Connect with us

በውሃና ፍሳሸ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የታዩ የህግና የአሰራር ክፍተቶች               

በውሃና ፍሳሸ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የታዩ የህግና የአሰራር ክፍተቶች
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

ዜና

በውሃና ፍሳሸ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የታዩ የህግና የአሰራር ክፍተቶች               

በውሃና ፍሳሸ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የታዩ የህግና የአሰራር ክፍተቶች               

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 12(1) እና (2) የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ለሕዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ መከናወን እንዳለበት እና ማንኛውም የስራ ሃላፊ እና ሰራተኛ ሃላፊነቱን ቢያጓድል ተጠያቂነት ያለበት መሆኑን ይደነግጋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 55/15/ መሠረት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 211/92 ተቋቁሞ ሥልጣንና ተግባሩ በ1142/2011 እንዲሻሻል በተደረገው መሰረት የተቋማቱን የአገልግሎት አሸጣጥና አሰራር በመፈተሽ ጉድለት ሲገኝ ተገቢውን ማስተካከያ እንዲያደርጉ አቅጣጫ ከማስቀመጥ ባለፈ በህግ እንዲጠየቁ ያደርጋል።

በዚሁ መሠረት ተቋሙ የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡና ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመወጣት እንዲያስችለው በ2013 በጀት ዓመት ከታቀዱ ተግባራት መካከል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሸ ባለስልጣን በሚሰጡ አገልግሎቶች፣ በሚተላለፉ ውሳኔዎችና አሰራሮች በሕግ መሰረት ስለማስፈፀማቸው ቁጥጥር ተካሂዷል።

በመሆኑም ከመስሪያ ቤቱ ከማኔጅመንት አባላት ፣ ከፈጻሚዎችና ከተገልጋዮች ጋር ከመልካም አስተዳደር አኳያ በሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ውይይት በማድረግ አስፈላጊ መረጃዎችን በማሰባሰብ በተደረገ ቁጥጥር የተለዩ ግኝቶች ማለትም ጠንካራ ጎን፣ የሕግና የአሰራር ክፍተቶች እና የመፍትሄ ሃሣቦች ተለይተው የቀረቡ ሲሆን፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሸ ባለስልጣን በሚሰጡ አገልግሎቶች፣ በሚተላለፉ ውሳኔዎችና አሰራሮች በሕግ መሰረት ስለማስፈፀማቸው በተደረገው ቁጥጥር የታዩ ክፍተቶች እንደሚከተለው ቀርቧል።

አንደኛ ከንፁህ የመጠጥ ውሃና አቅርቦት ጋር ተያይዞ የወጡ የህግ ማዕቀፎች /አዋጅ ፣ደንብ፣ መመሪያ ማንዋል / በሕግ ማዕቀፍ አተገባበር በሚመለከት የተስተዋሉ ችግሮች፤ ኮንዶሚኒየም ቤቶች (ከቤቶች ኤጀንሲ) እና የሬልስቴት ባለቤቶች ከባለስልጣን መስሪያቤቱ ጋር ያላቸውን የስራ ግንኙነቶችን በተመለከተ ግልፅ የሆነ መመሪያዎች አለመኖር፤ መመሪያዎች ወቅቱን ባማከለ መልኩ (የውሃ ታሪፍ፣ የመንግስት የኪራይ ቤቶች፣ ሰነድ አልባ ቤቶች) ያለመሻሻል ክፍተቶች አሉ።

