Connect with us

ህወሓት እና ኦነግ “ሸኔ” ምን እና ምን ናቸው ?

ህወሓት እና ኦነግ “ሸኔ” ምን እና ምን ናቸው ?
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ህወሓት እና ኦነግ “ሸኔ” ምን እና ምን ናቸው ?

ህወሓት እና ኦነግ “ሸኔ” ምን እና ምን ናቸው ?

( ኃይሌ ተስፋዬ )

 

እስካሁን ከህወሓት ያልጠቀስኩት አንድ “ኳሊቲ ¡¡” አለ። እሱም፦ ግለሰብን ወይም ቡድንን በጠላትነት ከመፈረጇ በፊት፥ የእሷን እኩይ ዓላማ አስፈጻሚ ትሆን ዘንድ ዕድሉን መስጠት ነው። ዕድሉን ስትሰጥህ ያኔ ከተስማማህ፣ አትነካህም፤ በተለይ ከእሷ ሥር እያጎበደድክ፣ ተላላኪ እና አሸርጋጅ ኾነህ የምትኖር ከሆነ፣ በጥርጣሬ ውስጥ ያለ ንቄትም ላይ ሆና በሕይወት ታኖርሃለች።

የህወሓት ጠባይ እንደ ጃርት ነው። ጃርት በርቀት ላይ ሆነህ እሾኾቿን አትወድርብህም። ይልቁንም እየቀርብካት በሄድክ ቁጥር ሊያጠፋኝ ነው በሚል “ሜንታሊቲ” ያለ የሌለ ኃይሏን ትጠቀማለች። ሕወሓትም እንዲሁ ነች። በርቀት አትነካህም። በማንኛውም ሁኔታ ስትቀርባት ግን የጃርቷን ሥራ ትሠራለች።

ህወሓት ኦነግን በሽግግሩ ሰሞን እንደ ቂል ነበር የምትቆጥረው። ምክንያቱ ደግሞ ዓላማና ኢላማውን ያልጠነቀቀ አማጺ እንደሆነ አድርጋ ቀድሞውኑ ስለፈረጀችው ነበር።

 በርግጥ ሁላችን እንደምናውቀው ኦነግ ትላንትናም ዛሬም ዓላማና ኢላማ የሌለው ቡድን ነው። ኦነግ በወቅቱ ዓላማ ቢኖረው ፥ በአቶ መለስ ዜናዊ ፖለቲካዊ ቁማር ፈዞ ወታደሮቹን “ሚኒ” ካምፕ አያስገባም ነበር። ኦነግ ዓላማ ቢኖረው፥ በዚህ በለውጡ ዘመን በፓርቲነት ተመዝገብ ሲባል “ እኔ ከሃያ ዓመት በፊት በሀገሪቱ ምርጫ ቦርድ ባህር መዝገብ ውስጥ የምታወቅ በመሆኑ፥ ድጋሚ በምርጫ ቦርድ መመዝገብ አያስፈልገኝም” ባላለ ነበር። ኦነግ ዓላማ ቢኖረው፥ እንደ ጭራቅ ይፈራ የነበረውን ማንነቱን አንጽቶለት፣ ወደ ሀገር ቤት ገብተህ በሰላማዊ መንገድ ታገል ያለውን የለውጥ ኃይል መልሶ በጠመንጃ አይወጋም ነበር።

ኦነግ ኢላማ ቢኖረው፥ ከቡራዩ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በተለያዩ አካባቢዎች በንጹሐን ላይ የተካሄዱ አሰቃቂ፣ ዘግናኝ እና አሳዛኝ ግድያዎችን አይፈጽምም ነበር። ኦነግ ኢላማ ቢኖረው፥ አሥር ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አሥራ ሰባት ባንኮችን አይዘርፍም ነበር።

ግን ኦነግ ዓላማም ኢላምም የሌለው፣ ሀገር የሚያደማ፣ ጠባብና ከፋፋይ የኾነ የአድኀሪያን ስብስብ በመሆኑ በእንዲህ ዓይነት የክህደት ግብር ተገልጦ አይተነዋል። ትላንት በአሸባሪነት ስታሳድደው የነበረችውም ህወሓት ዛሬ ለኦነግ ወዳጇ ነው፤ ተልዕኮም የምትሰጠው ራሷ ነች።

ሥለሆነም ፦

ኦነግ ሸኔ የኦሮሞ ህዝብ ጠላት ነው !!

ኦነግ ሸኔ የህወሓት መጠቀሚያ ዕቃ ነው !!

ኦነግ ሸኔ ኦሮምኛ ተናጋሪ የህወሓት ክንፍ ነው !!

ኦነግ ሸኔ ሁሌ በፖለቲካ የሚሸነፍ፣ተመራጭ ሀሳብ የሌለው ቡድን ነው !!

ኦነግ ሸኔ ግልገል ጁንታ ነው !!

ሥለሆነም ህወሓትና ኦነግ ሸኔ በባህርይም፣ በጠባይም፣ በአካሄድም፣ በሞራልም በአንድም በሌላም መንገድ አንድ ናቸው። የሁለቱም መሠረታዊ ዓላማ ፥ በኃይል እና በአመጽ የመንግስትን ስልጣን ተቆናጦ ኢትዮጵያን በሚፈልጓት መልኩ መቅደድና መስፋት ነው።

ይሁንና ፥ ህወሓትና ኦነግ ሸኔ በአሁኑ ሰዓት ትዳር መስርተው አገር ሊያፈርሱ ቢሰናዱም፣ ያልጠበቁት እና ያልገመቱት የእሳት ዱብዳ በላያቸው ላይ ሲወርድባቸው እየተመለከትን እንገኛለን።

እንግዲህ ከዚህ በኋላ መንግስት በእነዚህ እኩያን ኃይላት ላይ አንድ የቤት ሥራ ይቀረዋል። ይኸውም ሁለቱንም ጽንፈኞች በአሸባሪነት ዶሴ መዝግቦ፣ድርጅቶቹን በሕግ አፍርሶና ዳግም ወደ ፖለቲካ እንዳይመለሱ ደንግጎ፣  አቋማቸውን ማራመድ፣ መጋራት እንዲሁም ስምና ምልክታቸውን መጠቀም ወንጀል አድርጎ፣ ሀብታቸውን ሙሉ በሙሉ በመውረስ እኩያንን ከምድራችን ማስወገድ ግድ ይለዋል  ።

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top