Connect with us

በትግራይ ክልል የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ክልከላዎች ምንድናቸው? 

በትግራይ ክልል የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ክልከላዎች ምንድናቸው?
Photo: Social media

ዜና

በትግራይ ክልል የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ክልከላዎች ምንድናቸው? 

በትግራይ ክልል የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ክልከላዎች ምንድናቸው? 

 

በትግራይ ክልል ተፈፃሚ የሚሆነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን የሚያስፈፅሙ ግብረ ኃይል እንዲንቀሳቀሱ እውቅና ከሚሰጣቸው ሰዎች እና ተሽከርካሪዎች ውጭ ማንኛውም ሰው ወይም ተሽከርካሪ መመሪያው ተፈፃሚ በሚሆንበት ቦታ ሁሉ ከምሽት 2 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑ አስታውቋል።

ከግብረ ኃይሉ ፍቃድ ውጭ ማንኛውም ሰልፍ ፣ በአደባባይ ወይም በቤት ውስጥ ስብሰባ ማድረግ እንዲሁም 4 እና ከዛ በላይ ሆኖ በቡድን መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው ተብሏል።

ከመከላከያ ፣ ከፌዴራል ፖሊስ ፣ ሌሎች ፍቃድ ከተሰጣቸው የፀጥታ አካላት ውጪ ማኛውም የጦር መሳሪያ ሆነ ጉዳት የሚያደርሱ የተለያዩ እቃዎችን ይዞ መንቀሳቀስም ተከልክሏል።

በተያያዘ ዜና ዶ/ር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሰሞኑን ስለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በጠ/ሚኒስትሩ የሚመራው የአስቸኳይ ጊዜ ግብረሀይል በሚያወጣው መመሪያ መሰረት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ፖሊስ ወይንም የፀጥታ ሀይል ትጥቅ እንዲፈቱ፣ የሰአት እላፊ ገደብ ሊጥል እንደሚችል፣የጦር መሳሪያ እንቅስቃሴ ሊገድብ እንደሚችል፣ የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን ሊያግድ እንደሚችል፣ በህገወጥ ተግባር የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችን መያዝ እና የተጠርጣሪ ቤቶችና ተሽከርካሪዎችን መበርበር እንደሚችል፣ ከሰላማዊ እንቅስቃሴ ተቃራኒ የሆኑ መግለጫዎችን ሊከለክል እንደሚችል መናገራቸው ይታወሳል።

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top