Connect with us

ትህነግን በእሳት ያስገረፈው “ የወረደ ልጅ “ ነው !

ትህነግን በእሳት ያስገረፈው “ የወረደ ልጅ “ ነው !
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ትህነግን በእሳት ያስገረፈው “ የወረደ ልጅ “ ነው !

ትህነግን በእሳት ያስገረፈው “ የወረደ ልጅ “ ነው !

(ንጉስ ወዳጄነው ማሙዬ)

 

 ታደሰ  ወረደ (ሜ/ጀ) የጁንታው ዋና አሰልጣኝና የወታደራዊው ሴራ  ክንፍ መሪ ነው። ትህነግ  በፖለቲካው መስክ የገጠመውን ኪሳራ ተነጋግሮ  እንዲፈታ ከመምከር ይልቅ” ልዮ ሀይል ገንብተናል፣ ሚሊሻው በክፍለጦሮች ተዋቅሯል፣ ተጋሩም ሴት ወንዱ ይዋጋል” እያለ በእብሪት ሲኮፍሰው የነበረው ይህ ሰው ነበር ።

አሁን ላይ ጡረተኛው ጀኔራል ወዲ ወረደ መረጃው ገና  የተረጋገጠ  ባይሆንም፤ ራሱ በለኮሰው ጦርነት መገደሉ እየተሰማ ነው ።  ቢያንስ ግን የትህነግ ሞት እንዲፋጠን፣ እብሪተኞች እንዲኮላሹ  ፣ የማይነካውን ቀይ መስመር አስረግጧልና ጋንግሪኑን ለመገላገል አስተዋፅ አድርጎል።   

አሳዛኝ  ቢሆንም በተወናበደ ቅስቀሳና በተራ እብሪት አነሳስቶ  የትግራይ ወጣትንም እሳት ላይ እንዲመገድ ያደረገው  ይሄው “የጦር ሊቅ”   በመሆኑ የህግም  የታሪክም ተወቃሽነቱን ግን አይቀርለትም።

እነጀኔራል ታደሰና በርከት ያሉት የህወሀት ማፍያዎች በስልጣናቸው ተጠቅመው ሀብት በሀብት ላይ ከምረዋል። ከለውጥ  በሆላ ግን ይሄ የጥቅምም ሆነ የሴራ  መንገድ ነጥፎባቸዋል።  ስለዚህ አገር ፈርሳም ቢሆን ወደዘረፋ ምንጫቸው ስልጣን መመለስ ፈልገዋል። 

እናም የድሀውን ተጋሩ ልጅ ወደጦርነት መልሰው ማግደውታል። ለራሳቸውም የፍፃሚያቸውን ቀን የሚያቀርብ እሳት ጭረዋል። ረመጡን መታቀፍ ይሆናል እጣቸው።

ታደሰ ወረደና ግብረአበሮቹ በተለይ አብሯቸው  የኖረውን ሰሜን እዝ ከድተው በማጥቃት ታሪክ ይቅር የማይላቸውን ጥፋት ፈፅመዋል። በባንዳነት እብሪትም የእናት ጡት ነካሽነታቸውን በግላጭ አሳይተዋል።

በምላሹ ግን መላው የአገራችን  ህዝቦችና ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን በአንድ ተነስተው፣ የትህነግን ግበአተ  መሬት እያፈጠኑት ይገኛሉ። 

ለሁሉም በመቅሰፍታዊው ውጊያ ታደሰ ወረደ ሞተም፣ ተረፈም ትህነግና ጁንታው የሚቃጠሉበትን ጦርነት በእውር ድንብር እይታው ለኩሷልና፣ በህወሀት  የታሪክ ፍፃሜ ላይ እናስታውሰዋለን።

ድል ለሰራዊታችን   !!

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top