Connect with us

የጥቅምት ወር  የምግብ ዋጋ ግሽበት በ23 በመቶ  አሻቀበ

የጥቅምት ወር የምግብ ዋጋ ግሽበት በ23 በመቶ አሻቀበ
Ethiopian News Agency

ኢኮኖሚ

የጥቅምት ወር  የምግብ ዋጋ ግሽበት በ23 በመቶ  አሻቀበ

የጥቅምት ወር  የምግብ ዋጋ ግሽበት በ23 በመቶ  አሻቀበ

 

የጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ19 ነጥብ 3 በመቶ ከፍ ማለቱን ማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ።

ኤጀንሲው የጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም የምግብ ዋጋ ግሽበትም ካለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ጋር ሲነጻጸር በ23 ነጥብ 2 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተጠቅሷል።

በጥቅምት ወር በአብዛኞቹ የእህል ዓይነቶች ላይ የታየው ጭማሪ ለምግብ ዋጋ ግሽበት ከፍተኛ ሚና እንደነበረው ኤጀንሲው አስታውቋል።

በዳቦ፣ እንጀራ፣ ስኳር፣ ከውጭ የሚገባ የምግብ ዘይት፣ ድንች፣ በርበሬ እና የቡና ዋጋ ላይ ጭማሪ መታየቱም ለዋጋ ግሽበት መጨመር ምክንያት መሆኑን መግለጫው አመልክቷል።

በአንፃሩ በበቆሎ፣ ስንዴ፣ አትክልትና አንዳንድ የጥራጥሬ እህል ዓይነቶች ላይ መጠነኛ የዋጋ ቅናሽ መመዝገቡም ተገልጿል።

ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶች የዋጋ ግሽበት የጥቅምት 2013 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ14 ነጥብ 4 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ኤጀንሲው ገልጿል።

በአልኮል፣ ትምባሆ፣ ጫት፣ የቤት ማፅጃ እና ኢነርጂ (የማገዶ ከሰል)፣ የቤት መስሪያ ቁሶች፣ የህክምና እና ጌጣገጥ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በመኖሩ ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶች ላይ የዋጋ ግሽበት ከፍ እንዲል ማድረጉም ተመልክቷል፡፡

የጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው መስከረም ወር ጋር ሲነፃፀር በዜሮ ነጥብ 4 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።(ኢዜአ)

 

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top