Connect with us

በአራት ወራት ብቻ 108 ቢለየን ብር ገቢ ተሰበሰበ

በአራት ወራት ብቻ 108 ቢለየን ብር ገቢ ተሰበሰበ
Ethiopian Broadcasting Corporation

ኢኮኖሚ

በአራት ወራት ብቻ 108 ቢለየን ብር ገቢ ተሰበሰበ

በአራት ወራት ብቻ 108 ቢለየን ብር ገቢ ተሰበሰበ

የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት አራት ወራት ለመሰብሰብ ካደቀው 104 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ 107 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው አስታወቁ፡፡

ሚኒስትሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት የተሰበሰበው ገቢ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ17 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር እድገት ማሳየቱን ጠቅሰው የህግ ተገዢነት ደረጃ መሻሻል፣ የተቋሙ ሰራተኛና አመራሮች ቁርጠኝነት መጨመር እና የገቢው መሰረትን ለማስፋት የተደረጉ ጥረቶች ገቢው እንዲጨምር ከሚጠቀሱ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውን የተናገሩት አቶ ላቀ የኤሌክትሮኒክ አገልግሎቶችም በአራት ወራት መጠናከራቸውን ለገቢ አሰባሰቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበረው ብለዋል፡፡

ህግን ለማስከበር ከተከናወኑ ተግብራት መካከል የኮንትሮባንድ ክትትል አንዱ ሲሆን በወጪና ገቢ ኮንትሮባንድ 1 ነጥብ 08 ቢሊየን ብር የተገኘ ሲሆን የፌደራል እና የክልል የጸጥታ አካላት፣ የጉምሩክ ኮምሽን ሰራተኞች እንዲሁም ሌሎች አጋር አካላት ሚና የላቀ በመሆኑ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ 

በፌደሬሽን ምክር ቤት በተወሰነው መሰረት የክልል እና የፌደራል መንግስት ገቢ ክፍፍልን ወደ ተግባር በመቀየር ባለፉት አራት ወራት ከ3 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ ለክልሎች መተላለፉን የገለጹት ሚኒስትሩ ተቋሙ ባለፉት ጊዜያት በሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ሀላፊነቱንም እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአራት ወራት ውስጥ በዝግጅት ምዕራፍ ከተከናወኑ ስራዎች መካከል ግብር ከፋዮችን በከፈሉት የገንዘብ መጠን ብቻ ሳይሆን ተጨማሪ መስፈርቶችን ባካተተ መልኩ ምደባ በመስጠት የታክስ ህግ ተገዢነትን ለማሳደግ እንዲሁም ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በብቃት ለመሰብሰብ ደግሞ ተጨማሪ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች መከፈታቸውን እንዲሁም የህግ ተገዢነትን ለማጎልበት በ2012 ዓ.ም በታማኝነት ግብራቸውን ለከፈሉ ግብር ከፋዮች እውቅና መሰጠቱን አንስተዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር በቀጣይ ጉድለቶችን በማረም፣ የአሰራር ችግሮችን በመቅረፍ ግልጽ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን የተናገሩት አቶ ላቀ በታማኝነት ግብራቸውን ለሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ምስጋናቸውን አቅርበው በተለይ ሀገር በብዙ ችግሮች እየተፈተነች ባለችበት በዚህ ሰዓት ግብር ከፋዩ ከሚያገኘው ላይ ግብሩን በወቅቱ በመክፈል ለሀገሩ ያለውን ፍቅር ሊያሳይ ይገባል ብለዋል፡፡(ገቢዎች ሚ/ር)

 

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top