Connect with us

ለአፍሪካ ፀረ-ሽብር ጥናት ማዕከል ተመራማሪዎች ገለፃ ተሰጠ

ለአፍሪካ ፀረ-ሽብር ጥናት ማዕከል ተመራማሪዎች ገለፃ ተሰጠ
አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ

ዜና

ለአፍሪካ ፀረ-ሽብር ጥናት ማዕከል ተመራማሪዎች ገለፃ ተሰጠ

ለአፍሪካ ፀረ-ሽብር ጥናት ማዕከል ተመራማሪዎች ገለፃ ተሰጠ

በአልጀርስ የሚገኘው የአፍሪካ ኀብረት ፀረ-ሽብር ጥናት ማዕከል ተመራማሪዎች በወቅታዊ የኢትዮጵያ መንግሥት ሕግን የማስከበር እርምጃ ዙሪያ በኀዳር 17 ቀን 2013 በሚሲዮኑ በተዘጋጀ ኘሮግራም ሠፊ ገለጻና ውይይት ተካሂዷል፡፡

ገለፃውን የሰጡት የሚሲዮኑ መሪ  አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ሲሆኑ፤ የጥናት ማዕከሉ በአፍሪካ ሠላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ክትትል የሚያደርግ ተቋም እንደመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግሥት በትግራይ ክልል እያካሄደ ያለውን የሕግ ማስከበር እንቅስቃሴ ዓላማ፣ በክልሉ የመሸገው የጥፋት ቡድን አባላት በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ የወሰዱት የክህደት ጥቃት እርምጃ መሆኑን፣ ሠራዊቱ ባደረገው ዘመቻም በርካታ ይዞታዎችን ነፃ በማውጣት በአሁኑ ወቅት የዘመቻው የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

የመንግሥት ሕግንና ሥርዓትን የማስከበር እንቅስቃሴው አጥፊው ቡድን ላይ ያነጣጠረና የሕወሃት ጁንታም በአጭር ጊዜ ውስጥ ለህግ የሚቀርብና ይህም የመላውን የትግራይ ህዝብና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ እፎይታ እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡

ይህ ቡድን ማይካድራ በተባለ አካባቢ ሠላማዊ ዜጐችን መጨፍጨፉንና ይህም ኢ-ሠብዓዊ ድርጊቱ በዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል በሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዝርዝር ሪፖርቶች የወጡ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በግጭቱም ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጐችን ወደ ተረጋጋ ሕይወት እነዲመለሱ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ የሠላምና መረጋጋት መልህቅ አገር መሆኗን በቀጠናው ሠላምና መረጋጋት እንዲሰፍን በፀረ-ሠላም ሃይሉ የሚያደርገውን አጥፊ እንቅስቃሴ መንግሥት በቁጥጥር ሥር የማዋል ሙሉ አቅም እንዳለውም አስረድተዋል፡፡

የአፍሪካ ኀብረት ፀረ-ሽብር ጥናት ማዕከል ተመራማሪዎች ጋር በተደረገው ውይይት የቡድኑ አባላት ላነሱት ጥያቄዎች በተሰጣቸው ምላሽ ስለ ሁኔታው ሙሉ ግንዛቤ መጨበጣቸውን እንዳስታወቁ ከዉጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር የተገኘዉ መረጃ ያሳያል፡፡(አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ)

 

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top