Connect with us

በምኞታቸው ኢትዮጵያንና አንድነቷን የደመሰሱት ከቅዠታቸው ሳይነቁ ተደመሰሱ፤

በምኞታቸው ኢትዮጵያንና አንድነቷን የደመሰሱት ከቅዠታቸው ሳይነቁ ተደመሰሱ፤ ያ ሁሉ ዛቻ መጨረሻው በየተራ ቂሊንጦ መውረድ ሆነ፤ "አትታበዩ" እንዲል መጽሐፉ
ነፍስሔር ሴኮቱሬ ጌታቸው

ነፃ ሃሳብ

በምኞታቸው ኢትዮጵያንና አንድነቷን የደመሰሱት ከቅዠታቸው ሳይነቁ ተደመሰሱ፤

በምኞታቸው ኢትዮጵያንና አንድነቷን የደመሰሱት ከቅዠታቸው ሳይነቁ ተደመሰሱ፤

ያ ሁሉ ዛቻ መጨረሻው በየተራ ቂሊንጦ መውረድ ሆነ፤ “አትታበዩ” እንዲል መጽሐፉ

(ስናፍቅሽ አዲስ)

ትዕቢት መጥፎ ነው፡፡ መጽሐፉም ቢሆን አትታበዩ በኩራትም አትናገሩ ይላልና፡፡ በየስፍራው ሲዝቱ የከረሙት ወንበዴዎች ከየስፍራው እየተለቀሙ ነው፡፡ በምኞታቸው ኢትዮጵያንና አንድነቷን ደምስሰውት ነበር፡፡ ምኞታቸው እውን አልሆነም፡፡ እውን የሆነው ከየጉሮኖው መለቀማቸው ነው፡፡

መጨረሻቸው እንዲህ ሊሆን የብዙ ንጹሃን ህይወት ተመሳቀለ፡፡ ሀገር ወደመ፡፡ ያ ምስኪን ህዝብ አገኘሁ ያለውን ብርቅ ሰላም ነጠቁት፡፡ ያለ እኛ ትግራይ አትኖርም በሚል ጭካኔያቸው በአንቡላንስ ተኩስ ከፍተው ሲበረታ ጥለው ጠፉ፡፡ በአርባ ደቂቃ አመድ አደረግነው ያሉት የሀገር ክብር ከነታሪካቸው አመድ አደረጋቸው፡፡

አቶ ሴኮቱሬ ምን አስበው እንዲህ ያለው መዓት ውስጥ እንደገቡ ለመገመት እቸገራለሁ፡፡ ዘርን አስቀይሮ፣ ሀገርን አስጠልቶ፣ ወንበዴን አስጠግቶ፣ ታሪክ አልባ ሞት መሞት ክብሩስ ለማን ነው?

ትናንት የገና ስጦታ ከመከላከያ ሠራዊት ቀርቦልናል፡፡ የሀገራችን ጠላቶች የሆኑት አኩራፊ ፖለቲከኞች በሚጠሏት ሀገር ሠራዊት እጅ ገብተዋል፡፡ መግለጫውን የሰጡት የሀገር መከላከያ ጀኔራል የትግራይ ህዝብ ምግብና ውሃ ሳይቀር እየከለከለ ያሉበትን እየጠቆመ ከየስራቸው እንዲወጡ እንዳደረጋቸው ገልጸው ለቀሪዎቹም ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከመደምሰሳቸውም ሆነ በስተርጅና ማረሚያ ቤት ከመንከራተታቸው እኛ አንዳች ጉዳይ የለንም፡፡ ይህንን ያደረሰባቸው ትምክህትና ጥጋብ ነው፡፡ ዘርፎ በቃኝ ያለ ማለት ውጤት ለዚህ አብቅቷቸዋል፡፡ የናቁት ህዝብና ሀገር ከእግሩ ጫማ በታች አውሏቸዋል፡፡

ሰዎቹ በትግራይ ህዝብ ላይ ያደረሱትን በደል ለተመለከተ ሌላውን ህዝብማ ምረውታል፡፡ በገዛ ወገኖቹ ወንድሞቹ እህቶቼና እናት አባቱ ላይ እንዲህ ያለ ጭካኔ የሚፈጽም ነጻ አውጪ በዓለም ታሪክ ታይቶ አይታወቅም፡፡ አሁን ያ ሁሉ ዛቻ በየተራ ወደ ቂሊንጦ በመውረድ እያበቃ ነው፡፡

ፎቶ:- ነፍስሔር ሴኮቱሬ ጌታቸው

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top