ 

የሚገርመው ስለዚህ ጉዳይ የምትሞግተው ግብጽ እንጂ ሱዳን በመንግስት ደረጃ እንዲህ ያለ አቋም ስታራምድ አይታይም፡፡ ፈርኦኖቹ በቀደዱት ቦይ እየፈሰሱ ያሉት ሱዳናውያን ብቻ ሳይሆኑ አንዳንድ ኢትዮጵያውያንም ተዋናይ ሆነው መገኘታቸው እየደነቀን ነው፡፡ በማህበራዊ ድረገጽ ላይ በኢትዮጵያውያን እየተጻፉ ያሉ ነገሮችን ስንመለከት ዘመን አይሽሬውን የባንዳነት ታሪክ በደማቁ ተጽፎ እናገኘዋለን፡፡ 

ስለሃገር የተገጠሙ ግጥሞችን ይዘታቸውን በመቀየር ለምሳሌ “ጎንደር፣ ጎንደር የጀግኖች ሃገር የሚለውን” ቀይረው “ጎንደር፣ ጎንደር የሱዳን ሃገር” እያሉ ማዜም ጀምረዋል፡፡ ታሪክ እራሱን ይደግማል ያለው ማን ነበር?

ይህ የዛሬው የባንዳነት ሁኔታ በ የ1928 ዓ.ም የኢጣሊያ ወረራ ወቅት የሆነውን ያስታውሰናል፡፡ በወቅቱ የ28 ዓመት ወጣት የነበረው የራስ ጉግሳ ልጅ ደጃዝማች ሃይለሥላሴ ጉግሳ ጣልያን አድዋን ሲቆጣጠር ደጃዝማቹ አዲግራትን ለማስያዝ በጄኔራል ሳንቲኒ በኩል ከሞሶሎኒ ጋር ይደራደር ነበር፡፡ 

ወጣቱ ደጃዝማች በወቅቱ ምንም አይነት የፖለቲካ ችግር አልነበረበትም፡፡ የገንዘብ ፍቅሩ ከፍተኛ ስለነበር ከጣልያን መንግስት በቀረበለት ከፍተኛ የገንዘብ ስጦታ ሃገሩን ለጣሊያን ወታደሮች አስረክቧል፡፡ ዛሬም የዘመናችን ደጃዝማች ሃይለሥላሴዎች ሃገራችንን ለሱዳን ለመሸጥ እላይና ታች ሲሉ እያየን ነው፡፡

በዚህ አጋጣሚ ከግብፅና ከሌሎች ኢትዮጵያ ህልውናዋ እንዲከስም ከሚፈልጉ ኃይሎች የተመደበውን ሃብት ለመቋደስና ሚሊየነር ለመሆን ያሰፈሰፉ ባንዳዎች ነጭ ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ህዝብን እያሸበሩ ይገኛሉ፡፡  ፊት ለፊት ከመጡት ወራሪ ጠላቶቻችን ባልተናነሰ ሁኔታ መንግስት ባንዳዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ይኖርበታል፡፡

የሱዳንና የኢትዮጵያ ጉዳይ በዲፕሎማሲና በውይይት መፍትሄ የማግኘት እድሉ እየጠበበ ነው የመጣው፡፡ ሁኔታው መሻሻል ካልቻለና ወደ ጦርነት የሚሸጋገር ከሆነ ኢትዮጵያውያን የሃገራችንን ህልውና ለማስቀጠል አንድነታችንን አጠንክረን መቆም ይኖርብናል፡፡ 

ህወሓት አሰልጥኗቸው ማይ ካድራ ላይ በንፁሃን ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ ፈጽመው ወደ ሱዳን የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን ከሱዳን ጎን ለመሰለፍ መዘጋጀታቸው በተለያዩ ሚዲያዎች እየተዘገበ ነው፡፡ የህወሓት ነባር ታጋይ የነበሩ ሰዎችም ከአሜሪካ ሱዳን ድረስ ሄደው ለዚሁ አላማ አዘጋጅተዋቸው እንደሄዱ ተሰምቷል፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top