Connect with us

ፈጣሪ ሆይ ስለ ደጋጎቹ ወገኖቻችን ስትል የክፉዎችን ክፉ መንፈስ ሰብረህ ህዝብህን አድን፡፡

ፈጣሪ ሆይ ስለ ደጋጎቹ ወገኖቻችን ስትል የክፉዎችን ክፉ መንፈስ ሰብረህ ህዝብህን አድን፡፡ ኢትዮጵያውያኑን ጠብቅ፤ የኢትዮጵያን ጠላቶች ያለ ንጹህ ነፍስ ጥፋት አውድም፡፡
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ፈጣሪ ሆይ ስለ ደጋጎቹ ወገኖቻችን ስትል የክፉዎችን ክፉ መንፈስ ሰብረህ ህዝብህን አድን፡፡

ፈጣሪ ሆይ ስለ ደጋጎቹ ወገኖቻችን ስትል የክፉዎችን ክፉ መንፈስ ሰብረህ ህዝብህን አድን፡፡ ኢትዮጵያውያኑን ጠብቅ፤ የኢትዮጵያን ጠላቶች ያለ ንጹህ ነፍስ ጥፋት አውድም፡፡

ከስናፍቅሽ አዲስ

እኛ ግድ የሚለን፤ዘርፈው ውስኪ ስለሚራጩት ሳይሆን ተዘርፈው የኩሬ ውሃ ስለሚጠጡት ትግራዋይ ነው፡፡

የሌላ ሀገር ፓስፖርት ስለጨበጡት ሳይሆን ብሔራቸው መታወቂያቸው ላይ ስለተጻፈና በሌቦች ዳፋ ስለሚሸማቀቁ ንጹሃን ነው፡፡ የሰለጠነ ሀገር ሆነው ባልሰለጠነ ምኞት ሀገር ስለሚያፈርሱት እፉኝቶች ተርባ ልጇን ያስተማረች ደግ እናት ልጇን ለፍሬ እንዲያበቃላት ሰላምን እንድታገኝ ነው፡፡  

መርከብ ስለሚሸጡት ሳይሆን በድህነት ሳቢያ በመርከብ ሲሰደዱ ባህር ሰጥመው ስለሚቀሩ ወጣቶች ነው፡፡

እኛ ግድ የሚለን አዎ ስለ ወገኖቻችን ነው፡፡ ስለ ባንዳ ልጆች ሳይሆን ስለ ደጃች አሉላ ልጆች፡፡

ሀገር ስለ ሸጡት ሳይሆን እንደ ባሻ አውሎም ሀገር ስላዳኑት ነው፡፡ወገን ዘር እንዳይተካ ስለሚያደርጉት ሳይሆን በወሊድ ምክንያት ስለሚሞቱት ነው፡፡

የመቶ አመት ታሪክ ስለሚሉት የታሪክ ሌቦች ሳይሆን የሺህ አመት ቅርስ ስለጠበቁልን የታሪክ ባለ አደራዎች ነው፡፡እኛ ግድ የሚለን ስለ ወገኖቻችን ተጋሩዎች ነው፡፡

በአድዋ ስለ ሚያፍሩት የቅኝ ገዢ ተላላኪዎች ሳይሆን ቀኝ ገዢን ስለመከቱ ጀግኖች ነው፡፡

የወገንን የዕለት ጉርስ ስለሚነጥቁ ሳይሆን ከዕለት ጉርሳቸው ማጉረስ ባህላቸው ስለሆነው ደጎች ነው፡፡

ስለ ሃይማኖት አልባ ሶሻሊስቶች ሳይሆን በምህላ ሀገር ስለሚጠብቁ አማኞች ነው፡፡ እኛ ግድ የሚለን ስለ ስለ ተጋሩ የገዛ ወገኖቻችን ነው፡፡

የተጋሩ ቋንቋ ስለሚናገሩና ተጋሩን ከወገኑ እንዳይደማመጥ ስላደረጉት አስገንጣዮች ሳይሆን ያለ ቋንቋ ከወገናቸው ጋር በልብ ስለሚግባቡ ወገኖቻችን ነው፡፡

የእርዳታ ጥሬ ሸጠው ጦር መሳሪያ ስለሚገዙ አረመኔዎች ሳይሆን ጥሬ በልተው የሀገር ቅርስ ስለሚጠብቁ የገዳማት አባቶች ነው፡፡

የሀገር መሬት ስለሚወሩ ሳይሆን የተራቆተ መሬት አረንጓዴ ስለሚያደርጉ ነው፡፡

አክሱም ኤርፖርትን ስላፈረሱት ሳይሆን አክሱም ሐውልትን ስለጠበቁት ነው፡፡ ኢትዮጵያን ስላራቆቱት ሳይሆን አብረሃ ወ አጽበሃን ስለ አለሙት ነው፡፡ እኛ ወገኖቻችን የኢትዮጵያ ወዳጆች ናቸው፡፡ ስለ እነሱ፣ ስለ ንጹሃኑ ግድ ይለናል፡፡ ስለ ወንበዴ፣ ስለ እናት ጡት ነካሾች፣ ስለ ትግራይ ህዝብ ጠላቶች፣ ስለ ትግራይ ምድር አጥፊዎች፣ ስለ ኢትዮጵያ የብዙ ዘመን መከራዎች ግን መጨረሻቸው እንዲሆን እንመኛለን፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top