Connect with us

ሀመር ከሠርጉ ቤት፤ ቡስካ ተራራ ሥር

ሀመር ከሠርጉ ቤት፤ ቡስካ ተራራ ሥር
ሄኖክ ስዩም

ነፃ ሃሳብ

ሀመር ከሠርጉ ቤት፤ ቡስካ ተራራ ሥር

ሀመር ከሠርጉ ቤት፤ ቡስካ ተራራ ሥር

(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም በሀመር ያደረገውን ቆይታ በተከታታይ እየተረከልን ነው፡፡ ከቡስካ ተራራ ሥር ሀመር ሠርግ ቤት ታድሞ የተመለከተውንና የምሽቱን የከብት ዝላይ ድባብ እንዲህ ያካፍለናል፡፡)

(ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ)

ቡስካ ተዘርግቷል፡፡ ሻንቆ ቀበሌ ትከሻዋ ቡስካ ነው፡፡ ጠባቧ ቅጥር ብዙ ሰው ይዛለች፡፡ ሀመሮች ከደግ ልባቸውና ከብርኩታ ትራሳቸው አይነጥሉም፡፡ እንዲህ ባሉ ሰዎች የተሞላው ሰርግ ቤት አንዱ እንግዳ እኔ ነኝ፡፡

ሠርግ ቤት ትንሽ ዳስ በቅጠል ተሰርታለታለች፡፡ ወንበር ደርድሮ እንግዳን መቀበል የለም፡፡ ሴቶቹ ስራ ያጣድፋቸዋል፡፡ የመጣው እንግዳ ብርኩታው ላይ ቁጢጥ ብሎ ወጉን ይሰልቃል፡፡ እስከአሁን ጭፈራ የለም፡፡ በሀመር ሠርግ የታደመ ሰው ያለውን ይጥላል፡፡

የሙሽራዋ መሄጃ ሰዓት ደረሰ፡፡ ሙሽራው አይመጣም፡፡ እሷ ብቻ በሚዜዎቿ ታጅባ ወደ ሙሽራው ቤት ትሄዳለች፡፡ በዚህ መካከል ግርግር ተፈጠረ፡፡ ሙሽሪት አልሄድም ብላ ጎጆው ቆጥ ላይ ወጣች፡፡ ከማማው እንድትወርድ የመንደሩ ሰውና አብሮ አደጎቿ ልመናቸውን ቀጠሉ፡፡ ደግሞ ሌላው ጥግ ምንም እንዳልተፈጠረ የሀመርን ባህላዊ መጠጥ ከውብ ጨዋታው ጋር የሚኮሞኩሙ የሽማግሌዎች ስብስብ ይታየኛል፡፡

ከብዙ ማግባባት በኋላ ሙሽሪት ወረደች፡፡ ከዓይኗ እንባ እየወረደ ጭምር፡፡ አሳዘነቺኝ፡፡ ሚዜዎቿ አብረው ያለቅሳሉ፡፡ ነገሩ ሁሉ የጨለመባት መሰለ፤ ከእናት ከአባቷ ቤት መውጣቱ ከብዷታል በዚያ ሁኔታ ውስጥ ጭፈራው ተጀመረ፤ እሷን ግን ማሳቅ አልቻለም፡፡ ከቅጥር ግቢው ወጣች፡፡ ከቦረቀችባት ጠባብ እልፍኝ፡፡

ተከትዬ አጅቤያለሁ፡፡ ዜማው ልብ ይነካል፡፡ ቢቶ አስተርጎመኝ፤ የሚሰድቡት ሙሽራውን ነው፡፡ የሴቷ ሚዜዎች መንግስት ቤት ጥበቃ የሚሰራውን ሙሽራ ከብት ብትጠብቅ ይሻልህ ነበር አሁን ምን ታበላታለህ እያሉት ነው፡፡

የወንዱ ቤት እዚያው ጎረቤት ነው፡፡ ግን የሀመር ሰርገኞች እርምጃ የምድር የመጨረሻው ቀሰስተኛ ነው፡፡ በየቦታው ይታረፋል፡፡ እናቶች አረቄ በሃይላንድ ይዘው ሁሉን ያቃምሳሉ፡፡ ጭፈራው አይቋረጥም፡፡ ሙሽሪት እረስታዋለች፡፡

ወንዱ ደጃፍ ደረስን፡፡ እሱ እንደ ባህሉ አይወጣም፡፡ የእሱ ወገኖች እሚጠጣ ይዘው ጠበቁን፡፡ አቀባበሉ ድረስ አብሬ ነበርሁ፡፡ ከዚያ እሷ ወደ ሙሽራው ቤት ስትገባ እኔ ወደ ከብት ዝላዮ በረርሁ፡፡

ከብት የሚዘለው ዝግጅቱን ጨርሷል፡፡ በሀመር ከብት ዝላይ ከሰርግ የሚደምቅ ግዙፍ ኩነት ነው፡፡ አቤት ድግስ፣ አቤት ጭፈራ፤ አቤት ውበት፡፡

ሁሉም ሥርዓቶች ተጠናቀው ወደ መዝለያው ቦታ ከብቶቹ ተደረደሩ፡፡ ጭፈራው ቀልጧል፡፡ ጩኽት ሰማሁ፡፡ ቀና ስል አንድ እርቃኑን የሆነ ወጣት ከከብቶች ጀርባ ላይ እንደ አሞራ እየቀዘፈ ነበር፡፡ ቡስካን አየሁት፤ እንዲህ ያለውን ትዕይት ሲመለከት የኖረ ውብ ተራራ፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top