ሁለተኛ በመሥሪያ ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች በመልካም አስተዳደር ዕቅድና በዕቅዱ ማስፈፀሚያ ድርጊት መርሐ-ግብር መሰረት ለተገልጋዩ ግልፅ፣ ቀልጣፋና ፍትሐዊ አገልግሎትን በተመለከተ፤ ባለስልጣኑ ዕቅዱን በየአመቱ ያውላል። በወጣው መርሃግብር መሠረት ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ወዲያው ችግሮችን በመለየትና በመቅረፍ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ለደንበኞች ፎረም በማሳወቅ በአመት አራት ጊዜ የታቀደውን ዕቅድ በማየት እና በመገምገም የሚሰራበት አካሂድ አለ። ነገር ግን ግልጽ፣ ቀልጣፋና ፍትሐዊ አገልግሎት ከመስጠት አኳያ ውስንነቶች አሉበት። ከግልጽነት አንጻር፡- የተቋሙ ደንበኞችና ባለድርሻ አካላት ስለተቋሙ በቂ መረጃ ያላቸው (ያወቁ) ሆነው ተገቢውን አቋም መያዝ ይኖርባቸዋል። ከዚህም አንጻር በተቋሙ በየደረጃው ያለውን የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱ ምን እንደሚመስል፣ በምን መርህና ህግ እንደሚመራ፣ እንዴት እንደሚፈጸም፣ በምን የአፈጻጸም እስታንዳርድ እንደሚፈጸም፣ በማን እንደሚፈጸም፣ መቼ እንደሚፈጸም ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉት ጉዳዮችን ለውስጥና ለውጭ ደንበኞች ግልጽ ከማድረግ አንጻር ወስንነት ያለ መሆኑ፤ ለአብነት ያህል ዜጎች /ደንበኞች/ ለልማት ተነሽ ማኅበረሠብ ቅድሚያ መስጠት በሌሎች ማለትም አዲስ በሚገነቡና ወረፋ የያዙ የማህበረሰብ ክፍሎች ቅሬታ እያስነሱ መሆኑ ነው።

ከቀልጣፋነትና ውጤታማነት አንጻር፡- ቀልጣፋነት ማለት የሚፈጸሙ መንግስታዊ አገልግሎቶች ባጠረ ጊዜ፣ በተመጣጣኝ ወጪና ያለሀብት ብክነት አገልግሎት መስጠት የመቻል ጉዳይ ነው። ውጤታማነት ማለት አንድን ስራ የተቀመጠለትን ግብና ዓላማ ለማሳካት በሚያስችል አኳኋን የመፈጸም ጉዳይ ነው። ከዚህ አንጻር ተቋሙ ሰፊ ክፍተት አለበት። ለአብነት ያህል የፍሳሽ ማስወገድ መስመር ዝርጋታ (ዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገድ፣ householding tube) ገና 20 በመቶ አልደረሰም።

ከፍትሐዊ አንጻር፡- ፍትሀዊነት በመንግስታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ተገልጋዩ /ዜጋ/ ያለአድሎና በደል እንዲገለገሉ፣ እንዲስተናገዱና ጥያቄና ቅሬታ ካላቸው በተገቢው መንገድ ምላሸ እንዲሰጣቸው የሚያስችል መርህ ነው። ከዚህ አንጻር የተሰሩ ስራዎች ቢኖሩም ገና ያልተሻገራቸው በርካታ ስራዎች አሉ። ለአብነት ያህል የውሃ ስርጭት ፈረቃው በአግባቡ አለመመራቱ አንዱ ማሳያ ነው።

