Connect with us

እንግዳ የናፈቃት ላል ይበላ

እንግዳ የናፈቃት ላል ይበላ
አብመድ

ነፃ ሃሳብ

እንግዳ የናፈቃት ላል ይበላ

እንግዳ የናፈቃት ላል ይበላ

ቅድስቲቷን ከተማ የዓለም ዐይኖች ማረፊያ፣ እግሮች ሁሉ ሊደርሱባት የሚመኟት ናት። በኢትዮጵያ የነጮች መኖሪያ ደሴት እስክትመስል ድረስ ነጮች ይመላለሱባታል። ረዘም ላለ ጊዜ መቆየትም ይመርጣሉ። በድንቅ ጥበብ የተሰሩትን ውብ አብያተክርስቲያናት፣ ሃይማኖታዊ ስርዓትና የከተማዋን እንግዳ ተቀባይነት ያዩ እንግዶች ሁሉ ደጋግመው መምጣትም ይፈልጋሉ።

ቅድስቲቷ ከተማ ላል ይበላ የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ ወዲህ እንደወትሮው ሁሉ እንግዶቿን ናፍቃለች። እንግዶቿም ላል ይበላን ናፍቀዋል። አብዛኛውን ኑሯቸውን በቱሪዝም የሚመሩት የላል ይበላ ከተማ ነዋሪዎችም በከተማዋ ጭር ማለት ተጎድተዋል። ተሪዝም ሲሰጣቸው የነበውን ሀብትም መተኪያ አጥተዋል። ሆቴሎች ስራ አቁመዋል። አስጎብኚዎች ለችግር ተጋልጠዋል።

የአጎቱን ሆቴል በመወከል የሚመራው ብርሃን ተስፋዬ አሁን ላይ ጎብኝ ስለሌለ ምንም አይነት ሥራ የለም ነው ያለው። የኮሮና ቫይረስ ከመከሰቱ በፊት የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ወደከተማዋ በብዛት እንደሚመጡና እነርሱም በሚገባ ይጠቀሙ እንደነበር ነው የተናገረው። በተለይም የልደት እና የጥምቀት ሰሞን ላል ይበላ የጎብኚዎች ፍሰት እንደሚጨምር ገልጿል። ጎብኚ በማይበዛባቸው ወራትም ቢሆንም ጥሩ እንቅስቃሴ እንደነበር ነው ያስታወሰው።

ከኮሮና ቫይረስ ወዲህ ግን ላል ይበላ በልደት በዓል እንኳን የውጭ ሀገር ጎብኚ ናፍቋት ነው ያሳለፈችው። የሠራተኛ ደሞዝ ለመክፈል እንደተቸገሩም ነግሮናል። የከተማዋ የቱሪዝም እንቅስቃሴ ሲዳከም እንግዶች ጥንቃቄ በተመላበት መንገድ እንዲገቡና እንዲንቀሳቀሱ የሚደረግበት ሁኔታ እንደሚመቻችም ጠይቀው እንደነበርም ነግሮናል።

በኢትዮጵያ ተጥሎ የነበረው አዋጅ ከተነሳ ወዲህ አንዳንድ ቱሪስቶች መምጣት ቢጀምሩም የላል ይበላ የቱሪዝም እንቅስቃሴ ግን መነቃቃት አልቻለም ነው ያለው።

የላል ይበላ አስጎብኚ እያያው ባዬ አካባቢው ከባድ ጊዜ እያሳለፈ ነው ብሏል። <<ለእኔ በእድሜዬ መጥፎው ጊዜ ይሄ ነው>> ብሎናል። በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው የልደት በዓል እንደለመዱት ባለመሆኑ ችግራቸው ሊቀጥል እንደሚችል ነው ስጋቱን የነገረን። ቱሪዝሙ ፍሰት መቀዛቀዙ ከፍተኛ መደናገጥ ፈጥሮባቸው እንደነበር ነው የተናገረው። በሕይወቱ እንዲህ አይነት ነገር ይፈጠራል ብሎ አስቦ እንደማያውቅ ነው የነገረን። የላል ይበላ ከተማ በቱሪዝም ዘርፉ ዳግም እንድትነቃቃ የባሕልና ቱሪዝም እንዲሰራም ጠይቋል።

የላል ይበላ ከተማ አስተዳደር ባሕልና ቱሪዝም ሰፖርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ መሪጌታ መልካሙ ዓለሙ የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ እስከተከሰተበት መጋቢት 2012 ዓ.ም ድረስ በከተማዋ ከፍተኛ የሆነ የቱሪስት ፍሰት እንደነበር ነው የተናገሩት። በ2012ዓ.ም 55 ሺህ የውጭ ሀገር ጎብኚ ይጎብኛል ተብሎ እቅድ ተይዞ እስከ መጋቢት ድረስ ብቻ 65 ሺህ የውጭ ሀገር ጎብኚ እንደነበር ተናግረዋል።

በላል ይበላ ከሀገር ውስጥ ይልቅ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች እንደሚበዙ የተናገሩት ኃላፊው የቱሪዝም ዘርፍ እንቅስቃሴ ለረጅም ወራት ሙሉ ለሙሉ ዝግ ሆኖ መቆየቱንም አስታውሰዋል።

ኢትዮጵያ የተዘጉ የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲከፈቱ ካደረገች በኋላ አንዳንድ ቱሪስቶች መምጣት ጀምረው እንደነበርም ተናግረዋል።

በከተማዋ 195 አስጎብኚዎች፣ 225 ድጋፍ ሰጪ አስጎብኚዎች እንዳሉ የተናገሩት መሪጌታ መልካሙ በቱሪዝሙ የደረሰው ጫና ከፍተኛ ነው ብለዋል። 47 በሚደርሱ የከተማዋ ሆቴሎች የሚሰሩ ሠራተኞችም ለችግር መዳረጋቸውን ነው የተናገሩት።

በቱሪዝም ገቢ የሚደጎሙት የላል ይበላ አብያተክርስቲያናት አገልጋይ ካሕናት ጭምር ተጎጂዎች መሆናቸውን ነው የነገሩን።

ሆቴሎች ሠራተኛ እንዳያሰናብቱ ብድር የሚመልሱበት ጊዜ እንዲራዘምና በዝቅተኛ ወለድ ብድር በማመቻቸት ሥራ መስራታቸውንም ገልፀዋል። የተሠራው ሥራ ግን በቂና የተሳበውን ያክል ፍሬ አለማምጣቱን ነው የተናገሩት።

የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ኂሩት ካሳው በዘንድሮው የልደት በዓል በላል ይበላ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዜጎች መምጣታቸውን ተናግረዋል። ከውጭ ሀገር የመጡ የበዓሉ ታዳሚዎች ግን አናሳ መሆናቸውን አንስተዋል። በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በላል ይበላ የቱሪዝም እንቅስቃሴው ቆሞ መቆየቱንም አስታውሰዋል።

የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ፈንታ ማንደፍሮ በላል ይበላ ያለውን የጎብኚ መቀዛቀዝና የደረሰውን ችግር ለመፍታት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ማሳሰባቸው ይታወሳል።

(ታርቆ ክንዴ – አብመድ)

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top