Connect with us

“በትግራይ እየተካሄደ ያለው ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ኦፕሬሽን ነው”

"በትግራይ እየተካሄደ ያለው ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ኦፕሬሽን ነው" አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን
Photo: ካፒታል ጋዜጣ

ዜና

“በትግራይ እየተካሄደ ያለው ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ኦፕሬሽን ነው”

“በትግራይ እየተካሄደ ያለው ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ኦፕሬሽን ነው”

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

በሀገሪቷ የተፈጠረው ሁኔታ ከጦርነት ይልቅ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ወንጀለኞችን ለፍርድ የማቅረብ ኦፕሬሽን ነው ሲሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የኮሚኒኬሽን ቡድን ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን  ገለጹ፡፡

ጎረቤት ሀገራትም የኢትዮጵያ መንግስት ሁኔታን በመረዳት ለመንግስት ድጋፍ እንደሚያደርጉ የገለፁት አምባሳደር ሬድዋን ጅቡቲ፣ ሱዳን እና ኤርትራ ከመንግሥት ጎን ቆመዋል፡፡

በዚህም ኤርትራ ራሷን ወደ ጦርነት በማስገባት ተሳታፊ እንደማትሆን ገልፀው ነገር ግን ድንበር አልፈው ለሚመጡ ንፁሃን ዜጎችን እንደምትቀበል ገልፀዋል፡፡

በጅቡቲ በኩልም ማንኛውም የጦር ወንጀለኛ ወደ ጅቡቲ የሚያሸሹ ካለ ለኢትዮጵያ መንግስት ለማስረከብ ቃል በመግባት እየሰሩ ሲሆን በተጨማሪም ገቢ እና ወጪ እቃዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ተገቢውን ጥበቃ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡

ሱዳን በበኩሏ በትግራይ በኩል የሚያዋስናትን ድንበር ህገወጥ መሣሪዎችን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ሲባል ድንበሯን ዘግታለች፡፡

በተጨማሪም አምባሳደር ሬድዋን መንግሥት ባለፉት ጊዜያት ወደ ውይይት በመምጣት ነገሮችን ለማረጋጋት ሙከራዎችን ቢያደርግም ውጤት አላመጣም ሲሉ ከአሁን በኋላ ግን በውይይት ለመፍታት እንደማይሰራ ይገልፃሉ ፡፡

ይልቁንስ አሁን የተፈጠረው ሁኔታ ሀገርን መካድ፣ መከላከያ ሰራዊት ላይ ያልታሰበ ጥቃት በማድረስ ጉዳት ማስከተልና መሳሪያዎችንም መንጠቅ ሲሆን ቡድኑን ወደ ህግ በማምጣት ህገ መንግሥቱን ማስከበርና በእጁ የገቡትን መሣሪያዎች ማጥፋት እስካልተቻለ ድረስ ለሀገር ህልውና አስጊ ነው ይላሉ፡፡(ካፒታል ጋዜጣ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top