Connect with us

ሰው ሀገር ሊያፈርስ ዱር ገብቶ፤ ቋጥኝ ላይ ያድራል፣

ሰው ሀገር ሊያፈርስ ዱር ገብቶ፤ ቋጥኝ ላይ ያድራል፣
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ሰው ሀገር ሊያፈርስ ዱር ገብቶ፤ ቋጥኝ ላይ ያድራል፣

ሰው ሀገር ሊያፈርስ ዱር ገብቶ፤ ቋጥኝ ላይ ያድራል፣

~ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዓለም ታላቅ እንግዳ ይዞ ሀገር ሊሰራ ጫካ ያድራል፣

~ ኮይሻን ሊጎበኙ የዱባይን ታላቅ ሰው ይዘው ጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ ያደሩት ዶክተር ዐብይ ወደ መናገሻ ከተማዋ ተመልሰዋል፣

(ፍቅሩ ዳሳለኝ)

ኢትዮጵያን ለማፍረስ በየዋሻው ስለተሸሸገው፣ የደሃ ልጅ አስጨርሶ ዱር ስለገባው ጢም አጎፋሪ ለምን እናወራለን? ሀገር እሰራለሁ ብሎ ጫካ ስለሚያድረው የኢትዮጵያ መሪ ብናወራስ፤ እሱ ዐብይ አህመድ ነው፡፡ 

ዶክተር ዐብይ የትናንትናዋን ምሽት በማራኪው የኮይሻ ሥነ ምህዳር አሳለፉ፡፡፡ ባይነኩላር ይዘው የዱር ውበት ተመለከቱ፤ የኮንታ ሰው ወደ ሸገር ቤተ መንግስታቸው ይሄዳሉ ብሎ ሲጠብቅ ሰውዬው ውቡ ዱር ዳርቻ አደሩ፡፡

ገና ሲመለከቱት በፍቅር ወድቀዋል፤ ፓርላማ ላይ ተአምር ነው ሲሉ መሰከሩ፡፡ ከዚያን ቀን ጀምሮ የእረፍት ጊዜያቸውን ጨበራ ጩርጩራን ስለመስራት እንቅልፍ አጡ፡፡ ወደ ዱር የሚሮጡ ሆኑ፡፡ በተፈጥሮው ፍቅር ተለክፈዋል የትውልድ ቀዬቸው አይደለም፤ ሀገራቸው ነው፡፡ ገበታ ብለው በሀብታችን ከገበታችን ምግብ እንዳይጠፋ ያቀዱት እቅድ ኮይሻን ለመልካም ነገር አጨው፡፡

ዶክተር ዐብይ ኮይሻ የገቡት ብቻቸውን አይደለም፡፡ ያደርኩበት እደር ያሉትን የዱባይ ታላቅ ሰው ይዘው ነው፡፡ ኮይሻ የሚባለው የገበታ ፕሮጀክት በዋናነት ጨበራ ጩርጬራ ብሔራዊ ፓርክን መሰረት ያደርጋል፡፡ በኮንታና በዳውሮ መካከል የሚገኝ ተደብቆ የኖረ የተፈጥሮ መስህብ ነው፡፡

የግቤ ሦስትና አራት የሃይል ማመንጫ ግድቦች የሚፈጥሩትን ሰው ሰራሽ ሐይቅ ለቱሪዝም መስህብነት የሚያውለው ይህ ፕሮጀክት እንጦጦና ሸገር ከማለቁ ቀድሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ልብ የሰረቀ ነው፡፡ የንጉሥ ሀላላን ረዥም ካብ ጭምር የመዳረሻ ልማቱ አካል ያደረገው ይህ ስራ በኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጥብቅ ስፍራ በከፍተኛ በጀት የተሰራ የመጀመሪያው የሀገራችን መስህብ ያደርገዋል፡፡

ራሳቸው ብቅ እያሉ የሚከታተሉት ከኮይሻ ገበታ ፕሮጀክት በጥሩ ሁኔታ እየተሰራ ነው፡፡ ድምጽ አጥፍቶ ማልማት ብቻ ሳይሆን ድምጽ አጥፍቶ ዱር ማደርንም ጀምረዋል፡፡ ታላቅ ባለሃብት ይዘው በኮይሻ ያደሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ብዙ የሀገር ውስጥና የውጪ ባለሃብቶች በአካባቢው እንዲያለሙ ሲጋብዙ ከርመዋል፡፡

ትናንት በዝሆኖቹ ማዶ ይዘውት ያደሩት እንግዳ ለጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክና ለኮይሻ ኢንቨስትመንት ምን ትርፍ እንደሚኖረው ወቅቱ ሲደርስ እናያለን፡፡ እንዲህ ያለውን ተግባር ሀገር ለማፍረስ ጫካ ከተገባው በላይ ደጋግመን ብናወራውና ሀገር ለመስራት ዱር ማደርን ብናከብረው ዛሬ ሆቴል አድሮ ማልማት ዳገት የሆነበትን ብዙ ሹም ብዙ ያስተምራል፡፡

ገበታ ለሀገር የተረሱትን ቀጠናዎች ያስታወሰ የልማት እቅድ ነው፡፡፡ ወንጪን ያበለጽጋል፤ ጎርጎራን ያለመልማል፡፡ ሀገር በየቀኑ ካልለማ በየቀኑ ይሞታል፡፡ ከብዙ ችግሮቻችን ጋር የቀደሙት መሪዎች ምቹ ያልሆነ ሁኔታን ተጋፍጠው ያለሙትን ልማት ዛሬ እናጣጥመዋለን፡፡ ገበታው ገበታችን ነው የምንለው ለዚህ ነው፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top