ሦስተኛ በከተማዋ የውሃ እጥረትንና የሥርጭት ችግርን፣ የመስመር ብልሽትን፣ ከፍሳሽ የልማት ስራና አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም የባለሙያ እጥረት እና ፍልሰትን እንዲሁም የግንዛቤና የአመለካከት ችግሮችን ለመፍታትና ለመቅረፍ የተሠሩ ሥራዎች መኖራቸውን በሚመለከት፤ በከተማዋ የውሃ እጥረትን በተመለከተ የውሃ ምርቱ ከፍላጎቱ ጋር አለመጣጣም። ይህም ሲባል የችግሩ መንስኤዎች የውሃ ምርት መቀነስ፣ የውሃ ብክነት መጨመር የውሃ ጉድጓዶች በዲዛይን ካፓሲታቸው ልክ እንዲሰሩ አለመደረጉ፣ ከፍተኛ የውሃ እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች ተጨማሪና በቂ የውሃ ጉድጓድ አለመቆፈሩ፣ ለግንባታ ስራ፣ ለእሳት አደጋ ወ.ዘ.ተ አገልግሎት የሚውል አማራጭ ውሃ አለማዘጋጀቱ። የውሃ ሥርጭትን በተመለከተ፡- የውሃ ስርጭት ፍትሀዊ አለመሆን ከዚህም አኳያ የችግሩ መንስኤዎች የውሃ ስርጭት ፈረቃው በደንብ በአግባቡ ባለመመራቱ ለውሃ ምርቱ ስርጭት ምክንያት የሆኑ የውሃ ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ያለውን ችግር አለመፈታቱ (ተጨማሪ የማስተላለፊያ መስመሮችን አለመዘርጋት) የመብራት መቆራረጥና ትራንስፎርመር መቃጠል፣ ውሃ በቦቴ አለማቅረብ፣ የቦኖ ውሃ ያለመገንባት፣ የውሃ ስርጭት ስራው ክትትልና ቁጥጥር በቴክኖሎጂ የታገዘ አለመሆን (ስካዳ ሲስተም አለመኖር)፣ የተሻለ የመግፋት አቅም ያላቸው የውሃ ፓምፖችን አገልግሎት እንዲውሉ አለማድረግ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር ትርጉም ባለው መልኩ ተቀናጅቶ አለመስራት።

የመስመር ብልሽት በተመለከተ፡- እነዚህ ችግሮች በሚያጋጥሙበት ጊዜ ህብረተሰቡ ጥቆማ በመስጠት ያለውን ቅሬታና ጥቆማ በመቀበል እንዲሁም ከሕብረተሰቡ ጋር በተለያየ ደረጃ በጋራ በመሥራት ክፍተቶችን ለመሙላት ውጤታማ ሥራዎች እየተስሩ መሆኑ። ነገር ግን ከአፋጣኝ ምላሸ ከመስጠት አኳያ ውስንነቶች አሉ። ለአብነት የተሽከርካሪ እጥረት። ከፍሳሽ የልማት ስራና አገልግሎት አሰጣጥ በተመለከተ፡- ህብረተሰቡ የፍሳሽ ይነሳልኝ ፍላጎትና አገልግሎቱ የተመጣጠነ አለመሆን። ይህም ሲባል ዘመናዊ የፍሳሽ መስመር ተጠቃሚ ቁጥር ዝቅተኛ መሆን። የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ የፍሳሽ ማጣሪያ ግንባታ በበቂ ሁኔታ አለመከናወኑና ስራው በቂ የፍሳሽ ማንሻ ተሽከርካሪ አለመኖሩና አለመከናወኑ። የባለሙያ እጥረት እና ፍልሰትን በተመለከት በጥሩ ደረጃ ላይ ቢገኝም ሠራተኞች ጡረታ በሚወጡብት ጊዜ በእነሱ ምትክ ሰራተኛ ያለመቅጠር እና የስራ መጓተት እንዲሁም በዕቅዱ መሰረት እንዳይካሄድ ከማረግ አኳያ ክፍተት መኖሩ።

አራተኛ የውስጥና የውጭ የቅሬታ ሰሚ ማስተናገጃ ሥርዓት በተመለከተ የተቋሙ ባለሙያዎች ሙያቸውንና ተገልጋዮችን አክብሮ ከመስራት አንፃር የደንበኞች የቅሬታ ሰሚ ተቋቁሞ ክትትልና ግምገማ በማካሄድ የውስጥም የውጭም ቅሬታዎች የሚፈቱበት አሠራር ተዘርግቶ ለአብነት፤ ያህል ከ15 በላይ የተቋሙ ሰራተኞች የመመሪያና የህግ አተገባብር ችግር በዲሲፕሊን የተቀጡ መኖራቸው (ከቆጣሪ ንባብ ጋር በተገናኘ።

(ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ጋር በመተባበር በየሣምንቱ ቅዳሜ የሚወጣ፤ ታህሣሥ 10 ቀን 2013 ዓ.ም)

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top