Connect with us

ወገኔ 600 ቁጥር አይደለም!!

ወገኔ 600 ቁጥር አይደለም!!
Ethiopian News Agency

ነፃ ሃሳብ

ወገኔ 600 ቁጥር አይደለም!!

ወገኔ 600 ቁጥር አይደለም!!

(አሥራት በጋሻው)

 

ወደ ሰማይ የደረሰ የንጹሃን የጣር  ድምጽ እና የምትቃትት ነፍስ ጥሪ። በስለት የታረዱ ጎናቸውን የተወጉ ሆዳቸው የተቀደደ የተተለተሉ ህጻናት ወጣቶች አዛውንት እናቶች  አራስ  እና ነፍሰ ጡሮች ጬኸት።

600 ቁጥር አይደለም ወገኔ ።ሰውነትህን ጠልተህ ሰው መሆንህን ትተህ አራዊት ትሆን ዘንድ የተፈረደብህ ቀን ሜዳ ላይ ተወርውረህ ከንቱ ነህ ሲሉህ ያኔ ቁጥር ነህ ። በጠመኔ ጽፈው እንዳጠፉት ቁጥር ነህ።በእርሳስ ጽፈው በላጲስ እንዳጠፉት አሀዝ ትሆናለህ።

ወንድሜ ብሄርህን ጠይቀው ሲገደሉህ  ያኔ ቁጥር ነህ።  ከተማው ላይ የተጣለው አስክሬን ሸተተ ።ያኔ  ለነሱ ቁጥር ይሄ ነው።

የሞተ ሰው ልብሱን  ገፈህ ሬሳውን አስተኝተህ የጀግና ዘፈን እየዘፈንክ  ዙሪያውን እየዞርክ ጨፈርክ ። አንተ ከሰውነት ተራ የወጣህ አልባሌ ነህና የተረገምክ ሁን። በተቀዳጅ ወረቀት ላይ በጻፈከው ርእዮተ አለም ታስረህ ክቡሩን የሰው ልጅ አጥፍተሀልና የገሀነም ደጆች ተከፍተው ይጠብቁሀል ።

600 ቁጥር አይደለም ወገኔ 

አንድ ሰው 600 ነው 600ም ስንትም አይደለም። ስጋ የለበሰ እንጀራ ፈላጊ ከርታታ ሰው ነው። በቃ ሰው ማለት ሌላ ምን ሊባል ነው?

ያንተው ወገን ሰው ነው ። ሰው ቁጥር አይሆንም ነፍሱ ትጸይፈሀለች ። ባለእዳም ታደርግሀለች።

ፍጡር የሰው ልጅ ከንቱ ። ለአንተ ርእዮተ አለምህን መቀየር ከብዶህ ደምህን መቀየሩ ቀለለህ። ይቅርታን ለመንፈስህ ሰላም ወስደህ አታንቀላፋም? ዳሩ ደም የጠራው ይቅበዘበዛልና የእጅህን ታገኛለህ።

መግደልን ከመነሻህ ትፈጽማት እንደነበር አውቃለሁ። በተኙበት የተረሸኑት የኢህአፓ አመራሮች በበደኖ ለአመጽ መቀስቀሻ የተገደሉት ንጹሀን ዜጎች በሀዋሳ ሎቄ በጠራራ ጸሀይ በመትረየስ የተገደሉት ወጣቶች በጋምቤላ የተጨፈጨፉት አኝዋኮች በመተከል በሱማሌ በጉራፈርዳ የፈጀሀቸው በአዲስ አበባ የገደልካቸው ወጣቶች በየስፍራው የወደቁ ነፍሳት ሁሉ የአንተ እጅ ስራ ውጤቶች ናቸው። ሌላም ሌላም  ታሪክና ጊዜ ያወጣዋል።እንቅልፍ አጥተህ ትሞታለህ።

የአንተን የ27 አመት መርዝ ተግተው ያደጉ የመንፈስ ፍሬዎችህ ዛሬም በማይካንድራ በዚያው በትውልድ ስፍራህ ዘር ለይተው ጨፈጨፉ ።አሁን ጽዋው ሞላ። 

 ህወሀት በተጸነችበት ስፍራ ታበቃ ዘንድ የ600 ፍጡራን ነፍስ ይጣራል ። ወንጀለኞች ለፍርድ እስኪቀርቡ ጦርነቱ ይቀጥላል።

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top