Connect with us

ለሥራ ፈጣሪዎች እጅግ ጠቃሚ መረጃ!!

ለሥራ_ፈጣሪዎች እጅግ ጠቃሚ መረጃ!!
የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን

ዜና

ለሥራ ፈጣሪዎች እጅግ ጠቃሚ መረጃ!!

#ለሥራ_ፈጣሪዎች እጅግ ጠቃሚ መረጃ!!

የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን በቀጣይ ሦስት ዓመታት 200 ከፍተኛ የማደግ ብቃት ያላቸው የንግድ ፈጠራ ሀሳቦችን ለማብቃት  ዓላማው ያደረገ አገር አቀፍ የሥራ ፈጠራ ሀሳብ ውድድር መርሃግብር በማስተርካርድ ፋውንዴሽን አጋርነት አዘጋጀ፡፡

በውድድሩ ማብሰሪያ ወቅት እንደተገለጸው ብሩህ የሥራ ፈጠራ ሀሳቦች ውድድር  በሀገራችን በተለያዩ ዘርፎች የተለያዩ  ቁልፍ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ አዳዲስ ሀሳቦችን የሚያፈልቁና ለብዙ ዜጎች የሥራ ዕድል  የሚፈጥሩ ወጣቶችን ለማበረታታትና ዕድል ለመስጠት የተዘጋጀ ዓመታዊ ውድድር ነው።

መርሃ ግብሩ በወጣቶች የሚመሩ ኢንተርፕራይዞችን ለመፍጠርና ለማብቃት ለሚቀጥሉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት የሚቀጥል ሲሆን የስልጠና፣ የመነሻ ገንዘብና ጠንካራ የንግድ ልማት አገልግሎት በመስጠት የበቁ እንዲሆኑ የማድረግ ዓላማ ያነገበ ነው። በተጨማሪም ከ5-10 ዓመታት ውስጥ አድገው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚሆኑና ኢትዮጵያን የሚያስጠሩ  ድርጅቶች ሊመሰርቱ የሚችሉ፣ ለብዙዎች  የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ እንዲሁም ለሌሎች ተምሳሌት የሚሆኑ የንግድ ፈጠራ ሀሳብ ያላቸውን ወጣቶች ለማፍራት  ነው።

ውድድሩ የሀሳቦች እንደመሆኑ መጠን የማሰልጠን፣ የመሸለምና የማብቃት ሶስት ደረጃዎች ይኖሩታል። በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታትም 500 ሀሳቦችን በመመልመል ልዩ ልዩ እውቀትና ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች ለአንድ ወር በአንድ ቦታ በማሰልጠንና በማወዳደር በውድድሩ መስፈርት መሰረትም አሸናፊ ለሚሆኑት 300 ሀሳቦች የሥራ ማስጀመሪያ ማበረታቻ ሽልማትን ይሰጣል። ከተሸለሙት 300 ሀሳቦች 200 ወደ ንግድ ሀሳብ ማጎልበቻ ፕሮግራም (Acceleration) ይገባሉ። በዚህ ውድድር የሚበለጽጉ ጀማሪ የንግድ ሀሳቦችን በቀጥታ የንግድ ልማት አገልግሎት ድጋፍ ከሀሳብ ማጎልበት እስከ ማቋቋም ድረስ ይሰጣቸዋል። የፉክክር መንፈስ በማሳደርም የሚተገበሩ እና ወደ ገበያ ዘልቀው ሊገቡ የሚችሉ እንዲሁም በትንሽ ጊዜ ውስጥ ገቢን የሚያስገኙ ድርጅቶችን ይፈጥራሉ፡፡

ለዚህ ውድድር አመልካቾችን የመሰብሰብ ሥራ በሁሉም የአገራችን ክፍሎች የሚከናወን ሲሆን ቀጣይ ውድድሩና የስልጠናውና የማብቃት ፕሮግራሞች በማዕከላዊነት በአዲስ አበባ ይካሄዳሉ።

በ2013 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ዙር 50 የንግድ ሀሳቦች ሰልጥነውና ተወዳድረው 30 የሚሸለሙ ሲሆን፤ 20 ደግሞ  ወደ ማጎልበቻ ፕሮግራሙ (Acceleration Program) የሚገቡ ይሆናል። በተቀመጠው መርሃ ግብር የመጀመሪያው ዓመት ውድድር ምዝገባ ከጥር 1 እስከ ጥር 30/2013 ዓ.ም www.bruh-et.com የማመልከቻ ቅፅ በመሙላት ወይም ማመልከቻቸውን በአካል በአቅራቢያቸው ባለ የከተማ የሥራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ በማስገባት ማመልከት ይችላሉ።

የሀሳብ አመንጪዎች ኢትዮጵያዊያን መሆን አለባቸው። የሚወዳደሩበት የንግድ ኃሳብም በኢትዮጵያ ውስጥ ተፈጻሚ ለመሆን መታቀድ ይኖርበታል። አመልካቾች ከ15-29 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ መሆን አለባቸው። የሚወዳደሩበት ሀሳብ በንግድ የተመዘገበና ፍቃድ ያለው ከሆነ ንግዱ ከተመዘገበ ከሁለት ዓመት ያልበለጠው መሆን አለበት። በተጨማሪም ሴቶች ፣ አካል ጉዳተኛ ወጣቶች ፣ በሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ እና መጠለያ አልባ ወጣቶች እንዲያመለክቱ በጣም ይበረታታሉ።

የውድድሩ ዋና ዋና ክፍሎች (ስልጠናና የመድረክ ፉክክሮች) በቪዲዮ ተቀርጸው በቴሌቪዥን ለእይታ ይቀርባሉ። ይህም የተወዳዳሪዎች ጉዞና ፈተና ላይ የሚያተኩር ሲሆን ለሌሎች ወጣቶች መማሪያና መነቃቂያ ይሆናል።

ብሩህ የፈጠራ ሀሳቦች ውድድር በኮሚሽኑ፣ በማስተርካርድ ፋውንዴሽን፣ በከተሞች ሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲና በክልሎች የሥራ ዕድል ፈጠራ አስፈጻሚ አካላት በጋራ የሚተገበር ነው፡፡(የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን)

 

Continue Reading
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top