Connect with us

መንግስት መቀሌንና ነዋሪዎቿን ከነዚህ በሽተኞች የመጨረሻ ትንፋሽ ለመጠበቅ የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ አለበት፡፡

መንግስት መቀሌንና ነዋሪዎቿን ከነዚህ በሽተኞች የመጨረሻ ትንፋሽ ለመጠበቅ የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ አለበት፡፡
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

መንግስት መቀሌንና ነዋሪዎቿን ከነዚህ በሽተኞች የመጨረሻ ትንፋሽ ለመጠበቅ የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ አለበት፡፡

መንግስት መቀሌንና ነዋሪዎቿን ከነዚህ በሽተኞች የመጨረሻ ትንፋሽ ለመጠበቅ የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ አለበት፡፡

መላው የኢትዮጵያ ህዝብም ከጎኑ ሊቆም ሊተባበር ይገባል፡፡

(ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)

ከአመታት በፊት፣ በአንድ ጽሁፌ ውስጥ፣ ‹‹የወያኔ መሪዎች እኛ ስልጣን ከለቀቅን ኢትዮጵያ ትፈርሳለች፤ እንደ ኢራቅና ሊቢያ ትሆናለች፤ ይላሉ፡፡ ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ እንደኢራቅና ሊቢያ ከመሆኗ፣ እኛም እንደነዚህ ሀገር ዜጎች ከመሆናችን በፊት እነሱ እንደሳዳም ሁሴንና ጋዳፊ መሆናቸውን አያስቡም፡፡›› ብዬ ነበር፡፡ እነሆ ጊዜው ደረሰ! ሀገራችን እንደሊቢያና ኢራቅ ሳትሆን እነሱ እንደ ጋዳፊና ሳዳም ይሆናሉ፡፡

አንባገነንነት በሽታ ነው፤ ሳዳም የቤተመንግስቱ ምድር ቤት ውስጥ ሆኖ በኬሚካል መሳሪያ ሀገራትን ሊያጠፋ እንደሆነ ያወራ ነበር፡፡ የትህነግ በሽተኞችም መቀሌ ውስጥ በየቤተ እምነቱ ተሸሽገው፣ በጦርነቱ ያልተሳተፈውን የኤርትራ ጦር ጨፍጭፈው እንደጨረሱት፣ የኢትዮጵያን ጦር እንደደመሰሱት ይናገራሉ፡፡ . . . እና እየፎከሩ፣ እየገደሉ አድገው፣ ነግሰው፣  ምላሳቸው እንደፎከረ፣ ጣታቸው ምላጭ እንደሳበ እየሞቱ ነው፡፡ . . . .

አረመኔዎች ለዜጎቻቸው አይመለሱም፤ በሽታቸው ካንሰር ነው፤ አይፈወስም፡፡ አያድጉም፡፡ በሽምቅ ውጊያ ዘመን በአብዮታዊ ዲሞክራሲ መስመር፣ በመጋዣ ጀርባ ስንቅና ትጥቅ ጭነው፣ ሽርጥ አንገታቸው ላይ ጠምጥመው፣ ድልድይ እያፈረሱ፣ ወንድሞቻቸውን ሳይቀር እየገደሉ፣ እንበር ተጋዳላይ እየዘፈኑ መጥተው፤ ዛሬም መንግስት ሆነው ኖረው፣ በዛው መስመር፣ በዛው ዘፈን፣ ሽርጣቸውን ጠምጥመው፣ ድልድይ እያፈረሱ፣ እየገደሉ ይሞታሉ፡፡ አረመኔነት ካንሰር ነው፡፡ . . . .

መንግስት መቀሌንና ነዋሪዎቿን ከነዚህ በሽተኞች የመጨረሻ ትንፋሽ ለመጠበቅ የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ አለበት፡፡ መላው የኢትዮጵያ ህዝብም ከጎኑ ሊቆም ሊተባበር ይገባል፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top