Connect with us

“ መቀሌን ይይዛሉ ማስተዳደር ግን አይችሉም !! ” – አዲሱ የህወሓት ነጠላ ዜማ !!

“ መቀሌን ይይዛሉ ማስተዳደር ግን አይችሉም !! ” - አዲሱ የህወሓት ነጠላ ዜማ !!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

“ መቀሌን ይይዛሉ ማስተዳደር ግን አይችሉም !! ” – አዲሱ የህወሓት ነጠላ ዜማ !!

“ መቀሌን ይይዛሉ ማስተዳደር ግን አይችሉም !! ” – አዲሱ የህወሓት ነጠላ ዜማ !!

( ኃይሌ ተስፋዬ )

………

ትህነግ ቀልድ አያልቅባትም ። ስትቀልድም ያለ ሀፍረት “አድምታ” ነው የምትቀልደው ። ጥቁሩን ነጭ፣ ነጩን ደግሞ ጥቁር ከማለት በዘለለ፣ በሬ ይወልዳል እንወራረድ ዓይነት የህልም ቅዤት ታበዛለች።

47 ዓመት ሙሉ ህዝባዊነት ጌጤ፣ መገለጫዬ ነው ! እያለች በድግግሞሽ መፈክሯ እዚህ የደረሰችው ትህነግ፥ ዛሬም ለትግራዋይ ሁሉ ብቸኛው መከታውና ጋሻው ከእሷ ሌላ ላሣር እንደኾነ እየነገረችው ትገኛለች። በርግጥ ትህነግ በተለይ ከሰሞኑ ከተግባራዊ ጦርነት ይልቅ ወደ እንካ ስላንቴ ቁልቁል የወረደች ብትሆንም፥ በዚህ በ11ኛው ሰዓት ግን እያሳየች ያለችው ጠባይ (Fun children’s game) የሚሉትን ዓይነት አዝናኝ የልጆች ጨዋታ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

 የትግራይ ሴንትራል ኮማንድ ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ ቴሌቪዢን ቀርበው ፦ “ ጦርነቱ ህዝባዊ ጦርነት ነው። እያንዳንዱ የትግራይ ተወላጅ ጠመንጃም የያዘም፣ ያልያዘም ጦር ፣ጩቤ የያዘው በሙሉ የሚመክተው ጦርነት ነው ። ይህንን ጦርነት ለመከላከል ከሊቅ እስከ ደቂቅ በመሰለፍ ጠላቶቻችንን እንጠርጋለን ፥ መቀሌ ገባ አልገባ የእኔ ርዕስ አይደለም። እርግጠኛ መሆን የምችለው  ግን ይሄ ኃይል ትግራይን ማስተዳደር አይችልም።” ሲሉ ተደምጠዋል።

በዚህ በአቶ ጌታቸው ንግግር ውስጥ ሽንፈትና መደናገር የሚነበብ ሲሆን፥ ጦርነቱን ህዝባዊ የማድረግና መከላከያ ኃይላችንን ከተማ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ካስገቡ በኋላ ቦታዎችንና ከተሞችን እየለዋወጡ ቃላቸውን እንደሚፈጽሙ በማያልቀው የመጨረሻ ዛቻቸው ላይ አቅርበዋል።

 መቼም ከመጀመሪያው ጀምሮ የህወሓትን መዘባረቅ ልብ ብሎ ያስተዋለና የተከታተለ ሰው እነዚህ ሰዎች ግን ምን ኾነው ይሆን ? ወይንስ የህዝብንና የቡድንን ፍላጎትና ሀሳብ ጠንቅቆ ማስተዋል አቃታቸውን ? ያስብላል። ምክንያቱም ህዝብን እንደ ግለሰብ ወይም ጥቂት ቡድን በአንተ አስተሳሰብና መርህ ብቻ በግዴታ ጠርንፈህ ልትመራው አትችልም። ይህ ለህዝብ ካለ ንቀትና፥ እንደ ትህነግ  ህዝብ ሸርተቴ ነው ! ከሚል የማን ያህሎኝ አስተሳሰብ የሚመነጭ ድካም ነው። ህዝብ ሸርተቴ አይደለም። የሚጠቅመውን ያውቃል ! ህወሓት ቡድን ናት ! የትግራይ ህዝብ ደግሞ ሰፊና ታላቅ ህዝብ ነው! እውነታው ይሄው ነው !!

ይኹንና ህወሓት ከተግባራዊው ጦርነት ይልቅ ወደ መፈክር ወርዷል። ሌላውን ሁሉ ትተን የህወሓት ተደጋጋሚ “ሞቶ” የሆነውን ቃል እንኳን ብንጠቅስ፥ “ትግራይ የጠላቶቻችን የአድኀሪያን መቀበሪያ ናት” ሲሉ ነበር። በኋላ ደግሞ አሻሽለው “መቀሌ የወራሪዎች መቀበሪያ ናት” አሉ! አሁን ደግሞ “መቀሌን ይይዛሉ ማስተዳደር ግን አይችሉም !!” ወደሚል እንቶፈንቶ ውስጥ ገብተዋል። ይሄም ስልታዊ ማፈግፈግ መሆኑ ነው ?

እንግዲህ ይሄ ሁሉ ቃላባይነት የገለጠው ነገር ቢኖር ትህነግ ህዝባዊ መሠረት ማጣቱን ነው። ህዝባዊ መሠረት ሊኖር የሚችለው የህዝቡን ዘለቄታዊ ተጠቃሚነትና የህልውና ጥያቄ ስትመልስለት ብቻ ነው።ታዲያ ህወሓት አንድ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር ጠመንጃ እየወለወለችና እየወዘወዘች ከመደንፋት በቀር ለትግራይ ህዝብ ምን ዓይነት ምላሽ ነው ስትሰጥ የኖረችው ? መልሱን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያውቀው ጉዳይ ነው።

ይኹንና አቶ ጌታቸው ህዝባዊ መሠረት አለንና ህዝባችን ሆ ብሎ ጠላቱን እንዲወጋ ብለዋል። ጠላቶቻችን መቀሌን ይይዛሉ ማስተዳደር ግን አይችሉም። መንግስቱ ኃይለ ማርያምም ትግራይን ይዞ ነበር፤ ትግራይን አስተዳድሮ ግን አያውቅም የሚል ገለባ ሀሳብ አቅርበዋል።

ይህ ደግሞ ከሰሞኑ አዲሱ የህወሓት ነጠላ ዜማ መሆኑ ነው ።?!

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top