Connect with us

ልደቱ አያሌው ከሰዓታት በኋላ ከእስር ሊለቀቁ ይችላሉ- አቶ አዳነ ታደሰ

ልደቱ አያሌው ከሰዓታት በኋላ ከእስር ሊለቀቁ ይችላሉ- አቶ አዳነ ታደሰ
Photo: Social media

ዜና

ልደቱ አያሌው ከሰዓታት በኋላ ከእስር ሊለቀቁ ይችላሉ- አቶ አዳነ ታደሰ

ልደቱ አያሌው ከሰዓታት በኋላ ከእስር ሊለቀቁ ይችላሉ- አቶ አዳነ ታደሰ

(በድሬቲዩብ ሪፖርተር)

በ30 ሺ ብር ዋስ ከእስር ተለቅቀው በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ አዳማ ከተማ በሚገኘው የኦሮምያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተወሰነላቸው አቶ ልደቱ አያሌው ከሰአታት በኋላ ከእስር ይወጣሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸው አቶ አዳነ ታደሰ የኢዴፓ ሊቀመንበር ለድሬቲዩብ ገለፁ።

አቶ ልደቱ ከዛሬ በፊት በነበረው ቀጠሮ በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ችሎት (አዳማ ከተማ) ቀርበው የክልሉ ዐቃቤ ህግ ክስ አሻሽሎ እንዲያቀርብ በታዘዘው መሰረት የተሻሻለው ከስ ሰምተዋል። የአቶ ልደቱ ጠበቆችም መልስ እንዲሰጡ ለዛሬ ታህሳስ 2 ቀን 2013 ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ቀጠሮ ተሰጥቶ ነበር፡፡

አቶ አዳነ ታደሰ ለድሬቲዩብ እንዳስረዱት የአቶ ልደቱ ጠበቆች ዐቃቤ ሕግ አሻሽል በተባለው መሰረት ህግና ስርአቱን በተከተለ መልኩ አሻሽሎ አለመቅረቡን በመጥቀስ መልስ የሰጡ ሲሆን አቶ ልደቱ አያሌውም አቃቤ ህግ እኔን በቀጠሮ ለማጉላላት እንጅ በተጨባጭ ከስሶ ለማስቀጣት እየተንቀሳቀሰ አይደለም በማለት ከጤናቸው አንፃር ዋስትና ተፈቅዶላቸው በውጭ ሆነው ለመከራከር እንዲፈቀድላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

በዋስትናው ጉዳይ ፍርድቤቱ የአቃቤ ህግን አስተያየት ሲጠይቅ ዋስትና ቢፈቀድላቸው ተቃውሞ እንደሌለው ገልጷል።

በዚህ መሰረት የ 30 ሺ ብር ዋስትና አቅርበው በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ፍርድቤቱ ወስኗል።

አቶ አዳነ እንደነገሩን በአሁን ሰአት የዋስትናውን ጉዳይ በማስጨረስ ሂደት ላይ መሆናቸውን የነገሩን ሲሆን ከሰአታት በኋላ አቶ ልደቱ ከእስር እንደሚለቀቁ ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል።

ከዚህ በፊት የኦሮሚያ ክልል ዐቃቤ ህግ ያቀረበውና እንዲሻሻል የታዘዘው ክስ “መንግሥትን ለማፍረስ በማሰብ” የሚል የነበረ ሲሆን ባለፈው ቀጠሮ የተሻሻለው ክስ “መንግስትን በማፍረስ” በሚል አንቀጽ ተሻሽሎ ወንጀሉን በማክበድ የቀረበ ነው።

አቶ ልደቱ ከዚህ ቀደም ፍርድቤት በ100ሺ ብር ዋስ ከእስር ተለቅቀው በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ቢወስንም በአስፈፃሚው አካል እምቢተኝነት ተፈፃሚ ሳይሆን ቀርቷል። ይህም የፍትህ ስርአቱን ክፉኛ ሲያስተቸው መቆየቱ የሚታወስ ነው።

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top