Connect with us

የኢትዮጵያ አብዛኞቹ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከታህሳስ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮሳት ብቻ ይሰራጫሉ

የኢትዮጵያ አብዛኞቹ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከታህሳስ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮሳት ብቻ ይሰራጫሉ
Photo: Social media

ዜና

የኢትዮጵያ አብዛኞቹ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከታህሳስ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮሳት ብቻ ይሰራጫሉ

የኢትዮጵያ አብዛኞቹ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከታህሳስ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮሳት ብቻ ይሰራጫሉ

የኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ተመልካቾች አብዛኛዎቹን ተወዳጅ ጣቢያዎቸ ከታህሳስ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በ57 ዲግሪ ምስራቅ በኢትዮሳት ላይ ብቻ ያገኛሉ፡ ፡ ማክሰኞ ታህሳስ 6 ቅም 2013 ዓም በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ መንግስት የተሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫ ተከትሎ የቴሌቪዥን ተመልካቾች ኢትዮሳትን ለማግኘት ባቅራቢያቸው የሚገኙ የሳተላይት ዲሽ ቴክኒሻኖችን በመጥራት የሳተላይት ዲሻቸውን ማዞር ይኖርባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን (ኢብባ) እና የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ መንግስትን፥ የህዝብ እና የግል ብሮድካስተሮችን በመወከል ዓለም አቀፍ የይዘት ግንኙነት አገልግሎት አቅርቦት ቀዳሚ ስፍራ ከሚይዘው ኤስ.ኢ.ኤስ ጋር የተፈራረሙት የአጋርነት ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያዊ ይዘት ያላችው ፕሮግራሞች በአንድ የቴሌቪዥን ሰፈር በቋሚነት መገኘትና መጠናከር በሃገሪቱ አዲስ ምዕራፍ መጀመሩን አብስሯል፡፡

የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውና በኤን.ኤስ.ኤስ-12 ሳተላይት የሚስራጨው ኢትዮሳት ነፃ የቴሌቪዥን አገልግሎት (FT A) መድረክ ነው ፡፡ ኢትዮሳት በጥቅምት ወር 2011 በኢትዮጵያ ብሮድካስተሮች ዘርፍ ማህበር፣ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) እና በኤስኢኤስ አማካኝነት ስራውን ያስጀመረ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ለማጠናከርና ተመልካቾች ቁጥራቸው ከፍ ያለ የውጪ ጣቢያዎቸ መካከል ሳይማስኑ በአንድ ቦታ ከአንድ ምሕዋር እንዲያሰራጩ ለማስቻል የተደረገ ስምምነት ነበር፡፡

የብሮደካስት ባለስልጣን፥ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና ኤስ.ኢ.ኤስ በጋራ በመሆን በ’ኢሊቬት’ ዓለማቀፍ የሳተላይት ዲሽ ቴክኒሻኖች ስልጠና 20 ሺህ ወጣቶችን በማሰልጠን በመላ ሃገሪቱ ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ ይገኛል፡፡ ተመልካቾች ኢትዮሳትን ለማግኘት ዲሻቸውን በቀላሉ ወደ ኤን.ኤስ.ኤስ -12 በማዞር ወይም በአካባቢያቸው የሚገኙ የሳተላይት ዲሽ ቴክኒሻኖች በመጥራት እንዲያዞሩላቸው ማድረግ የሚችሉ ከመሆናቸውም በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት ዲሽ ያላቸው ሁሉም የቴሌቪዥን ባለቤቶቸ ባላችው ሪሲቨር የኢትዮሳትን ማግኝት ስለሚችሉ አዲስ የ Set-Top Box (S TB) ወይም አንቴና መግዛት አያስፈልጋቸውም፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ድንቁ ሲናገሩ “አብዛኛዎቹን የኢትዮጵያ የሳተላይት የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ወደ አንድ ቦታ በማዛወር የሀገርን ኢኮኖሚ የሚጠቅምና በእርግጥም ኢትዮጵያዊ ብቻ የቴሌቪዥን አቅርቦትን ፈጥረናል። ከተለያዩ

የብሮድካስቲንግ ማህበራት እና ከ SES ጋር በመሆን በመላ አገሪቱ የሚገኙ ሁሉም የቴሌቪዥን ባለቤት ኢትዮጵያውያን ጥራት ያለው ይዘት ማግኘታቸውን እንዲቀጥሉ እስከ ወሩ መጨረሻ ድረስ የሳተላይት አቅጣጫ እንዲያስተካክሉ ለማገዝ እየሰራን እንገኛለን” ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ ቲቁ በበኩላቸው “ከኤስ.ኢ.ኤስ ጋር በኢትዮሳት ላይ ሙሉ በሙሉ አዲስ የቴሌቪዥን ልምድን የሚያመጣ ስትራቴጂካዊ ትብብር ለማድረግ በመቻላችን ደስታ ይሰማናል።” ብለዋል ፡፡ “ይህ ትብብር በተጨማሪ በኢትዮጵያ ያለውን የህዋ ዘርፍ ለመደገፍ ያለንን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ሲሆን ይህ ለኢትዮጵያውያን በልዩነት የቀረበው የቴሌቪዥን መድረክ ለኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ ብሩህ ተስፋን እንደሚጭር እምነት አለን” ሲሉም አክልዋል፡፡

የኤስኢኤስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ስቲቭ ኮላር በበኩላችው “ኤስ.ኢ.ኤስ እንደዚህ ባለ ላቅ ያለ ፕሮጀክት ውስጥ ወሳኝ ሚና በመጫወቱ ኩራት ይሰማዋል ፣ ቀሪ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ወደ ኢትዮሳት የሚያደርጉት ዝውውር ያለ ምንም ችግር እንዲካሄድ በቁርጠኛ እንሰራለን፡፡ ሽግግሩን ውጤታማ ለማድርግ እያንዳንዱን የቴሌቪዥን ቤት ጥራት ያለው የዲሽ ማዞር አገልግሎት እንዲያገኝ  የሳተላይት ገጠማ ሥልጠናው አጠናክሮ በማስቀጠል እና ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት የተመልካቾችን እርካታ ለማስጠበቅ እንሰራለን ” ብለዋል፡፡

ኢትዮሳት በአሁኑ ጊዜ 65 ቻናሎችን በነፃ ያቀርባል ፣ ከእነዚህ 16ቱ ቻናሎች በከፍተኛ ጥራት (HD) ያላቸው ሲሆኑ ከታህሳስ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮሳት ላይ ብቻ የሚገኙ ይሆናል፡

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top